TIKVAH-MAGAZINE

Канал
Логотип телеграм канала TIKVAH-MAGAZINE
@tikvahethmagazineПродвигать
199,32 тыс.
подписчиков
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
" በዓለም አቀፍ ደረጃ ከስኳር በሽታ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ከ800 ሚሊዮን በልጠዋል " - ጥናት

° " አገራት ጤናማ አመጋገብን እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የሚደግፉ ፖሊሲዎችን ማውጣት አለባቸው " ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም

ከ1990 ጀምሮ የስኳር ታማሚዎች ቁጥር በአራት እጥፍ በመጨመር በአለም ከ800 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በስኳር በሽታ መያዛቸውን የአለም ጤና ድርጅት ያወጣው አዲስ ጥናት አመለከተ።

ጥናቱ ይፋ የተደረገው የዓለም የስኳር በሽታ ቀን በትላንትናው እለት በተከበረ ቀን ነው።

ጥናቱ የተሰራው የአለም ጤና ድርጅት ከ NCD Risk Factor Collaboration (NCD-RisC) ጋር በመተባበር ሲሆን ከ1,500 ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን አሳትፏል።

ከ18 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ 140 ሚሊዮን ሰዎችን መረጃ በመተንተን የተሰራው ይህ ጥናት የስኳር በሽታ የስርጭት መጠን እና የህክምና ሽፋን ላይ ትኩረቱን በማድረግ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

በዚህም በ1990 እና 2022 መካከል ባለው ጊዜ የስኳር ህመም ከ7 ወደ 14 በመቶ መጨመሩን ያመለከተው ጥናቱ የስኳር ህመም መጠኑ እየጨመረ፤ የህክምና ተደራሽነቱም ዝቅተኛ እየሆነ መምጣቱን አሳይቷል።

አፍሪካ ደቡብ-ምስራቅ እስያ እና ምስራቅ ሜዲትራኒያን ዝቅተኛው የስኳር በሽታ ህክምና ሽፋን ያላቸው አህጉራት እንደሆኑ ተመላክቷል።

በ2022፣ ዕድሜያቸው 30 እና ከዚያ በላይ የሆኑ 450 ሚሊዮን የሚጠጉ አዋቂ የስኳር ህመምተኞች ውስጥ 59 በመቶው የስኳር በሽታ ህክምና እንደማያገኙ ጥናቱ አመላክቷል።

ይህ ቁጥር በ1990 ከነበሩት በስኳር ተይዘው የማይታከሙ ታማሚዎች ጋር ሲተያይ በ3.5 ጭማሪ ያሳየ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ከስኳር በሽታ ተማሚዎች ውስጥ ዘጠና በመቶው ያልታከሙ አዋቂዎች የሚገኙት ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ነው ተብሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም " ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ የስኳር በሽታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አይተናል " ብለዋል።

በሽታው የተስፋፋው ከመጠን ባለፈ ውፍረት፣ ጤናማ ባልሆነ አመጋገብ እና የአካል ብቃት  እንቅስቃሴ ባለማድረግ እንደሆነ ሲገልፁ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ደግሞ የበሽታውን ሁኔታ እንዳባባሱት ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ " ዓለም አቀፉን የስኳር በሽታ ለመቆጣጠር አገራት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አለባቸው " ሲሉም አሳስበዋል።

አክለውም አገራት ጤናማ አመጋገብን እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የሚደግፉ ፖሊሲዎችን በማውጣት እና በሽታን በመከላከል እና በመቆጣጠር የበቃ የጤና ስርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

@tikvahethmagazine
#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ3 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በትራንስፖርት ዘርፍ ለማሰማራት የሚያስችል ስምምነት ከተማ አስተዳደሩ ከስዊፍት ቴክኖሎጂ እና ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር ተፈራርሟል።

የስዊፍት ቴክኖሎጂ ተወካይ አቶ ብሩክ አሸብር  በሚቀጥሉት ሶስት አመታት የባጃጅ ተሽከርካሪዎችን በኤሌትሪክ መኪኖች ለመተካት  መታቀዱን ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለትም 21 የኤሌትሪክ መኪኖች መመረቃቸውን የገለጹት አቶ ብሩክ፥ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እነዚህን ዘመናዊ የኤሌትሪክ የትራንስፖርት መኪኖች በፍጥነት ስራ ለማስጀመር የብድር ምችችት እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።

ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖቹ ወደ ስራ በሚገቡበት ወቅት የሀይል አቅርቦት ችግር እንዳይከሰት በተለያዩ ቦታዎች ቻርች ማድረጊያ ጣቢያዎች እንደሚዘጋጁም ተገልጿል።

@tikvahethmagazine
ቢጂአይ ኢትዮጵያ በባቱ ከተማ ያስገነባውን ትምህርት ቤት አስመርቆ ለማህብረሰቡ አስረከበ

ቢጂአይ ኢትዮጵያ በባቱ ከተማ ያስገነባውን አባ ገዳ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የምረቃ ስነ-ስርዓት በዛሬው እለት አስመርቋል።

ትምህርት ቤቱ ተገንብቶ ያለቀው በ 6ወራት ጊዜ ውስጥ ሲሆን ተማሪዎች በአዲሱ የትምህርት ዘመን ትምህርት መጀመራቸው ተነግሯል።

600 ህፃናት ተማሪዎችን በፈረቃ ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለው ይህ ትምህርት ቤት 9 ሚሊዮን ብር እንደወጣበት የቢጂአይ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሄርቬ ሚልሃድ ተናግረዋል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የከተማው እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ባለድርሻ አካላት ትምህርት ቤቱ እንደ አጥር ያሉ አስፈላጊ  ግብዓቶች እንዲሟሉለት ጠይቀዋል።

ቢጂአይ በማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ በሰራው ስራ በዘንድሮው አመት ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ በትምህርት፣ ጤና፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ላይ ማውጣቱን የ
ዋና ስራ አስፈፃሚው ጠቅሰዋል።

ኩባንያው ዛሬ በባቱ ከተማ ያስመረቀውን ፕሮጀከት ጨምሮ በሐዋሳ፤ በጕራጌ ዞን ዘቢዳር እና በኮምቦልቻ ባሉ ከተሞች የትምህርት መሰረተ ልማትን በመገባት ለነዋሪዎች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።

በዘቢዳርና በኮምቦልቻ ያሉ ት/ቤት ግንባታዎች በቅርቡ  ለማህበረሰቡ እንደሚያስረክብም ኩባንያው አሳውቋል።

@tikvahethmagazine
የሰውነት አካል ልገሳ ጉዳይ በኢትዮጵያ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ʺሰዎች ኩላሊታችንን ግዙን እያሉ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እንደሚመጡ ተገለጸʺ በሚል የሚሰራጨው ዜና ሀሰት እና ኮሌጃችንን  የማይመለክት ነው ብሏል፡፡

ኮሌጁ ʺሰዎች ኩላሊት ግዙን ብለው ወደ ማእከሉ ይመጣሉʺ የሚለው አባባል  ፍጹም ከእውነት የራቀ መሆኑ መታወቅ አለበት ሲል አሳውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ህግ የሰውነት ክፍልን በፈቃደኝነት ስለመለገስ ምን ይላል?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠበቃ እና የህግ አማካሪ የሆኑትን አቶ ዳንኤል ፈቃዱን አነጋግሯል።

ጥያቄ:-የሰውነት ክፍልን በፈቃደኝነት ስለመለገስ የኢትዮጵያ ህግ ምን ይላል?

አቶ ዳንኤል:- "የኢትዮጵያ ህግ እንደሚደነግገው እና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያም እንደሚያመላክተው የሰውነት አካልን በፈቃደኝነት መለገስ በዘመዳሞች መካከል ብቻ ይፈቀዳል" ብለዋል።

ነገር ግን በህጉ መሰረት በዘመዳሞች መካከል የሚደረግን የሰውነት አካል ልገሳ ምንም አይነት የገንዘብ ውል እንዳይኖረው ክልከላ የሚያስቀምጥ ሲሆን ገንዘብን እንደ ውል በማስቀመጥ የሚደረግ ልገሳን ህገ ወጥ መሆኑን ተናግረዋል ።

ጥያቄ:- የሰውነት አካልን በፈቃደኝነት ለመለገስ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው።

አቶ ዳንኤል:- ህጉ አስገዳጅ ነገሮች ብሎ ካስቀመጣቸው በዘመዳሞች መካከል ብቻ ፣ያለ ምንም ክፍያ እና በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት ገልጸው ከሦስቱ አንዱ ከጎደለ ልገሳው ተቀባይነት እንደማይኖረው ተናግረዋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የምግብ፣ መድኃኒት እና የጤና እንክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ደንብ 299/2006 እንደሚያስቀምጠው የሰውነት አካልን በፈቃደኝነት ዝምድና ለሌለው አካል ለመለገስ በመሀከል ምንም አይነት የጥቅም ግንኙነት አለመኖሩን መረጋገጥ እንዳለበት እንደሚያስቀምጥ ተናግረዋል ።

ይህንን የሚያረጋግጥ ራሱን የቻለ ተቋም መኖሩን ጠቁመዋል ።

ጥያቄ :- ከላይ ከተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች ውጪ የሰውነት ክፍሉን በሽያጭ ያቀረበን አካል ህጉ ምን አይነት ቅጣት ያስቀምጣል?

አቶ ዳንኤል:- ህጉ በሦስት መንገድ የሚያየው መሆኑን ተናግረዋል።

- አስተዳደራዊ እርምጃ
-የወንጀል ተጠያቂነት
-የፍትሃብሔር ተጠያቂነት

በ 1997 በወጣው በኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 573 ላይ እንደተቀመጠው በህጉ ከተቀመጠው ውጪ ይህንን ድርጊት የፈጸመ ከሆነ:-

በተቋሙ ላይ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደሚጣል የሚያስቀምጥ ሲሆን ይህም ፈቃድን መንጠቅ ሊሆን ይችላል።

ለጋሹ በህይወት ያለ ከሆነ ከ 3-5 ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት እና የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ይላል።

ወሳጁ ሐኪም የአካል ክፍሉን ከሞተ አካል የወሰደ ከሆነ ከ 5 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ያስቀምጣል ።

ወሳጁ ሐኪም የአካል ክፍሉን በህይወት ካለ ሰው በህጉ ከተቀመጠው ውጪ ከወሰደ ከ 5-10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ አስቀምጧል።

በማጭበርበር ፣በማስገደድ ወይም በማታለል ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው ሳይፈቅድ አካል ክፍል የወሰደ ከሆነ ከ 10-25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ አስረድተዋል።

የፍትሀብሔር ተጠያቂነትን በሚመለከት የሰውነት አካል ልገሳ ያደረገ ሰው ልገሳውን በማከናወኑ የደረሰበት ጉዳት ካለ ለፍርድ ቤት በሚያቀርበው ክስ መሰረት ጉዳቱ በሚመለከተው አካል ተረጋግጦ የሚገባውን ካሳ የሚያገኝበት አሰራር መሆኑን የህግ ባለሞያው ተናግረዋል።

#ምስል: ከዚህ ዜና ጋር የተያያዘው ምስል በሰው ሰራሽ አስተውሎት (Generative AI) አማካኝነት የተሰራ ነው።

@tikvahethmagazine
ሮያል ሆምስ ሪል እስቴት

በሴራሚክ አቅርቦት የሚታወቀው አንጋፋው ሮያል ሴራሚክስ ሮያል ሆምስ ሪል አስቴትን ይዞሎት ቀርቧል ።

በመካኒሳ ጀርመን አደባባይ ግንባታ ደረጃቸው 70% የደረሱ አፓርትመንቶች በጥራት ገንብቶ እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ በካሬ 70,000 ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ ይሎታል!

ኮምፓዉንዳችን ያካተተው ጂም፣ስፓ፣ ሱፐርማርኬት፣የህፃናት ማቆያ፣አረንጓዴ ስፍራ፣የህፃናት መጫወቻ ስፍራ፣ሰገነት አና በቂ የሆነ የመኪና መቆምያ።

ለበለጠ መረጃ በ 0930627256 ወይም 0911005545 ይደውሉልን ።
ባሳለፍነው ሩብ ዓመት በአዲስ አበባ 107 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል ተብሏል።

ሁሉም የደንብ ጥሰቶች የትራፊክ አደጋን የሚያስከትሉ ቢሆኑም ዋና ዋና በሚባሉ የትራፊክ አደጋ መንስኤዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየተሰራ መሆኑን በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የትራፊክ ሞያ እና ህዝብ ግንዛቤ ዲቪዥን ሃላፊ  ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ሃላፊው በ2017 ሩብ ዓመት 612 ሺ 445 ግለሰቦች በትራፊክ ደንብ ጥሰት ምክንያት ለቅጣት መዳረጋቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥ:-

° መንጃ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሲያሽከረክሩ የተገኙ 306

° ሐሰተኛ መንጃ ፈቃድ ይዘው ሲያሽከረክሩ የተገኙ 213

° ቀይ የትራፊክ መብራት የጣሱ 45 ሺ

° የደህንነት ቀበቶ ሳያስሩ ያሽከረከሩ 24 ሺ

° የእጅ ስልክ እያዋሩ ሲያሽከረክሩ የተገኙ 28 ሺ

° አመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ሳያከናውኑ ሲያሽከረክሩ የተገኙ 6,671

° ከፍጥነት ወሰን በላይ ሲያሽከረከሩ የተገኙ 7,316 ሰዎች ይገኙበታል።

ጠጥቶ ማሽከርከርን በሚመለከት ለ28 ሺ አሽከርካሪዎች ምርመራ ተደርጎ 871 ዱ በህግ ከተቀመጠው በላይ ጠጥተው የተገኙ በመሆናቸው ምክንያት እንዲቀጡ መደረጋቸውን ተናግረዋል።

በሩብ አመቱ 107 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በ 2016 ሩብ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት 106 ሰዎች ህይወታቸው አልፎ ነበር።

ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር 379 ሲሆን በ 2016 ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 385 ሰዎች ጋር ሲነጻጸር መቀነስ ታይቶበታል።

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት በአንጻሩ ከፍተኛ ጭማሪን ያሳየ ሲሆን በሩብ ዓመቱ 8,953 ንብረቶች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ባሳለፍነው ሩብ ዓመት ካጋጠመው 8,253 የንብረት ጉዳት ጋር ሲነጻጸር በ 700 ብልጫ ያለው ነው።

በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት በገንዘብ አልተተመነም።

የተሽከርካሪ መለያ፣ መመርመሪያ እና መመዝገቢያ አዋጅ 681/2002 መሰረት ማንኛውም ተሽከርካሪ በዓመት አንድ ጊዜ የተሽከርካሪ የምርመራ ሂደትን አልፎ በመንገድ ላይ መንቀሳቀስ እንዳለበት ቢደነግግም በሩብ ዓመቱ ከ 6 ሺ በላይ ተሽከርካሪዎች ይህንን ሳይፈጽሙ በመንገድ ላይ መገኘታቸውን ኃላፊው አክለው ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በገበያ ሞሎች ላይ የቁጥጥር ሥራ በዘመቻ መልክ እየሰራው ነኝ ብሏል። የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች በግብር ከፋይነት ተመዝግበው ደረሰኝ የማይሰጡ በመሆናቸው እና ችግሩም በጣም እየሰፋ በመሆኑ ወጥነት ባለው መንገድ ህጉን እንዲያከብሩ እና ወደስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል። ቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ…
"ያለደረሰኝ አትሽጡ አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም" -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች በግብር ከፋይነት ተመዝግበው ደረሰኝ የማይሰጡ በመሆናቸው እና ችግሩም በጣም እየሰፋ በመሆኑ ወጥነት ባለው መንገድ ህጉን እንዲያከብሩ እና ወደስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

ቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ የቁጥጥር ስራው ከዚህ ቀደምም የነበረ ቢሆንም በዘመቻ መልክ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ዘመቻ ሲባል ወደ ቫት ስርዓት ውስጥ ያልገቡትን ማስገባት ፣ፈቃድ የሌላቸው ፈቃድ እንዲያወጡ ማድረግ፣ ደረጃቸው ደረሰኝ መስጠት የሚገባቸው ሆኖ ሳለ የማይሰጡትን ደረሰኝ አስፈቅደው እና አሳትመው መጠቀም እንዲጀምሩ ማስቻልን ያካትታል።

የቁጥጥር ስራው በተለይም በገበያ ሞሎች ላይ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘም በዛሬው ዕለት በመርካቶ አካባቢ ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው የሚል የተለያዩ ውዥንብሮች መፈጠራቸው እና ይህም አንዳንድ ነጋዴዎችን ግርታ ውስጥ መክተቱ ተናግሯል።

ስለ ጉዳዩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽን አነጋግሯል።

ዳይሬክተሩ በምላሻቸው "ጠዋት ሱቆች ሁሉ ተዘግተዋል ተብሎ ተወርቶ በአካል ዞሬ አይቻለሁ የተወሰኑ ሱቆች የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተዘጉ የሚመስሉ አሉ ነገር ግን መደበኛ ሥራ ቀጥሏል" ብለዋል።

"በዚህ ደረጃ ተዘግቷል ለማለት እይቻልም ተዘጋ የሚባለው ምን ያህል ሱቅ ሲዘጋ ነው? አንድ ቤት ሁለት ቤት ተዘግቶ ይሆናል ነገር ግን አብዛኛው እየሰራ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ህገ ወጥነትን ማስቀጠል የሚፈልግ አካል  አለ ያለት ዳይሬክተሩ " ሆን ብሎ የሆነ ነገር ተሰርቷል፣ ሊሰራ ነው የሚል ውዥንብር መፍጠር የሚፈልግ አካል እንዳለ ነው የተረዳሁት " ብለዋል።

"ቁጥጥር ሊደረግ ነው በተለይ አስመጪ እና አከፋፋይ ላይ ሲባል ቸርቻሪ ላይ ስጋት የሚፈጥሩ አሉ፣ በትላንትናው ዕለትም የሚሸሹ ነጋዴዎች ገጥመውናል ያለፍቃድ ይነግዱ የነበሩ ናቸው ብንጠየቅ መልስ የለንም በሚል ስጋት ነው። ሱቃቸውን ቢዘጉም እነሱ ናቸው የሚሆኑት" ሲሉ አክለዋል።

ተዘግቷል የሚለውንም እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል በእርግጥ የተዘጋ ነው ወይስ ነጋዴው በsocial ችግር ሱቃቸውን ዘግተው ስለሌሉ ነው የሚል ጥርጣሬ የሚያጭር ስለሆነ የተዘጉ አይደሉም ወደሚል ድምዳሜ ነው የደረስነው ብለዋል።

ይርጋ ሃይሌ የገበያ ሞል ላይ ከ 15 ቀን በፊት ኮንትሮባንድ ስለነበረ ጎምሩኮች በርብረዋል ደረሰኝ የሌለውን ወርሰዋል ደረሰኝ ያለውን ጥለው ወጥተዋል።

"የገበያ ሞሉ ላይ እቃዎችን መለየት አስቸጋሪ ስለነበር እና ሰዎቹም ተባባሪ ስላልነበሩ ለጊዜው ታሽጎ ነበር"  ያሉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ሀሉም መከፈታቸውን ጠቁመው የቀረ ካለ በንግድ ቢሮ በኩል ፈቃድ ያልነበረው በመሆኑ በተወሰደ እርምጃ መሆኑን ጠቁመዋል።

"ታሽገው የነበሩ አብዛኛው ሱቆች ተከፍተዋል እስካሁን ያልተከፈተ ካለ ፈቃድ ስላላወጣ ነው የሚሆነው በተረፈ እቃ የሚወረሰው ኮንትሮባንድ ሲሆን ብቻ ነው" ብለዋል።

በተጨማሪም ሁሉም ሰው ደረሰኝ ስለማይሰጥ የሚመለከተው ብቻ ነው ደረሰኝ  እንዲሰጡ የሚጠበቀው መስጠት የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች ደረሰኝ እየሰጡ ግብይታቸውን ይቀጥሉ ብለዋል ።

"እቃችሁ እየተወረሰ ነው፣ ሊወረስብን ነው ፣የሚሉ አካላት እቃቸው ምን ስለሆነ ነው የሚወረሰው ? እንደዚህ የሚሉ አካላት ኮንትሮባንድ ስለሆነ ይመስላል።"

አክለውም "ያለደረሰኝ አትግዙ ፣የሚሸጥላችሁን ጠቀሙ እኛ ደግሞ ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈጽምን አካል እንቆጣጠራለን ብለናል የምንከታተላቸውም ለዛ ነው።" ያሉ ሲሆን እቃ ለመውረስ የህግ መሰረት የሚያስፈልግ መሆኑን ተናግረው እቃ የሚወረሰው የታክስ እዳ ማካካሻነት ከተያዘ ብቻ ነው መሆኑን አስረድተዋል።

"ግብይት ላይ ያለ እቃን የታክስ ማካካሻ ብለን የምንወርስበት ምክንያት የለንም። ክፍተት ያለበትን ነጋዴ ለማወናበድ የሚሮጥ ሌላ ጥላ የሚፈልግ አካል የሚያወራው ወሬ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ዳይሬክተሩ " ያለደረሰኝ አትሽጡ አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም" ብለው ይህም ለነጋዴዎች በደብዳቤ እንዲደርሳቸው መደረጉን ነግረውናል።

@tikvahethmagazine
"ከ250 በላይ ሀይስኩሎች ላይ የዲጂታል ላይብረሪ አቋቁሚያለው"  SRE

በኢትዮጵያ ‘Scientific Revolution Earth (SRE) በሚል የተመሰረተውየቴክኖሎጂ ኩባንያ የ10ኛ ዓመት በዓሉን አክብሯል። 

ተቋሙ በስካሁኑ ጉዞው በገጠራማው ክፍል ሁሉ ያለ ኢንተርኔት አገልግሎት የዲጂታል ላይብረሪዎችን ማቋቋም፤ የትራፊክ ፍሰት የሚቆጣጠርና ሌሎች ከውጪ በውድ ዋጋ የሚገዙ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ማምረቱን ገልጿል።

የዲጂታል ላይብረሪውን በተመለከተ ለምሳሌ በትግራይ ክልል በራያ የኒቨርሲቲ ድጋፍ ከ20 በላይ አካባቢዎች ሃይስኩሎች ላይ መተግበሩን እና በቡልቲም ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ደግሞ በአካባቢው ባሉ በርካታ ተቋማት ላይ መተግበሩን አስረድቷል።

በአማራ ክልል በተመሳሳይ በአማራ ልማት ማኀበር አማካኝነት ከ110 በላይ ተግባሪዊ ሆኗል ያለው ድርጅቱ በአማራ ትምህርት ቢሮ አማካኝነት ደግሞ ደሴ፣ ወልዲያ፣ ሰቆጣ፣ ከሚሴ መምህራት ትምህርት ኮሌጆች ኢምፕልመንት ተደርጓል ሲል አስታውቋል።

በአጠቃላይ የድጅታል ላይብረሪው ከ250 በላይ ሀይስኩሎች፣ ከ16 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ መተግበሩን ገልጿል።

በተቋሙ የለሙ ቴክኖሎጂዎች በሀገር ውስጥ በመመረታቸው ከውጪ ከሚገዙበት ዋጋ 50 በመቶ ቅናሽ እንዳላቸውም ተገልጿል። በተጨማሪም የአንድ አመት ዋስትና እና በቀላሉ የጥገና አገልግሎት ማመቻቸት ይቻላል ተብሏል።

ተቋሙ 10ኛ ዓመቱን አስመልክቶ ባዘጋጀው የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የማስተዋወቅ ዝግጅት እስካሁን በሪሰርች ያሉ 32 ፕሮዳክቶችን ጨምሮ በዕለቱ ለዕይታ ያቀረባቸውን 10 የሚሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን አስተዋውቋል።

ተቋሙ አንዳንዶቹ ቴክኖሎጂዎች የመንግስትን አብሮነት የሚጠይቀ ናቸው ብሏል። "ለምሳሌ እንደ ትራፊክ ራዳር፣ የትራፊክ መብራቶች፣ ከተማው ላይ ያሉ የስማርት ሲቲ ቴክኖሎጂዎች ከመንግስት ጋር መስራትን የሚፈልጉ ናቸው” ነው ያለው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethmagazine
ኢትዮጵያ ለዲጂታል ማጭበርበር ከተጋለጡ ሃገራት መካከል መሆኗን ጥናት አሳይቷል።

Sumsub የተሰኘ መረጃ ጠቋሚ የ103 ሀገራትን ለዲጂታል ማጭበርበር ያላቸውን ተጋላጭነት የሚያሳይ የመጀመሪያውን አለም አቀፍ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ጥናቱ የዲጂታል ማጭበርበር ስጋትን የሚያሳይ በ103 አገሮች ላይ የተደረገ የመጀመሪያው ጥልቅ ጥናት ነው ተብሏል።

ኢትዮጵያ ለዲጂታል ማጭበርበር ተጋላጭ ተብለው ከተለዩ ሃገራት መካከል የተቀመጠች ሲሆን በሰንጠረዡ ላይም ከ 113 ሃገራት በ 99 ላይ ተቀምጣለች።

ከዲጂታል ማጭበርበር ደህንነታቸው የተጠበቁ 10 አገሮች መካከል ሲንጋፖር፣ ሉክሰምበርግ፣ ስዊዘርላንድ፣ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፊንላንድ፣ ስዊድን፣ አየርላንድ እና ሊቱዌኒያ ይጠቀሳሉ።

ለዲጂታል ማጭበርበር ተጋላጭ የሆኑ ወይም ደህንነታቸው ውስን የሆኑ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ ፣ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዥያ፣ አርጀንቲና፣ ዩክሬን፣ ብራዚል፣ አልጄሪያ እና ሲሪላንካ ተጠቃሽ ናቸው ይላል ሪፖርቱ።

ጥናቱ ከቁጥሮች ይልቅ ለዲጂታል ማጭበርበር የሚያጋልጡ መንስኤዎችን በመለየት የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ በማለም የተደረገ ነው።

እስካሁን ድረስ፣ ዲጂታል ማጭበርበር በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ስጋት ቢፈጥርም ስለ ማጭበርበር መጠን የሚያሳይ አጠቃላይ የሆነ ዓለም አቀፍ ትንታኔ አልነበረም።

ትንበያዎች እንደሚያሳዩት በአለም በኦንላይን የክፍያ ማጭበርበር ሳቢያ የሚደርሰው ኪሳራ ከ2023 እስከ 2028 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ362 ቢሊዮን ዶላር በላይ ይሆናል ይላል።

የጥናቱ ዓላማ በዓለም ዙሪያ የኦንላይን ማጭበርበርን የሚያነሳሱትን ዋና ዋና ምክንያቶች እና ሁኔታዎች በጥልቀት በመመርመር ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ግንዛቤዎችን ለመስጠት፣ መንግስታት እና ተቆጣጣሪዎች ማጭበርበርን የሚገቱ የታለሙ እርምጃዎችን እንዲተገብሩ ለማስቻል ያለመ ነው ።

ለዲጂታል ማጭበርበር ተጋልጠው ያቃሉ? እንዴት ?ያካፍሉን!

@tikvahethmagazine
ሳዑዲ አረቢያ በ100 ቢሊዮን ዶላር በጀት አዲስ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ልትገነባ ነው።

ሳዑዲ አረቢያ ከጎረቤት አገሯ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጋር ለመወዳደር የሚያስችላትን እስከ 100 ቢሊዮን ዶላር በጀት የተመደበለት አዲስ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ልትገነባ ነው ተብሏል።

"Project Transcendence" የተሰኘው ይህ ተነሳሽነት አዳዲስ ባለተሰጥኦዎችን ወደ ሀገሪቱ የመመልመል፣ የቴክኖሎጂ ስነ-ምህዳሩን በማዳበር የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ በማበረታታት ላይ ያተኩራል ተብሏል።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘም ከቀናት በፊት የጎግል ኩባንያ በሳውዲ አረቢያ  የአረብኛ ቋንቋ AI ሞዴሎችን እና ሳዑዲ-ተኮር AI መተግበሪያዎችን ለመስራት የሚያገለግል ማዕከል ለመገንባት ተስማምቷል።

ይህ የሳውዲ ፕሮጀክት አላማው ከተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ገበያ ጋር በመወዳደር የሰለጠነ የሰው ሀይል ማቅረብ ነው ተብሏል።

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በ2017 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሚኒስትር ዴኤታ በመሾም የመጀመሪያዋ ሀገር ስትሆን በ2031የ AI የስህበት ማዕከል ለመሆን ብሔራዊ ስትራቴጂ ነድፋ እየተንቀሳቀሰች ያለች ሀገር ናት።

@tikvahethmagazine
🌺ውብ የሆኑ አበባዎች ወብ ለሆናችሁ ደንበኞቻችን
🌺ለሚወዱት ፍቅረኛዎ በስጦታ ለመስጠት
🌺ለፍቅርዓመታዊ በዓሎ(Anniversary
🌺ለቀለበት ኘሮግራሞ(Engagement)
🌺 ለአራስ ጥየቃ
🌺ለሰርግ (Full package ) በተጨማሪ ለተለያየ ፕሮግራሞ አስቀድመው ደውለ ይዘዙን ያሉበት እናደርሳለን ።
🌺 ለሽያጭ ምትፈልጉ በብዛት ለመውሰድ እታች ባለው ቁጥር ይደውሉ
Contact us on -0911359234
                         -0954882764
https://t.center/bluebellgiftstore
ወጋገን ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የአንድ አክሲዮን ትርፍ 36.89 በመቶ መድረሱን ገለጸ

ባንኩ እ.ኢ.አ በ2023/24 በጀት ዓመት በታሪኩ ከፍተኛውን ብር 9.8 ቢሊዮን ገቢ ማስመዝገቡን አስታውቋል።

ባንኩ ዛሬ በሒልተን ሆቴል 31ኛ መደበኛና 15ኛ አስቸኳይ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የጠራ ሲሆን፣ በዚህም ከታክስ በፊት 2.2 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን የባንኩ የዳይሬክቶሬት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዲሹ ሁሴን ተናግረዋል።

በገለጻው መሠረት፦

- ባንኩ 9.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን፣ ተቀማጭ ገንዘቡ ደግሞ 22 በመቶ እድገት በማሳዬት 52.1 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ገልጿል።

- እ.ኤ.አ ሰኔ 30/2024 የባንኩ ባለአክሲዮኖች ብዛት 12 ሺሕ፣ የተከፈለ ካፒታሉ 27 በመቶ እድገት በማሳዬት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 5.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

- የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል 33 በመቶ እድገት በማሳዬት 9.2 ቢሊዮን ብር፣ የአንድ አክሲዮን ትርፍ 36.9 በመቶ ደርሷል።

- ባንኩ የሰጠው ብድር በዓመቱ መጨረሻ ሲሰላ 45.1 ቢሊዮን ብር፣ የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 65.7 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
አሐዱ ባንክ ከታክስ በፊት ብር 119.96 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ገለፀ

አሐዱ ባንክ 3ተኛ መደበኛ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን ዛሬ አከናውኗል።

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ሰብስቤ የባንኩን የሥራ እንቅስቃሴና የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት ለባለአክስዮኖች አቅርበዋል፡፡

የባንኩ ሪፖርት ምን ይመስላል ?

- ባንኩ ከታክስ በፊት ብር 119.96 ሚሊዮን ትርፍ ማስመዝገቡን ገልጿል።

- ባንኩን የቅርንጫፍ ተደራሽነት ወደ 104 ከፍ ማድረግ ችያለው ያለ ሲሆን የደንበኞች ቁጥርን 704,000 በማድረስ የተቀማጭ ሃብት መጠኑ ብር 4.6 ቢሊዮን መድረሱን አሳውቋል።

- በውጭ ምንዛሪ ረገድ 80.1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማሰባሰብ መቻሉን ሲጠቀስ በዚህ በጀት ዓመት በባንኩ የተሰጠ የብድር መጠን ብር 1.7 ቢሊዮን ደርሷል።

- የባንኩ አጠቃላይ ሃብት ብር 6.26 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ የባንኩ የተፈረመ የካፒታል መጠን ብር 1.4 ቢሊዮን ነው። አጠቃላይ የተከፈለ ካፒታል መጠን ደግሞ ወደ ብር 1.03 ቢሊዮን ማድረስ መቻሉ ተነግሯል።

አቶ አንተነህ እንደገለፁት የባንኩ ዘርፍ ተለዋዋጭና ጥብቅ በሆኑ መመሪያዎች ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፣ ለማሳያነት በነሐሴ 2016 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የናረውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር በማለም፣ የንግድ ባንኮች በሚያበድሩት ብድር ላይ ጣርያ ማስቀመጡን አስታውሰዋል፡፡

ይህ ፓሊሲ የንግድ ባንኮች በሚያበድሩት ብድር ላይ ጣርያ ማስቀመጡን እና ፓሊሲው አዳዲስ ባንኮችን በከፍተኛ ሁኔታ ገቢ ከሚያስገኝላቸው የብድር አገልግሎት ስለሚገድብ፣ በባንኮቹ አፈጻጸም እና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም በሀብት ማንቀሳቀስ አቅም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ እንደነበር ጠቅሰዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
Telegram Center
Telegram Center
Канал