View in Telegram
ሳዑዲ አረቢያ በ100 ቢሊዮን ዶላር በጀት አዲስ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ልትገነባ ነው። ሳዑዲ አረቢያ ከጎረቤት አገሯ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጋር ለመወዳደር የሚያስችላትን እስከ 100 ቢሊዮን ዶላር በጀት የተመደበለት አዲስ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ልትገነባ ነው ተብሏል። "Project Transcendence" የተሰኘው ይህ ተነሳሽነት አዳዲስ ባለተሰጥኦዎችን ወደ ሀገሪቱ የመመልመል፣ የቴክኖሎጂ ስነ-ምህዳሩን በማዳበር የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ በማበረታታት ላይ ያተኩራል ተብሏል። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘም ከቀናት በፊት የጎግል ኩባንያ በሳውዲ አረቢያ  የአረብኛ ቋንቋ AI ሞዴሎችን እና ሳዑዲ-ተኮር AI መተግበሪያዎችን ለመስራት የሚያገለግል ማዕከል ለመገንባት ተስማምቷል። ይህ የሳውዲ ፕሮጀክት አላማው ከተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ገበያ ጋር በመወዳደር የሰለጠነ የሰው ሀይል ማቅረብ ነው ተብሏል። የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በ2017 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሚኒስትር ዴኤታ በመሾም የመጀመሪያዋ ሀገር ስትሆን በ2031የ AI የስህበት ማዕከል ለመሆን ብሔራዊ ስትራቴጂ ነድፋ እየተንቀሳቀሰች ያለች ሀገር ናት። @tikvahethmagazine
Telegram Center
Telegram Center
Channel