View in Telegram
ኢትዮጵያ ለዲጂታል ማጭበርበር ከተጋለጡ ሃገራት መካከል መሆኗን ጥናት አሳይቷል። Sumsub የተሰኘ መረጃ ጠቋሚ የ103 ሀገራትን ለዲጂታል ማጭበርበር ያላቸውን ተጋላጭነት የሚያሳይ የመጀመሪያውን አለም አቀፍ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ የዲጂታል ማጭበርበር ስጋትን የሚያሳይ በ103 አገሮች ላይ የተደረገ የመጀመሪያው ጥልቅ ጥናት ነው ተብሏል። ኢትዮጵያ ለዲጂታል ማጭበርበር ተጋላጭ ተብለው ከተለዩ ሃገራት መካከል የተቀመጠች ሲሆን በሰንጠረዡ ላይም ከ 113 ሃገራት በ 99 ላይ ተቀምጣለች። ከዲጂታል ማጭበርበር ደህንነታቸው የተጠበቁ 10 አገሮች መካከል ሲንጋፖር፣ ሉክሰምበርግ፣ ስዊዘርላንድ፣ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፊንላንድ፣ ስዊድን፣ አየርላንድ እና ሊቱዌኒያ ይጠቀሳሉ። ለዲጂታል ማጭበርበር ተጋላጭ የሆኑ ወይም ደህንነታቸው ውስን የሆኑ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ ፣ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዥያ፣ አርጀንቲና፣ ዩክሬን፣ ብራዚል፣ አልጄሪያ እና ሲሪላንካ ተጠቃሽ ናቸው ይላል ሪፖርቱ። ጥናቱ ከቁጥሮች ይልቅ ለዲጂታል ማጭበርበር የሚያጋልጡ መንስኤዎችን በመለየት የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ በማለም የተደረገ ነው። እስካሁን ድረስ፣ ዲጂታል ማጭበርበር በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ስጋት ቢፈጥርም ስለ ማጭበርበር መጠን የሚያሳይ አጠቃላይ የሆነ ዓለም አቀፍ ትንታኔ አልነበረም። ትንበያዎች እንደሚያሳዩት በአለም በኦንላይን የክፍያ ማጭበርበር ሳቢያ የሚደርሰው ኪሳራ ከ2023 እስከ 2028 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ362 ቢሊዮን ዶላር በላይ ይሆናል ይላል። የጥናቱ ዓላማ በዓለም ዙሪያ የኦንላይን ማጭበርበርን የሚያነሳሱትን ዋና ዋና ምክንያቶች እና ሁኔታዎች በጥልቀት በመመርመር ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ግንዛቤዎችን ለመስጠት፣ መንግስታት እና ተቆጣጣሪዎች ማጭበርበርን የሚገቱ የታለሙ እርምጃዎችን እንዲተገብሩ ለማስቻል ያለመ ነው ። ለዲጂታል ማጭበርበር ተጋልጠው ያቃሉ? እንዴት ?ያካፍሉን! @tikvahethmagazine
Telegram Center
Telegram Center
Channel