View in Telegram
"ከ250 በላይ ሀይስኩሎች ላይ የዲጂታል ላይብረሪ አቋቁሚያለው"  SRE በኢትዮጵያ ‘Scientific Revolution Earth (SRE) በሚል የተመሰረተውየቴክኖሎጂ ኩባንያ የ10ኛ ዓመት በዓሉን አክብሯል።  ተቋሙ በስካሁኑ ጉዞው በገጠራማው ክፍል ሁሉ ያለ ኢንተርኔት አገልግሎት የዲጂታል ላይብረሪዎችን ማቋቋም፤ የትራፊክ ፍሰት የሚቆጣጠርና ሌሎች ከውጪ በውድ ዋጋ የሚገዙ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ማምረቱን ገልጿል። የዲጂታል ላይብረሪውን በተመለከተ ለምሳሌ በትግራይ ክልል በራያ የኒቨርሲቲ ድጋፍ ከ20 በላይ አካባቢዎች ሃይስኩሎች ላይ መተግበሩን እና በቡልቲም ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ደግሞ በአካባቢው ባሉ በርካታ ተቋማት ላይ መተግበሩን አስረድቷል። በአማራ ክልል በተመሳሳይ በአማራ ልማት ማኀበር አማካኝነት ከ110 በላይ ተግባሪዊ ሆኗል ያለው ድርጅቱ በአማራ ትምህርት ቢሮ አማካኝነት ደግሞ ደሴ፣ ወልዲያ፣ ሰቆጣ፣ ከሚሴ መምህራት ትምህርት ኮሌጆች ኢምፕልመንት ተደርጓል ሲል አስታውቋል። በአጠቃላይ የድጅታል ላይብረሪው ከ250 በላይ ሀይስኩሎች፣ ከ16 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ መተግበሩን ገልጿል። በተቋሙ የለሙ ቴክኖሎጂዎች በሀገር ውስጥ በመመረታቸው ከውጪ ከሚገዙበት ዋጋ 50 በመቶ ቅናሽ እንዳላቸውም ተገልጿል። በተጨማሪም የአንድ አመት ዋስትና እና በቀላሉ የጥገና አገልግሎት ማመቻቸት ይቻላል ተብሏል። ተቋሙ 10ኛ ዓመቱን አስመልክቶ ባዘጋጀው የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የማስተዋወቅ ዝግጅት እስካሁን በሪሰርች ያሉ 32 ፕሮዳክቶችን ጨምሮ በዕለቱ ለዕይታ ያቀረባቸውን 10 የሚሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን አስተዋውቋል። ተቋሙ አንዳንዶቹ ቴክኖሎጂዎች የመንግስትን አብሮነት የሚጠይቀ ናቸው ብሏል። "ለምሳሌ እንደ ትራፊክ ራዳር፣ የትራፊክ መብራቶች፣ ከተማው ላይ ያሉ የስማርት ሲቲ ቴክኖሎጂዎች ከመንግስት ጋር መስራትን የሚፈልጉ ናቸው” ነው ያለው። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethmagazine
Telegram Center
Telegram Center
Channel