ጎንደር የገባው ወራሪ ሠራዊት በየቀጠናው እየነደደ ነዉ
🔥🔥👉በሁሉም የጎንደር ቀጠናዎች ጠላትን የመቅበር ውጊያዎች ተቀጣጥለው ቀጥለዋል።
👉በዚህ መሠረት የመጀመሪያው መረጃችን ደቡባዊ ጎንደር በእስቴና በስማዳ መካከል ላይ የምትገኘው ሸንበቆች ላይ ሁለተኛ ቀኑን የያዘ ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ይገኛል። የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ እስቴ ዴንሳ ብርጌድ፣ ሃገረ ቢዘን ብርጌድ እንዲሁም የሜ/ጄ ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦሮች አማካኝነት በከፍተኛ ደረጃ ተመትቷል። ወራሪ ሠራዊቱ ከስማዳ፣ ከጠዶዬ፣ ከምክሬ ከእስቴና ከአንዳቤት ዛሬ ላይ ደግሞ ከወረታ ዋንዛዬን አቋርጦ፣ ከደብረ ታቦር እና ከክምር ድንጋይ የተንቀሳቀሰን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ኃይል አንቀሳቅሶ የነበረ ቢሆንም ያሰበው ሳይሳከ እንደቅጠል ረግፎ ሙትና ቁስለኛውን እየጎተተ ወደኋላ ፈርጥጧል።
👉ከዚህ ሌላ የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ ጥቁር አንበሳ ብርጌድ እና የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ፣ ነብዩ አሳምነው ከአዲስ ዘመን በወይንዬ አድርጎ ሚካኤል ደብር ለመግባት የተንቀሳቀሰን ወራሪ ሠራዊት ሲረፈርፉት ውለዋል። በዚህ አስደናቂ እና መብረቅ ክ/ጦር ቅንጅታዊ ኦፕሬሽንም ከአንድ ሻንበል በላይ የአገዛዙ ጦር እስከወዲያኛው ሲሸኙ ከ50 በላይ የነፍስ ወከፍ መሣሪያን፣ 30 የአገዛዙ ጦር እጅ ወደላይ ብሎ ገቢ ሆኗል።
👉ሁለተኛውና እጅግ አስደናቂው መረጃ ወደ 6ኛ ቀኑን የያዘው ከደባርቅ እስከ አምባጊዮርጊስ ያካለለውና በርካታው ወራሪ ሠራዊት እጁን የሰጠበት፣ እስከ ወዲያኛው የተሸኘበት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች እየተገኘበት ያለው ውጊያ ነው።
👉በዛሬው እለትም አጅሬ አካባቢ በአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ እና በአማራ ፋኖ በጎንደር ቅንጅታዊ ምት ፤ከሞት የተረፈው ወደ እንቃሽ ተሻግሮ፣ የአምባ ጊዮርጊሱም የሙት ቅራውቹን ለመቀበል ተስቦ መጥቶ የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ ራስ ደጀን ክ/ጦር ነበልባሎች በሚያውቁት የማጫወቻ ሜዳ ላይ ከታችም ከላይም ስበውና ሰብስበው ሲወቁት ውለዋል። በጠዋቱ በተጀመረው በዚህ ዓውደ ውጊያ በርካታ የአገዛዙ ሠራዊት እንደቅጠል ረግፏል።
👉ከዚህ በተጨማሪም በዳባቱ አቅጣጫ ኃይል ለመክፈል ከወቅንና ከዳባት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰን ኃይል የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ አያሌው ብሩ ክ/ጦር አረቡር፣ ጭላና በንከር እንደ እንደቅጠል ሲያራግፉት ውለዋል።
👉ሦስተኛው መረጃ የሻሁራውን ተጋድሎ ይመለከታል። ከትናንት ጀምሮ ከፍተኛ ትንቅንቅ እየተደረገበት ባለው በዚህ ዓውደ ውጊያም የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ አድዋ ክ/ጦር፣ ንጋት ጮራ ብርጌድ ጠላትን ከፍንጀት አፋፍ ላይ ወደ ታች ወደ ወኩ ስልታዊ ማፈግፈግ አድርገው ጎትተው ገደል ስር አስገብተው በከፍተኛ ደረጃ መትተውታል።
👉አራተኛው የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ ድል በር ብርጌድ ከማክሰኝት ወደ ጄራ ሚካኤል የተንቀሳቀሰን የአገዛዙ ወራሪ ሠራዊ መንገድ ላይ ገዥ ቦታዎችን በመያዝ 4 ቦታዎች ላይ አስደናቂ ደፈጣ በመጣል በርካታውን ሙትና ቁስለኛ አድርገው ወደ ማክሰኝት ከተማ ፈርጥጦ እንዲገባ ተደርጓል።
👉በመጨረሻም ምዕራብ ጎንደር ዞን፣ አርባ ጅርሃ ወረዳ፣ ሞገሴ ከተማ ላይ የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ አጣናው ዋሴ ክ/ጦር እና የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ፦ ጎቤ ክ/ጦር በተውጣጡ ኃይሎች በርካታ ሚሊሻና አድማ ብተና ባንዳዎች ተቀንድሸዋል።
👉በጥቅሉ ጠላት ያቀደው የኅልውና ታጋዮን እየነጠለ ከፍተኛ ቁጥር ባለው ሠራዊት ለመምታት፣ ፋኖን በትኘዋለሁ የሚል የበትኘዋለሁ ፕሮፓጋንዳ የመሥራት ፍላጎቱን ያፈረስንባቸው፣ ከፍተኛ የትጥቅ ቁሳቁሶችን የታጠቅንባቸው፣ በወራሪ ሠራዊቱ ላይ የውጊያ የበላይነትን የወሰድንባቸው፣ የሥነ ልቡና ስብራትን ያደረስንባቸው የድል የአሸናፊነት ውጊያዎች አድርገናል፤ እለታዊ እቅዳችንንም ከበቂ በላይ አሳክተናል ሲል የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ ገልጿል።
ድል ለሰፊው የአምሓራ ሕዝብ‼️🟢🟡🔴⚔⚔⚔🟢🟡🔴https://t.center/Negedeamharaphttps://t.center/Negedeamharap