View in Telegram
የጀነራሉ አጃቢዎች መክዳት የጀነራሉ አጃቢ ኮማንዶዎች ስርዓቱን ከድተው ፋኖን መቀላቀላቸው ተሰማ በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን የሚከዱና የሚጠፉ ወታደሮች ቁጥርም እየጨመረ ነው፡፡ በባህርዳር ቅርብ ርቀት ላይ ባሉ የጎጃም አካባቢዎች ትናንት ከባድ ውጊያ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን ብራቃትና አማሪት ደግሞ ይህ ውጊያ የተካሄደባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡ በአካባቢዎቹ በተካሄደው ውጊያ በፋኖ ሽንፈት ያስተናገደው የአገዛዙ ጦር በንጹሃን መኖሪያ መንደሮች ላይ ዙ 23ን ጨምሮ ከባድ መሳሪያዎችን ሲወረውር ነበር፡፡ በተመሳሳይ እነ አበባው ታደሰ ሰሞኑን ባካሄዱት ስብሰባ ሚሊሻን በሚመለከት አንድ ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡ በዚህ ውሳኔያቸውም ወጣቱን ለሚሊሻነት ማስታጠቅ አደጋ ያመጣብናል ብለዋል፡፡ ስለሆነም ወጣቱ ለእኛ ስለማይታመን ለሚሊሻነት ሲመለመል መሳሪያ ማስታጠቅ አያስፈልግም ፣ ሌላ መፍትሄ ፈልጉ መባሉ ተሰምቷል፡፡ በተጨማሪም እነ አበባው ታደሰ የመሳሪያ እጥረት እንደገጠማቸው ነው የተነገረው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በክልሉ የሚደረጉ ወታደራዊ ስምሪቶች በመከላከያ እንዲመሩና ሚሊሻና አድማ ብተና በራሳቸው ሥምሪት እንዳይሰጡ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ በሌላ በኩል ከሰሞኑ በርካታ ወታደሮች ከስምሪት ቦታቸው ጠፈተዋል ፣ ለፋኖ እጃቸውን ሰጥተዋል ፣ ተማርከዋል ፣ ወደ ፋኖ በፍቃዳቸው ተቀላቅለዋል፡፡ ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በምዕራብ ጎንደር መተማ ከ34 በላይ ወታደሮች በፋኖ ተይዘዋል፡፡ የጦር መሪያቸውን ጨምሮ 29 የሚሆኑት ደግሞ ጠፍተዋል፡፡ በበለሳ የሚሊሻ ሃላፊውን ጨምሮ ከ33 በላይ የሚሆኑት የአገዛዙ ሃይሎች በፋኖ ተይዘዋል ፣ በመንዝ ደግሞ ድሽቃ ይዘው ቁጥራቸው ያልታወቀ ኮማንዶዎች ፋኖን ተቀላቅለዋል፡፡ በፍኖተ ሰላም 8 ወታደሮች በፋኖ ሲያዙ ፣ 37 የሚሆኑት ደግሞ ጠፍተው በፈቃዳቸው ፋኖን ተቀላቅለዋል፡፡ በደብረማርቆስ ፣ ደብረኤሊያስ ፣ ጎዛመንና ቢቸና ቀጠናዎች አጠቃላይ ከ41 በላይ ወታደሮች ከስምሪት ቀጠና ጠፍተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ጎንደር ጋይንት የጀነራሉ አጃቢዎች ፋኖን መቀላቀላቸው ነው የተሰማው፡፡ የብርጋዴር ጀነራል መላኩ ገላነህ አጃቢዎች ናቸው ፋኖን የተቀላቀሉት ተብሏል፡፡ እነዚህ አጃቢዎች የሲዳማና የኦሮሞ ተወላጅ ኮማንዶዎች መሆናቸውም ነው የተነገረው፡፡ በአካባቢው ያሉ የፋኖ ሃይሎችም ቃለ መጠይቅ እንዳደረጉላቸው ነው የተነገረው፡፡ ድል ለሰፊው የአምሓራ ሕዝብ‼️ 🟢🟡🔴🟢🟡🔴 https://t.center/Negedeamharap https://t.center/Negedeamharap
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Find friends or serious relationships easily