View in Telegram
ቀኝ አዝማች ይታገሱ አዳሙ እንደ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ " በታሪክ ምስክርነት ፣በዓለም የጠበብቶች ብራና በአኩሪ ገድል የሚታወቀው የአፄ ቴዎድሮስ የእጀን አልሰጥም ዘላለማዊ ክብር በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር ዋና አዛዥ በቀኝ አዝማች ይታገሱ አዳሙ በድጋሜ በሸዋ ምድር መርሀቤቴ አውራጃ ተደገመ። ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም የአገዛዙ ነፍሰ በላ ቡድን በሸዋ ክፍለ ሀገር በመርሐቤቴ አውራጃ ከአለም ከተማ በመነሳት በአካባቢው አጠራር ወደ ገረንና በርቃቶ ቀበሌዎች በማምራት አማራ ጠል መሆኑን በግልፅ ለማሳየት ከትጥቅ ትግሉ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸውን ስድስት ግለሰቦችን በግፍ ገሏል:: 1ኛ መኳንንት ሲያሰኝ 2ኛ ጫብሰው አማረ 3ኛ ደምሰው ሽታው 4ኛ ብርሀኑ ተሰማ 5ኛ አባቴነው ማርቆስ 6ኛ የቻለሰው ንጉስ የተባሉ ንፁሀንን ከግብርና ስራቸው ማለትም ከአውድማቸው ላይ በማፈን እጃቸውን በገጀራ አይናቸውን በጩቤ አውጥቶ ፍፁም አረመኔነቱን በሚያሳይ መልኩ በግፍ ከገደለ በኋላ አስከሬናቸውን በየቦታው ጥሎት ሄዷል። ያኔ ነበር ለሌላ ስራ በአካባቢው ቅርብ ርቀት ላይ ሲንቀሳቀስ የነበረው ጀግናው መሪና ሁለት ጓደኞቹ"የአማራ ህዝብ ሆይ ካንተ በፊት ሞቴን፣ከአንተ አጠገብ ብስራቴን ያድርገው" ብሎ ለራሱና ለህዝቡ ቃል የገባው ሞት አይፈሬው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር ዋና አዛዥ ቀኝ አዝማች #ይታገሱ አዳሙ ከሌሎች ሁለት አመራሮችና አጃቢዎቻቸው ጋር በመሆን ጠላትን ፊት ለፊት የተጋፈጡት። አዎ ያማል ወገንህ አገር ሰላም ብሎ በተቀመጠበት እጁ ተቆርጦ አይኑ ወጥቶ ስታይ እንኳንስ ክላሽ ይዘህና በድንጋይም ቢሆን መጋፈጥ የጥንት ስሪታችን አማራዊ ስነልቦናችንም ነው። የወገኖቹ የግፍ ግድያ ያንገበገበው ግፍና መከራ ያንገሸገሸው ቀኝ አዝማች #ይታገስ አዳሙ ለአንድያ ነፍሱ ለሰከንድ እንኳን ሳይሳሳ የያዘውን ዘጠና የክላሽ ጥይት ጠላት ላይ አርከፍክፎ የያዘውን ሦስት ኤፍ ዋን ቦንብ አረመኔው ላይ አዝንቦ በርካቶችን እስከወዲያኛው ሸኝቶ በርካቶችን ክፉኛ አቁስሎ በስተመጨረሻም እጅህን ለጠላት አትስጥ የሚለውን የመቅደላውን ጀግና የቴዎድሮስን ተግባር ማተቡ ላይ በማሰር በቀረችው አንድ ጥይት ራሱን ሰማዕት አደረገ። ይብላን እንጂ እንመረዋለን የሚሉትን ህዝብ ጨፍጫፊ ቡድን እያሰማሩ ወገናቸውን በግፍ የሚያስገድሉ የደም ፊርማ የሚፈርሙ የክልል፣የዞንና የመርሐቤቴ ወረዳ ካድሬዎች ምድሪቷ እሾህ ፣ሰማዩ ደግሞ እሳት ሲሆንባቸው! ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል፣ላይጠናቀቅ የተጀመረ የአማራ ትግል የለም!!! ክብር ለጀግኖቻችን! ድል ለሰፊው የአምሓራ ሕዝብ‼️ 🟢🟡🔴🟢🟡🔴 https://t.center/Negedeamharap https://t.center/Negedeamharap
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Find friends or serious relationships easily