TIKVAH-ETHIOPIA

Channel
Logo of the Telegram channel TIKVAH-ETHIOPIA
@tikvahethiopiaPromote
1.52M
subscribers
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
TIKVAH-ETHIOPIA
የአቶ በቴ ኡርጌሳ ምርመራ ከምን ደረሰ ? “ ... ምርመራው ተጀምሯል ፤ እየቀጠለ ነው ” - ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል፣ መቂ ከተማ ተገደሉትን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር አቶ በቴ ኡርጌሳን ጉዳይ በተመለከተ በርካታ መረጃዎች አድርሰናችሁ ነበር።  ሰሞኑን ደግሞ ፦ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ የጀመረውን ምርመራ በደረሰበት ጫና ማቆሙን…
" በቴ ምን ያህል ለህዝቡ አስፈላጊ እንደነበር በህዝቡ ሁኔታ፣ በህዝቡ ለቅሶ ተመልክቻለሁ ! " - የፖለቲከኛ አቶ በቴ ኡርጌሳ ባለቤት

ከወራት በፊት መቂ ላይ በግፍ የተገደሉት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር ፖለቲከኛው አቶ በቴ ኡርጌሳ ባለቤት ከልጆቻቸው ጋር ከሀገር ወጥተው አሜሪካ መግባታቸው ተሰምቷል።

ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ አንበሴ በአጭር ቪድዮ ባሰራጩት ቃላቸው ፥ አሁን ላይ ከልጆቻቸው ጋር አሜሪካ ሀገር እንደሚገኙ ገልጸዋል።

" ባለቤቴ በቴ ኡርጌሳ ከሞተ 7ኛ ወር ሊሞላ ነው። " ብለዋል።

" በዓለም ላይ ያላችሁ ሃዘናችንን የተካፈላችሁ ፣ የኦሮሞ ኮሚውኒቲ ፤ በቴ ምን ያህል ለህዝቡ አስፈላጊ እንዳሆነ በሃዘናችሁ ፤ ባለው ነገር ሁሉ አይተናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" እሱ ካረፈበት ቀን ጀምሮ በሀዘናችን ያለቀሳችሁ፣ ከኛ ጋር ያዘናችሁ ፣ በገንዘባችሁ በሃሳባችሁ በጸሎታችሁ የረዳችሁን እግዚአብሔር ይስጥልን ፤ እናመሰግናለን " ብለዋል።

" የኛን ሰላም መሆን ለተጨነቃችሁ ፤ ድምጻችን ሲጠፋ ለተጨነቃችሁ ' ምን ሆናችሁ ነው ? ' ላላችሁን ያለንበትን ለመግለፅ ነው  ፤ አሁን ያለነው አሜሪካ ነው ፤ በሰላም ደርሰናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ኤምባሲዎች በጣም እናመሰግናለን ፤ ያለንበት ቦታ ድምጻችን የጠፋባችሁ ስልካችን እንቢ ያላችሁ ፣ ቤታችን ድረስ ሄዳችሁ ያጣችሁን ምን ሆናችሁ ነው ? ላለችሁን ላደረጋችሁልን ነገር ሁሉ እናመሰግናለን " ብለዋል።

" በቴ ምን ያህል ለህዝቡ አስፈላጊ እንደነበር በህዝቡ ሁኔታ፣ ለቅሶ ተመልክቻለሁ " ያሉት ወ/ሮ ስንታየሁ " እኔ እውነት ለመናገር በቴ ከሞተ በኃላ ነው ህዝቡ እንዴት በቴን ያውቅ እንደነበር የተረዳሁት ምክንያቱም በቴን እንደዚህ አላውቀውም ነበር እውነቱን ለመናገር ከጫፍ ጫፍ ነው ህዝቡ ያዘነው " ሲሉ በእምባ ታጅበው ስሜታቸውን ገልጸዋል።

እምባቸውን 😭 እያፈሰሱ የተናገሩት የበቴ ባለቤት " እሱ የኢትዮጵያ ብቻ አይደለም የዓለም ሰው እንደሆነ አውቃለሁ " ብለዋል።

አሁንም ከጎናቸው ሆነው በብዙ ነገር እየረዷቸው ላሉ በተለይ ለኦሮሞ ኮሚውኒቲ ፣ በውጭ ሆነው በስልክ እየደወሉ እያፅናኗቸው ያሉ፣ በፀሎታቸው ፣ በገንዘብ እየደገፏቸው ላሉ  ሁሉ " እግዚአብሔር ይስጥልን " ሲሉ አመስግነዋል።

ወ/ሮ ስንታየው አንበሴ ፤ ልጆቻቸው ደህንነታቸው የተጠበቀ ቦታ ላይ እንዳሉና ትምህርትም እንደጀመሩ ገልጸዋል።

ወደፊት ጊዜው ሲደርስ ደግሞ ስላሳለፉት ነገር እንደሚገልጹ ቃል ገብተዋል።

ለተደረገላቸው ነገር ሁሉ እያነቡ በልጆቻቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የ4 ልጆች አባቱ ፖለቲከኛው በቴ ኡርጌሳ ከወራት በፊት መቂ ላይ በግፍ መገደላቸው ይታወሳል። ከዛ በኃላ " ማጣራት ተደርጎ ስለ ግድያው ዝርዝር ማብራሪያ ለህዝቡ ይሰጣል " ተብሎ ቃል ቢገባም እስከ ዛሬ ስለ ግድያው ሁኔታ ፣ ከግድያው ጋር በተያያዘ ተጠያቂ ስለሆነ አካል በይፋ አንድም የተባለ ነገር የለም።

የፖለቲከኛ አቶ በቴ ኡርጌሳ ጉዳይ " ቄሱም ዝም መፅሃፉም ዝም " እንዲሉ ሆኖ ቀጥሏል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
🔈 #የወጣቶችድምጽ

" በየት በኩል እንስራ ? "

ከሰሞኑን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የኮንስትራክሽን እና ሌሎች ስራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ወጣቶች በምሬት አንድ ሃሳባቸውን አካልፈዋል።

" እንናገረውና ሰው ሰምቶት ይወጣልን ብለን ነው "  ሲሉ ስለደረሰባቸው ነገር አጋርተዋል።

እኚ ወጣቶች በክልል ከተሞች ተንቀሳቅሰው ለመስራት የሚታትሩ ናቸው።

ግን በብሄር፣ በዝምድና በትውውቅ የሚሰሩ ስራዎች ፈተና ሆነውባቸዋል። ተስፋም እያስቆረጣቸው ነው።

በቅርቡ ለአንድ ስራ ይወዳደራሉ ፤ ይህንን ስራ እንደሚያሸንፉ ባለሙሉ ተስፋ ሆነው ስራውን ለማሰራት ማስታወቂያ ወዳወጣው አካባቢና ቢሮ ያመራሉ።

ከአንድ ኃላፊ ተሰጠን ያሉት መልስ ግን " አትልፉ ፤ ይሄንን ስራ ወስዳችሁ ልትሰሩ የምትችሉ አይመስለኝም " የሚል ነው።

ይህ የሆነው ደግሞ " ከሌላ አካባቢ የመጡ ናቸው " በሚልና ከየት አካባቢ እንደመጡ በማጣራት እንደሆነ አስረድተዋል።

በዚህም " ከሌላ አካባቢ " በሚል አደገኛ አመለካከት ብቻ ስራውን ሌላ ሰው እንዲወስደው ስለመደረጉ በምሬት ተናግረዋል።

ድርጊቱ እጅግ እንዳሳዘናቸው ይሄ የብሄር፣ የዝምድና፣ የትውውቅ፣ የአካባቢ መርጦ ስራ ብዙ ወጣቶች አቅም እያላቸው እንዳይሰሩ እያደረገ ያለ እጅግ አደገኛ መርዝ መሆኑን ሳይናገሩ አላሉፍም።

ሌላ ቃላቸውን የተቀበልናቸው ወጣቶች ለስራ ጉዳይ ካለው የተንዛዛ ሂደት ባለፈ የዝምድና የትውውቅ ስራ ተስፋ አስቆርጧቸው ምን እንደሚያደርጉ ግራ እንደገባቸው ተናግረዋል።

በአንድ ሀገር በአንድ ባንዲራ ስር ከአንዱ ክልል ወደ ሌላው ሄዶ ስራ መስራት ፈተና እንደሆነና ስራዎች በዝምድና፣ ለተወላጅ፣ ለአካባቢ ሰው በትውውቅ እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።

" ሚዲያውም ሆነ ሌላው አካል እነዚህን መሰል ጉዳዮች ሳይሆን ለራሱ የገቢ ትርፍ እና ተመልካች የሚያስገኝለትን ጉዳይ እየመዘዘ ነው የሚሰራው " በማለትም ወቀሳ አቅርበዋል።

" ጨረታ፣ ውድድር በሚኖር ሰዓት እንኳን ዘመድ ያለው፣ ገንዘብ ያለው በእጅ አዙር ስራውን ያገኛል ይሄ ምንም የሚደበቅ አይደለም " ብለዋል።

ወጣቶች በፈለጉት ቦታ ተንቀሳቅሰው መስራት ካልቻሉ ሀገር ውስጥ እንዴት ይቀመጣሉ ? ቆይ በገፍ ቢሰደዱስ ምን ይገርማል ? ሲሉም ጠይቀዋል።

በዙሪያቸው ያለ እጅግ ብዙ ወጣት ባለው አሰራር ምክንያት ተማሮ ከሀገር ለመውጣት ብዙ እንደሚጥር ጠቁመዋል።

" አሁን ላይ ያለው ነገር ሁሉ ብሶበት ቁጭ ብሏል። የወጣቱን፣ የህዝቡን ድምጽ ሰምቶ ችግር ከማስተካከል ይልቅ ህዝብን ዝቅ ብለው እንዲያገለግሉ የተቀመጡ አካላት ሌላ ስም መስጠት እና መፈረጅ ስራቸው ሆኗል " ሲሉ አክለዋል።

ከአንድ ክልል፣  ዞን ፣ ወረዳ ሌላ ቦታ ሄዶ ለመስራት ችግር ከሆነና ስራው ሁሉ ብቃት ላለው ሳይሆን በብሄር፣ ትውውቅ፣ ዝምድና፣ በሙስና እየተመረጠ የሚሰጥ ከሆነ እንዴት ለውጥ ሊመጣ ይችላል ? ወደኃላ መጓዝ ማለትስ ይህ አይደለም ? ይህ የበርካታ ወጣቶች ጥያቄና ድምጽ ነው።

#TikvahEthiopia
#የወጣቶችድምጽ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወጣ ወጣት በተአምር ህይወቱ ተርፏል።

በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የወጣ ወጣት ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታውቋል፡፡

በዘርፉ የደቡብ ሁለት ሪጅን እንደገለፀው ወጣቱ ዛሬ  ከቀኑ  8:00  ጀምሮ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሳውላ በሚሄደው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወጥቶ " አልወርድም " በማለቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ፦
- ጎፋ ዞን፣
- አሪ ዞን፣
- ባስኬቶ ዞን እና ኦሞ ዞን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ጋሞ ዞን በከፊል ከሦስት ሰዓታት በላይ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

በምን ምክንያት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ እንደወጣ ያልታወቀው ወጣት በአካባቢው ሽማግሌዎችና የመስተዳድር አካላት ቢለመንም ለመውረድ ግን አስቸግሮ እንደነበር መምሪያው ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች ኃይል በማቋረጥ ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል፡፡

የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የሚያስተላልፉት የቮልቴጅ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መምሪያው አሳስቧል፡፡

#EthiopianElectricPower

@tikvahethiopia
ሕብር ሞባይል ባንኪንግ- አሁን የበለጠ ዘምኗል! - ቀሏል!


ውድ ደንበኞቻችን! ባንካችን የሕብር ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ላይ አዳዲስ አገልግሎቶችን ከጥብቅ የደህንነት ማሻሻያዎች ጋር ይዞላችሁ  ቀርቧል፡፡  እጅግ ዘምኖ የቀረበውን ሕብር የሞባይል መተግበሪያ ሲጠቀሙ  ፡-
•  በቀላሉ ከውጭ ሀገር የአገልግሎት ወይም የንግድ ክፍያን መቀበል
•  ስካን በማድረግ ክፍያ መፈፀም
•  ክፍያ ለመቀበል የራስ QR ኮድ መፍጠር እና ለሌሎች ማጋራት
•  የሞባይል ጥቅል አገልግሎት በቀላሉ መግዛት
•  አንድን ሂሳብ በቋሚነት መምረጥ እና መጠቀም
•  ተጨማሪ ስልክ/ኢሜይል መጠቀም one time password እንዲደርሶ ማድረግ ይችላሉ፡፡

የተሻሻለውን መተግበሪያ ከጉግል ፕሌይ ወይም አፕ ስቶር ያውርዱ! ይጠቀሙ!

https://www.hibretbank.com.et/hibir-mobile-landing-page

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞  ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች  እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ https://t.center/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡

#Hibirmobile #appupdate #Hibretbank
#InfinixEthiopia

የኢንፊኒክስ ስማርት ስልኮች የሆኑትን ሆት 40 ፣ ኖት 40 ፣ ዜሮ 40 እና የኢንፊኒክስ ስማርት TVን ሲገበያዩ የሽልማት ኩፖን ይውሰዱ፡፡ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር በመረጡት ስፍራ ፎቶ በመነሳት #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ በመጠቀም የማህበራዊ ገጾት ላይ ይለጥፉ የዛንዚባር የቢዝነስ ክላስ ደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት ፣ የኢንፊኒክስ ስማርት ቲቪ ፣ የኢንፊኒክስ ላፕቶፕ እንዲሁም ሌሎች አጓጊ ሽልማቶችን ያሸንፉ፡፡

መመሪያ

1. የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡
3. #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ መጠቀሞን አይርሱ፡፡

Tag ሲያደርጉ ለ Facebook @InfinixMobileEthiopia ፣ ለ Instagram @infinixethiopia ለ TikTok @Infinixet እና ለ Telegram @Infinixeth ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሳህለወርቅ_ዘውዴ

“ አቅጣጫዬን አሳይቻለሁ፤ በዛ መሠረት ለመስራት ሞክሬአለሁ ” - የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

በበጎ ፈቃድ የተሰባሰቡ ሴቶችና የሴት መሪ ድርጅቶች በጋራ በመሆን በቅርቡ የሥራ ዘመናቸውን ላጠናቀቁት ለቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሸራተን አዲስ ሆቴል ዛሬ የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጅተው ነበር።

በዚሁ መርሀ ግብር አቶ አባዱላ ገመዳ፣ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ፣ የሴቶች ማኀበራት መሪዎችና በሌሎች የሥራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ ሴቶች ተገኝተዋል።

ፕሮግራሙ ከተዘጋጀበት ዓላማ አኳያም ለቀድሞ ፕሬዜዳንቷ “ በጣም ውድ ” እና “ ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ ” የተባለለት የሀገር ቅርስ ጭምር የተቀረጸበት የስዕል ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን፣ “ ከሚገባው ቦታ አስቀምጠዋለሁ ” በማለት ስጦታውን ላበረከቱላቸው ምስጋና አቅርበዋል።

በመርሀ ግብሩ ባደረጉት ንግግር ደግሞ፣ “ የዛሬ 6 ዓመት ገደማ ያደረኩት ንግግር የ18 ደቂቃ ነበር። ጥቂት ጊዜ ነው የነበረኝ ለመዘጋጀት። የደረሰብኝም አልገባኝም ነበር ” ሲሉ አስተውሰዋል የቀድሞ ፕሬዜዳንቷ።

“ ሴቶች የሚለውን ቃል 29 ጊዜ፣ ሰላም የሚውን ቃል 30 ጊዜ ተናግሬ ነበር ” ያሉት ሳህለወርቅ፣ “ ለራሴ አልዋሽም፣ ለሌላም አልዋሽም። አቅጣጫዬን አሳይቻለሁ፣ በዛ መሠረት ለመስራት ሞክሬአለሁ ” ሲሉም አክለዋል።

“ ተያይዘን መስራት አለብን። ጡረታ የሚባለውን ነገር አሁን ነው የጀመርኩት ግን እረፍት የለም። ጡረታም ተወጥቶ እንደማይታረፍ የቀደሙኝ እያሳዩኝ ነው። ላደረጋችሁልኝ በጣም ነው የማመሰግነው ” ነው ያሉት።

የቀድሞዋ ፕሬዜዳንት ከዚህ ቀደም፣ “ ‘የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው፣ መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው’ ይላል ማህሙድ ‘ዝምታ ነው መልሴ’ን ሲያዜም ” ብለው፣ “ አንድ ዓመት ሞከርኩ ” የሚል ፅሑፍ በX (ቲዊተር) ገጻቸው አጋርተው ነበር።

በወቅቱም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ይህንን ምስጢር አዘል የሆነ ፅሑፋቸውን በተመለከተ ግን ዛሬም የሰጡት ማብራሪያ የለም።

የቀድሞዋ ፕሬዜዳንት ሳልለወርቅ ዘውዴ የመጀመሪያዋ ሴት የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሆነው ለ6 ዓመታት 4ኛ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተው፣ የሥልጣን ዘመናቸው በመጠናቀቁ ኃላፊነታቸውን ለፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ማስረከባቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Telegram Center
Telegram Center
Channel