#Ethiopia 🇪🇹 የ 2017 የሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል።
ለሀያ አራተኛ ጊዜ በሚካሄደው በዘንድሮው ውድድር 50,000 ተሳታፊዎች እንደሚካፈሉ ይጠበቃል።
በእሁዱ ውድድር የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአለምአቀፍ 10 ኪሎ ሜትር የሶስት ጊዜ አሸናፈው አቤ ጋሻሁን ወደ ውድድር እንደሚመለስ ተገልጿል።
የአምናው የውድድሩ አሸናፊ ቢኒያም መሃሪም በውድድሩ የሚካፈል ሲሆን ባለፈው አመት የውድድሩን ክብረ ወሰን ለመስበር በአንድ ሰከንድ ዘግይቶ ጠንካራ ፉክክር አድርጎ ነበር።
በሴቶች ውድድር እጅግ ከባድ ፉክክር የሚጠበቅ ሲሆን መታየት ካለባቸው አትሌቶች መካከል በመስከረም ወር በአምስተርዳም ዳም ቱ ዳም የ 10 ማይል አሸናፊ የሆነችው አሳየች አይቸው ትገኝበታለች፡፡
የዚህ ዓመት ውድድር ለሽልማት የሚቀርበው ሚዳሊያ በኢትዮጵያ ከተገኘች 50 ዓመት የሞላትን ድንቅነሽን (ሉሲ) የሚያስታውስ ቅርፅ እንደሚኖረው ተገልጿል።
የአዋቂ አትሌቶች ውድድር ከሌሎች ተሳታፊዎች ውድድር በአምስት ደቂቃዎች ቀድሞ እንደሚጀምር አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe