የአቶ በቴ ኡርጌሳ ምርመራ ከምን ደረሰ ?
“ ... ምርመራው ተጀምሯል ፤ እየቀጠለ ነው ” - ኢሰመኮ
በኦሮሚያ ክልል፣ መቂ ከተማ ተገደሉትን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር አቶ በቴ ኡርጌሳን ጉዳይ በተመለከተ በርካታ መረጃዎች አድርሰናችሁ ነበር።
ሰሞኑን ደግሞ ፦
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ የጀመረውን ምርመራ በደረሰበት ጫና ማቆሙን ኮሚሽኑ ወደ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከላከው ደብዳቤ ላይ መመልከቱን " አዲስ ስታንዳርድ " ድረገጽ ዘግቧል።
“ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተሳትፎ መኖሩን የሚያመለክት ምስክሮችን ማሰባሰብ ከጀመረ ከ3 ቀናት በኋላ የምርመራው ቡድን ‘ ምርመራውን እንዲያቆርጥ መገደዱን ’ ” በደብዳቤ መግለጹ ነው የተዘገበው።
“ በዕለቱ ሌሊት ላይ 6 ሰዓት አከባቢ ከከተማዋ ወጣ ብሎ የበቴ አስከሬን በተገኘበት መንገድ ላይ አንድ ባለሁለት ጋቢና ፒክአፕ በፍጥነት በመጓዝ ከዋናው መንገድ ወጣ ብሎ መብራት ሳያጠፋ መቆሙን ” በደብዳቤው መገለጹም ተመላክቷል።
ደብዳቤው ፥ “ ቀይ መለዮ ኮፊያ እና ዥጉርጉር ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱ እና መሳሪያ የታጠቁ አራት (4) ሰዎች ከመኪናዋ በመውረድ ከመኪናዋ ኋላ አንድ (1) ሰው ጎትተው በማውረድ በተደጋጋሚ በመተኮስ ጥለውት ሂደዋል ” ማለቱንም ዘገባው አትቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ፤ በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ የሚደረገው ምርመራ እውነት ቆሟል ወይስ እንደቀጠለ ነው ? ሲል ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥያቄ አቅርቧል።
የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ በሰጡት ቃል፣ “ ምርመራው ተጀምሯል ፤ እየቀጠለ ነው ” ብለዋል።
የምርመራው ሂደት ምን ይመስላል ? በተጨባጭ የተገኙ ጉዳዮች አሉ ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ ምርመራው Ongoing ስለሆነ አስተያየት ለመስጠት ትንሽ ያስቸግራል ” ከማለት ውጪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
“ Ongoing investigation ነው። የተወሰኑ #ቻሌንጆች_አሉ። ግን እየተነጋገርን ነው ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር ” ነው ያሉት።
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አቶ በቴ በተገደሉበት ወቅት ግድያው ' ባልታወቁ ሰዎች መፈጸሙን ' ገልጾ መርምሬ ለህዝብ ውጤቱን ይፋ አደርጋለሁ ማለቱ ይታወሳል። ይህን ካለ ሳምንታት ቢያልፉም እስካሁን ለህዝብ የተሰጠ ግልጽ የሆነ መረጃ / ማብራሪያ የለም።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia