TIKVAH-SPORT

Channel
Logo of the Telegram channel TIKVAH-SPORT
@tikvahethsportPromote
248.44K
subscribers
“ ዩናይትድ የፕርሚየር ሊጉ ዋናው ሞተር ነው “ ሩበን አሞሪም

አዲሱ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድኑን በሀላፊነት ከተረከቡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከክለቡ ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኙ በመጀመሪያ ንግግራቸውም “ በእኔ አሰተያየት ማንችስተር ዩናይትድ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋናው ሞተር ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።

“ አንድ የተለየ ሀሳብ እንደምትመለከቱ አረጋግጣለሁ “ ያሉት አሰልጣኙ “ ማንችስተር ዩናይትድ የሚገባው ቦታ ላይ እንዲቀመጥ ያለኝን ሁሉ እሰጣለሁ “ ብለዋል።

" ጊዜ እንደሚያስፈልገን እናውቃለን ነገርግን ማሸነፍ አለብን ጨዋታዎችን አሸነፍን ማለት ጊዜ አገኘን ማለት ነው።“ ሩበን አሞሪም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፖል ፖግባ ከጁቬንቱስ ጋር ሊለያይ ነው ! ፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፖል ፖግባ ከጣልያን ሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ጋር ያለውን ኮንትራት ሊያቋርጥ መሆኑ ተገልጿል። ፖል ፖግባ አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቅሟል በሚል ከእግርኳስ ለአራት አመታት ታግዶ የቆየ ሲሆን አሁን ላይ በይግባኝ ወደ 18 ወራት ተቀንሶለታል። ፖግባ በቀጣይ ከጁቬንቱስ ጋር ያለውን ኮንትራት በማቋረጥ በነፃ ዝውውር የፈለገውን…
ፖል ፖግባ በይፋ ከጁቬንቱስ ጋር ተለያየ !

ፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፖል ፖግባ ከጣልያን ሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ጋር ያለውን ኮንትራት ማቋረጡ በይፋ ተገልጿል።

አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቅሟል በሚል ከእግርኳስ ለአራት አመታት ታግዶ የነበረው ፖግባ እገዳው ወደ 18 ወራት ተቀንሶለት ወደ እግርኳስ መመለሱ ይታወሳል።

ፖግባ አሁን ላይ ከጁቬንቱስ ጋር ያለውን ኮንትራት ማቋረጡን ተከትሎ በነፃ ዝውውር የፈለገውን ክለብ መቀላቀል የሚችል ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ክርስቲያኖ ሮናልዶ አዲስ ታሪክ ይፅፍ ይሆን ?

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት 4:45 የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ መርሐ ግብሩን ከፖላንድ አቻው ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

በምሽቱ ጨዋታ ፖርቹጋል ባለድል መሆን ከቻለች የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ አዲስ ታሪክ የሚፅፍ ይሆናል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዛሬ ፖርቹጋል የምታሸንፍ ከሆነ በብሔራዊ ቡድኑ ያሳካው 1️⃣3️⃣2️⃣ኛ ድሉ ሆኖ ይመዘገብለታል።

ይሄም ሮናልዶ ከየትኛውም ተጨዋች በመብለጥ ከሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ጋር ብዙ ድሎችን ያሳካ ቀዳሚው ተጨዋች ያደርገዋል።

@Tikvahethsport             @kidusyoftahe
" ሁልጊዜም ከማድሪድ ጎን እቆማለሁ " ቶኒ ክሩስ

የቀድሞ የሎስ ብላንኮዎቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ ወደፊት ክለቡን በአዲስ ሚና ሊያገለግል እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል።

" ሁልጊዜም ከማድሪድ ጎን እቆማለሁ " ያለው ቶኒ ክሩስ " ሪያል ማድሪድ ለኔ ትልቅ ትርጉም አለው እስከመጨረሻው ከክለቡ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ይኖረኛል።" ብሏል።

ክሩስ በቀጣይ በሌላ ሀላፊነት ወደ ክለቡ ሊመለስ እንደሚችል ለተነሳለት ጥያቄ "ስለወደፊቱ ምንም ማለት አልችልም ሆኖም እድሎች ካሉ ወደ ምወደው ክለብ ከመመለስ ወደኋላ አልልም።" ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የአለም ክለቦች ውድድር ዋንጫ ምን ይመስላል ?

ፊፋ በቀጣይ በአዲስ መልክ የሚጀምረውን የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ያዘጋጀውን በወርቅ የተለበጠ የዋንጫ ሽልማት ትላንት አስተዋውቋል።

በዋንጫው ላይ የ 54ዓመቱ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋቲኖ ስም ሁለት ጊዜ ተቀርጾ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በተጨማሪም ትልቅ የእግርኳስ ታሪኮች እና የሁሉም 2️⃣1️⃣1️⃣ የፊፋ አባል ሀገራት ስም በዋንጫው ላይ ተቀርፆ እንደሚገኝ ተነግሯል።

የ 2025 የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር በሚቀጥለው ክረምት በአሜሪካ በ 3️⃣2️⃣ ክለቦች መካከል እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

በውድድሩ ከእንግሊዝ ክለቦች ማንችስተር ሲቲ እና ቼልሲ የሚሳተፉ ይሆናል።

የሊዮኔል ሜሲው ቡድን ኢንተር ሚያሚ እንዲሁ ከውድድሩ አዘጋጅ አሜሪካ የበውድድሩ የሚሳተፍ ክለብ ነው።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ባሎን ዶር ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ ፓልመር

የሰማያዊዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ኮል ፓልመር በቀጣይ ቼልሲ ውስጥ ባሎን ዶር ማሸነፍ እንደሚፈልግ ገልጿል።

በቼልሲ ማሳካት ስለሚፈልገው ነገር የተጠየቀው ፓልመር “ ከቼልሲ ጋር ዋንጫዎችን እና ባሎን ዶር ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ በማለት ተናግሯል።

የዋይን ሩኒን ግብ የማስቆጠር ክህሎት ሲመለከት ማደጉን የሚገልጸው ፓልመር “ እሱ በየጨዋታው ግብ ሲያስቆጥር እኔም እንደምችል ለማየት ወጥቼ እሞክር ነበር።“ ብሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ክላውዲያ ራኔሪ ወደ እግርኳስ እንዴት ተመለሱ ?

በይፋ ራሳቸውን ከእግርኳስ አግልለው የነበሩት ጣልያናዊው አሰልጣኝ ክላውዲያ ራኔሪ በድጋሜ በመመለስ ሮማን መረከባቸው ይታወቃል።

አሰልጣኙ ራሳቸውን ከእግርኳስ ሲያገሉ ሮማ ወይም ካግሊያሪ ጥያቄ ካቀረቡላቸው ወደ እግርኳስ ለመመለስ አስበው እንደነበር ገልጸዋል።

ክላውዲዮ ራኔሪ ሲናገሩም “ ሌስተርን ይዤ ዋንጫ ካሸነፍኩበት ጊዜ በበለጠ ከእግርኳስ ከተገለልኩ በኋላ በርካታ ጥያቄዎች ቀርበውልኝ አልተቀበልኩም ነበር “ ብለዋል።

" ሮማ ወይም ካግሊያሪ “ ካልሆኑ አልቀበልም ማለታቸውን ያስረዱት አሰልጣኙ አሁን ላይ ሮማ ደርሻለሁ በማለት ተናግረዋል።

የ 73ዓመቱ አንጋፋ አሰልጣኝ የሆኑት ክላውዲዮ ራኔሪ በ እግር ኳስ ከ 51ዓመታት በላይ መስራት ችለዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ኢንተር ሚላን የተጫዋቹን ውል አራዝሟል !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኢንተር ሚላን የጀርመናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ያን ቢሴክ ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 23ዓመቱ ተከላካይ ያን ቢሴክ በኢንተር ሚላን ቤት እስከ 2029 የሚያቆየውን የተጨማሪ አንድ አመት ውል መፈረሙ ተገልጿል።

ተጨዋቹ የነበረው ውል 2028 የሚጠናቀቅ የነበረ ሲሆን በአዲሱ የአስራ ሁለት ወራት ኮንትራት የክፍያ ጭማሬ ማግኘቱ ተነግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
በአሸናፊነቷ የቀጠለችው ጃፓን !

የጃፓን ብሔራዊ ቡድን ከኢንዶኔዥያ ጋር ያደረገውን የእስያ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ጃፓን ከሶስተኛው ዙር አምስት ማጣሪያ ጨዋታዎች አራቱን በአሸናፊነት ስተወጣ በአንዱ አቻ ተለያይታለች።

ብሔራዊ ቡድኑ ባደረጋቸው አምስት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች አስራ ዘጠኝ ግቦችን ሲያስቆጥር የተቆጠረበት አንድ ግብ ነው።

ቡድኑ በአማካይ በጨዋታ 3.8 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ጃፓን ምድቡን በአስራ ሶስት ነጥብ ስትመራ ከሶስተኛ ደረጃው ያላት ነጥብ ወደ ሰባት መስፋቱን ተከትሎ የምድቡ መሪ ሆና ለአለም ዋንጫው ለማለፍ ተቃርባለች።

ጃፓን በ 2024 ካደረገቻቸው አስራ ስድስት ጨዋታዎች መካከል በአስሩ ከሶስት በላይ ግቦችን አስቆጥራ ማሸነፍ ችላለች።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
#Wanaw_sportswear
🎉 Congrats to our partners, the Liberia National Team, on your well-deserved victory! Keep your eyes on the target, and let success be your reward. 🏆⚽️

Contact us!
📞 8289


Follow Us
Website|Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube|Telegram

🌍Made In Africa 🌍
🏅 ዋናው ወደፊት...
ውጤቱን ይገምቱ

ሀገራችን ኢትዮጵያን ወክለው የዓምናው የሴቶች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ የሆኑት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን ነገ ከምሽቱ 02፡00 ሰዓት ከሞሮኮዎቹ ኤፍ ሲ ማስር ጋር ይጋጠማሉ!

ይህንን ደማቅ ፍልሚያ በቀጥታ በSS Liyu 2 በጎጆ ፓኬጅ

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

የዲኤስቲቪ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3yBcOHc

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
🔊 🌟የሳፋሪኮም #1ወደፊት  የሙዚቃ ስልጠናችን እንደቀጠለ ነው!

ምርጥ 10 ኮከቦቻችን በ#1Wedefit የሙዚቃ ስልጠና ልምድ እያገኙ ነው! ሙሉ ቆይታቸውን በቅርቡ...📽️

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
ብዙ ጉዳት ያጋጠማቸው ክለቦች የትኞቹ ናቸው ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሊጉ ተጨዋቾቹን በጉዳት ብዙ ጊዜ ለማጣት የተገደደ ቀዳሚው ክለብ መሆኑ ተገልጿል።

ቶተንሀም በውድድር ዘመኑ ተጨዋቾቹን አስራ ሶስት ጊዜ በጉዳት ምክንያት በፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማጣቱ ተነግሯል።

ብዙ ጉዳት ያጋጠማቸው ክለቦች የትኞቹ ናቸው ?

  ቶተንሀም :- 13 ጉዳቶች

ብራይተን :- 12 ጉዳቶች

ኢፕስዊች ታውን :- 12 ጉዳቶች

አስቶን ቪላ :- 11 ጉዳቶች

ክሪስታል ፓላስ :- 11 ጉዳቶች

አርሰናል :- 10 ጉዳቶች

ማንችስተር ሲቲ :- 10 ጉዳቶች

ዌስትሀም ዩናይትድ በውድድር ዘመኑ በሁለት ጉዳቶች አነስተኛ ጉዳት ያጋጠመው ክለብ መሆኑ ተጠቁሟል።

@Tikvahethsport           @kidusyoftahe
" በጥሩ ሁኔታ ላይ አንገኝም " ኮቫቺች

የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማትዮ ኮቫቺች ቡድናቸው በዚህ ሰአት በጥሩ ሁኔታ ላይ #እንደማይገኝ በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

" በጥሩ ሁኔታ ላይ አንገኝም " ሲል የተደመጠው ኮቫቺች ሆኖም ከምንገኝበት የውጤት ቀውስ የመውጣቱ ሀላፊነት የሁላችንም ነው። " ሲል ቡድኑን አሳስቧል።

አሁን የምንገኝበት የእረፍት ጊዜ ለቡድናችን ጥሩ ይሆናል ሲል የገለፀው ተጨዋቹ "ይበልጥ ጠንካራ ሆነን እንድንመለስ ይረዳናል።" ብሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
" ዩናይትድን በመልቀቄ አልፀፀትም " ማክ ቶሚናዬ

ናፖሊን የተቀላቀለው ስኮትላንዳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ስኮት ማክ ቶሚናይ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በመለያየቱ እንደማይፀፀት ተናግሯል።

ተጨዋቹ ማንችስተር ዩናይትድን በመልቀቁ ይፀፀት እንደሆነ ሲጠየቅ " በእግር ኳስ ህይወቴ የምፀፀትበት ነገር የለም።" በማለት ምላሹን ሰጥቷል።

ስኮት ማክ ቶሚናይ አክሎም " አንዳንዴ ትልልቅ ውሳኔዎች ማሳለፍ ይኖርብሀል ቀጥሎም ወደ ኋላ መመልከት አያስፈልግም።" ሲል ተደምጧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ለድጋፋችሁ አመሰግናለሁ " ቫን ኔስትሮይ

ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የተለያየው አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ ባስተላለፈው የስንብት መልዕክት ለተደረገለት ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቧል።

“ በዩናይትድ ውስጥ ላሉ ሁሉ ላደረጋችሁልኝ ድጋፍ እና አብሮነት ከልብ አመሰግናለሁ " ሲል ቫን ኔስትሮይ በመልዕክቱ ገልጿል።

“ ማንችስተር ዩናይትድን መምራት ክብር ነበር አብረን የነበረንን ጊዜ ስደሰትበት እኖራለሁ “ ያለው ቫን ኔስትሮይ “ ማንችስተር ዩናይትድ ሁልጊዜም በልቤ ውስጥ የተለየ ቦታ ይኖረዋል “ ብሏል።

አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ ማንችስተር ዩናይትድን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ለአራት ጨዋታዎች ሲመራ በሶስቱ አሸንፎ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ኒውካስል ተጨዋቹ ቤቱ መዘረፉን ገለፀ !

ብራዚላዊው የኒውካስል ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጆኢሊንተን መኖሪያ ቤቱ በዘራፊዎች መዘረፉን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ገልጿል።

ተጨዋቹ መኖሪያ ቤቱ ሲዘረፍ ከአመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ተነግሯል።

ተጨዋቹ በማህበራዊ ገፁ ባሰፈረው መልዕክትም “ በድጋሜ ለማድረግ ላሰባቸሁ ምንም ሳይዘረፍ የቀረ ነገር እንደሌለ እወቁ ” ብሏል።

ተጨዋቹ አክሎም ቤተሰቦቻችን ያለፍርሀት በሰላም እንዲኖሩ እንፈልጋለን መብታችን እንዲከበር እንጠይቃለን በሰላም መኖር እንፈልጋለን በማለት ተናግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

የ 2017 የሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል።

ለሀያ አራተኛ ጊዜ በሚካሄደው በዘንድሮው ውድድር 50,000 ተሳታፊዎች እንደሚካፈሉ ይጠበቃል።

በእሁዱ ውድድር የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአለምአቀፍ 10 ኪሎ ሜትር የሶስት ጊዜ አሸናፈው አቤ ጋሻሁን ወደ ውድድር እንደሚመለስ ተገልጿል።

የአምናው የውድድሩ አሸናፊ ቢኒያም መሃሪም በውድድሩ የሚካፈል ሲሆን ባለፈው አመት የውድድሩን ክብረ ወሰን ለመስበር በአንድ ሰከንድ ዘግይቶ ጠንካራ ፉክክር አድርጎ ነበር።

በሴቶች ውድድር እጅግ ከባድ ፉክክር የሚጠበቅ ሲሆን መታየት ካለባቸው አትሌቶች መካከል በመስከረም ወር በአምስተርዳም ዳም ቱ ዳም የ 10 ማይል አሸናፊ የሆነችው አሳየች አይቸው ትገኝበታለች፡፡

የዚህ ዓመት ውድድር ለሽልማት የሚቀርበው ሚዳሊያ በኢትዮጵያ ከተገኘች 50 ዓመት የሞላትን ድንቅነሽን (ሉሲ) የሚያስታውስ ቅርፅ እንደሚኖረው ተገልጿል።

የአዋቂ አትሌቶች ውድድር ከሌሎች ተሳታፊዎች ውድድር በአምስት ደቂቃዎች ቀድሞ እንደሚጀምር አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የቀድሞ የአርሰናል ተጨዋች ጫማውን ሰቀለ !

የቀድሞ የአርሰናል እና የደቡብ ኮርያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ፓርክ ቹ ያንግ በ 39ዓመቱ ጫማውን እንደሰቀለ ይፋ አድርጓል።

ፓርክ ቹ ያንግ በአርሰናል መለያ መጫወት የቻለ ብቸኛው ደቡብ ኮርያዊ እግርኳስ ተጨዋች መሆኑ ተነግሯል።

ተጨዋቹ በአርሰናል ቤት ባሳለፈባቸው አራት አመታት ብዙም የመሰለፍ እድል ያላገኘ ሲሆን ስድስት ጨዋታዎች እና አንድ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
" ጥሩ ተጨዋቾች እና ጥሩ ቡድን አለን " ጋብሬል ማርቲኔሊ

ብራዚላዊው የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ጋብሬል ማርቲኔሊ ቡድናቸው አመቱን በስኬት ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

" በድንቅ ተጨዋቾች የተሟላ ጥሩ ቡድን አለን " የሚለው ተጨዋቹ " ያለፉትን አመታት በሊጉ ሁለተኛ ሆነ አጠናቀናል ዘንድሮ ዋንጫውን ለማሸነፍ ዝግጁ ነን።" ብሏል።

የውድድር አመቱ "ረጅም ነው" ሲል የገለፀው ማርቲኔሊ "በራሳችን እምነት አለን የምንፈልገውን ነገር ለማሳካት ቁርጠኛ ነንደ" በማለት ተናግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
Telegram Center
Telegram Center
Channel