View in Telegram
የአለም ክለቦች ውድድር ዋንጫ ምን ይመስላል ? ፊፋ በቀጣይ በአዲስ መልክ የሚጀምረውን የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ያዘጋጀውን በወርቅ የተለበጠ የዋንጫ ሽልማት ትላንት አስተዋውቋል። በዋንጫው ላይ የ 54ዓመቱ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋቲኖ ስም ሁለት ጊዜ ተቀርጾ እንደሚገኝ ተገልጿል። በተጨማሪም ትልቅ የእግርኳስ ታሪኮች እና የሁሉም 2️⃣1️⃣1️⃣ የፊፋ አባል ሀገራት ስም በዋንጫው ላይ ተቀርፆ እንደሚገኝ ተነግሯል። የ 2025 የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር በሚቀጥለው ክረምት በአሜሪካ በ 3️⃣2️⃣ ክለቦች መካከል እንደሚካሄድ ይጠበቃል። በውድድሩ ከእንግሊዝ ክለቦች ማንችስተር ሲቲ እና ቼልሲ የሚሳተፉ ይሆናል። የሊዮኔል ሜሲው ቡድን ኢንተር ሚያሚ እንዲሁ ከውድድሩ አዘጋጅ አሜሪካ የበውድድሩ የሚሳተፍ ክለብ ነው። @Tikvahethsport    @kidusyoftahe
Telegram Center
Telegram Center
Channel