View in Telegram
ኒውካስል ተጨዋቹ ቤቱ መዘረፉን ገለፀ ! ብራዚላዊው የኒውካስል ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጆኢሊንተን መኖሪያ ቤቱ በዘራፊዎች መዘረፉን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ገልጿል። ተጨዋቹ መኖሪያ ቤቱ ሲዘረፍ ከአመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ተነግሯል። ተጨዋቹ በማህበራዊ ገፁ ባሰፈረው መልዕክትም “ በድጋሜ ለማድረግ ላሰባቸሁ ምንም ሳይዘረፍ የቀረ ነገር እንደሌለ እወቁ ” ብሏል። ተጨዋቹ አክሎም ቤተሰቦቻችን ያለፍርሀት በሰላም እንዲኖሩ እንፈልጋለን መብታችን እንዲከበር እንጠይቃለን በሰላም መኖር እንፈልጋለን በማለት ተናግሯል። @Tikvahethsport    @kidusyoftahe
Telegram Center
Telegram Center
Channel