Смотреть в Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... የቤተሰብ ዋነኛ ፍላጎት ፍትህን ማግኘትና እውነቱን ማወቅ ነው " - የአቶ በቴ ኡርጌሳ ቤተሰብ የአቶ በቴ ኡርጌሳ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፅሟል። ስርዓተ ቀብራቸው ቤተሰቦቻቸው ፣ ዘመዶቻቸው በርካታ ሰዎች ፣ ወዳጆቻቸው በተገኙበት ዛሬ በመቂ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው የተፈፀመው። አንድ ቀላቸውን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ የሰጡ የቤተሰብ አባል ፤ " ያው እንደ በቴ ከዚህ በላይ ብጠበቅም ብዙ…
የአቶ በቴ ኡርጌሳ ምርመራ ከምን ደረሰ ? “ ... ምርመራው ተጀምሯል ፤ እየቀጠለ ነው ” - ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል፣ መቂ ከተማ ተገደሉትን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር አቶ በቴ ኡርጌሳን ጉዳይ በተመለከተ በርካታ መረጃዎች አድርሰናችሁ ነበር።  ሰሞኑን ደግሞ ፦ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ የጀመረውን ምርመራ በደረሰበት ጫና ማቆሙን ኮሚሽኑ ወደ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከላከው ደብዳቤ ላይ መመልከቱን " አዲስ ስታንዳርድ " ድረገጽ ዘግቧል። “ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተሳትፎ መኖሩን የሚያመለክት ምስክሮችን ማሰባሰብ ከጀመረ ከ3 ቀናት በኋላ የምርመራው ቡድን ‘ ምርመራውን እንዲያቆርጥ መገደዱን ’ ” በደብዳቤ መግለጹ ነው የተዘገበው። “ በዕለቱ ሌሊት ላይ 6 ሰዓት አከባቢ ከከተማዋ ወጣ ብሎ የበቴ አስከሬን በተገኘበት መንገድ ላይ አንድ ባለሁለት ጋቢና ፒክአፕ በፍጥነት በመጓዝ ከዋናው መንገድ ወጣ ብሎ መብራት ሳያጠፋ መቆሙን ” በደብዳቤው መገለጹም ተመላክቷል።  ደብዳቤው ፥ “ ቀይ መለዮ ኮፊያ እና ዥጉርጉር ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱ እና መሳሪያ የታጠቁ አራት (4) ሰዎች ከመኪናዋ በመውረድ ከመኪናዋ ኋላ አንድ (1) ሰው ጎትተው በማውረድ በተደጋጋሚ በመተኮስ ጥለውት ሂደዋል ” ማለቱንም ዘገባው አትቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ፤ በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ የሚደረገው ምርመራ እውነት ቆሟል ወይስ እንደቀጠለ ነው ? ሲል ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥያቄ አቅርቧል። የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ በሰጡት ቃል፣ “ ምርመራው ተጀምሯል ፤ እየቀጠለ ነው ” ብለዋል። የምርመራው ሂደት ምን ይመስላል ? በተጨባጭ የተገኙ ጉዳዮች አሉ ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ ምርመራው Ongoing ስለሆነ አስተያየት ለመስጠት ትንሽ ያስቸግራል ” ከማለት ውጪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል። “ Ongoing investigation ነው። የተወሰኑ #ቻሌንጆች_አሉ። ግን እየተነጋገርን ነው ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር ” ነው ያሉት። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አቶ በቴ በተገደሉበት ወቅት ግድያው ' ባልታወቁ ሰዎች መፈጸሙን ' ገልጾ መርምሬ ለህዝብ ውጤቱን ይፋ አደርጋለሁ ማለቱ ይታወሳል። ይህን ካለ ሳምንታት ቢያልፉም እስካሁን ለህዝብ የተሰጠ ግልጽ የሆነ መረጃ / ማብራሪያ የለም። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Telegram Center
Telegram Center
Канал