Смотреть в Telegram
፩ አማራ ሚዲያ
ሰበር የድል ዜና:- የአማራ ሳይንቱ ታቦር ተራራ ብርጌድ ሌሊቱን ድል ቀንቶታል:: "ዘመቻ ፊታውራሪ ደሳለው ስጦት እና ግራዝማች አረቡ ታደሰ" በሚል ልዩ የሰማዕታት መዘከሪያ እና አደራ መወጫ ኦፕሬሽን አዳሩን በደ/ወሎ ዞን ምዕራባዊ ክፍል አማራ ሳይንት ወረዳ ቄታ ቀጠና አቦ ሜዳ የተባለ ስፍራ ላይ ታሪክ ተሰርቷል!። በዚህም መሰረት የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አ/ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ታቦር ተራራ ብርጌድ 3ተኛ ወንድም መልኬ ሻለቃ እና የብርጌዱ ቃኝ ቡድን በጥምር ጦሩ ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈፅመው ጠላትን ጭዳ ማድረግ መቻላቸውን የክፍለ ጦሩ ስትራቴጅክ እቅድ ዘርፍ ኃላፊ እና የብርጌዱ ስራ አስፈጻሚ የሆነው ፋኖ መምህር ተመቸው ጀንበሩ አስታወቀ:: ከቀኑ 10 ሰአት ጀምሮ እስከ ሌሊት ድረስ ሞት አይፈሬዎቹ የአማራ ሳይንት አናብስት የፊታውራሪ ደሳለው ስጦት እና ግራዝማች አረቡ ታደሰን ደም በፀጉራቸው ልክ ለመመለስ በማሰብ በሰሩት በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን የጠላት ሐይል ክፉኛ የተመታ ሲሆን አስከሬን እና ቁስለኛውን ጭኖ ወደ አጅባር ከተማ ፈርጥጧል ብሏል። ጥምር ጦሩ በገጠመው ሽንፈት የበሳጭቶ ቄታን በሞርተር በመደብደብ ላይ እንደሚገኝም ነው ፋኖ ተመቸው ከስፍራው የገለፀው:: ታቦር ተራራ ብርጌድ የአማራ ሳይንት ወረዳን ከጠላት ነጻ ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ሲሆን የብርጌዱ ዋና አዛዥ የነበረው ፊታውራሪ ደሳለው ስጦት ከብርጌዱ የሰው ሀብት ሀላፊ ከግራዝማች አረቡ ታደሰ ጋር በመሆን የርዕሰ አድባራት ወ ገዳማት ተድባበ ማርያምን ደጅ አናስደፍርም ብሎ በጀግንነት አንበሳ መጫሪያ እና ተሮ ሜዳ ላይ ተፋልሞ የጠላት ሀይል ድሽቃ ተኳሽን ከአፈር ጋር ከቀላቀለ በኋላ የልቡን ሰርቶ ከጓዱ ጋር በክብር ማረፉ አይዘነጋም:: ዛሬ ወንድሞቹ ደም የመመለስ ግደታቸውን ጥንቅቅ አድርገው ተወጥተዋል:: በአንበሳ መጫሪያው ትንቅንቅ 100 አለቃ ምልክት የተባለውን የጠላት ሀይል አዋጊ አንገት ለመያዝ እና ዲሽቃውንም ለማስቀረት ፊታውራሪ ደሳለው ስጦት እየተከተለ ሙከራ በሚያደርግበት ቅጽበት በተተኮሰ ጥይት ነበር የተመታው:: እሱን ይዞ ሊወጣ ሲል የለጋምቦው ጀግና ግራዝማች አረቡ ታደሰም ሊሰዋ እንደቻለ በወቅቱ ክፍለ ጦሩ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል:: የእነዚህ ጀግኖችን ደም በመመለስ ወረዳውንም ከጠላት ነጻ አድርገው የሰማዕታቱን አደራ ለመጠበቅ የታቦር ተራራ ብርጌድ ጀግኖች እንቅስቃሴ ጀምረው በዛሬው እለትም አስደናቂ እና አኩሪ ጀብዱ ፈፅመዋል:: የምሽቱን ኦፕሬሽን የመራው የክፍለ ጦሩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ እና የታቦር ተራራ ብርጌድ ዋና አዛዥ ፋኖ ብሩክ ሞገስ መሆኑንም ነው ለማወቅ የተቻለው::
✍️
በላይነህ ሰጥአርጌ
ድል ለሰፊው የአምሓራ ሕዝብ
‼️
🟢
🟡
🔴
⚔
⚔
⚔
🟢
🟡
🔴
https://t.center/Negedeamharap
https://t.center/Negedeamharap
Поделиться
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Бот для знакомств
Запустить