Смотреть в Telegram
ሰበር ዜና! የጨሌ ገብርኤልን በሀይል አስከብራለሁ በማለት አሰሱንም ገሰሱንም አግተልትሎ ውጊያ የከፈተው የአገዛዙ ሰራዊት በነበልባሎቹ  ብርቱ ክንድ ተቀጥቅጦ አንድ አይሱዙ ሙትና ሦስት አምቡላንስ ቁስለኛውን ተሸክሞ ተመለሰ። ትናንት ሻምበል መሪውንና ምክትል መሪውን ከበርካታ የመከላከያ እና የሚሊሻ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው የተነጠቀው የብልፅግናው አሸርጋጅ የብርሀኑ ጁላ ጦር ታህሳስ 19/2017 ዓም በሸዋ ክፍለሀገር ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የጨሌገብርኤልን በእልህ ለማስከበር ከቀበሮ ጉድጓዱ ወጥቶ በአራት አቅጣጫ ያለ የሌለ ሀይሉን አለኝ ካለው ከባድ መሳሪያ ጋር በማዋሀድ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ከባድ መሳሪያውን በማስወንጨፍ እግረኛውን በማስጠጋት ጥቃት ለመፈፀም ቢጋጋጥም በሀምሳ አለቃ ፍቃዱ ጥላሁን የሚመራው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ነበልባል ብርጌድ የፋኖ አባላት በሰነዘሩት መብረቃዊ ጥቃት በዓል ሊያከብር የሔደው የጠላት ሀይል ራሱንም ሳያስከብር ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ተመልሷል። ማንነታችንም እምነታችንም በእጃችን ነው ያሉት ቀጫጭኖቹ የነበልባል ብርጌድ የፋኖ አባላት አማራን ለማጥፋት አሰፍስፎ የወጣውን የጠላት ሀይል በአራት አቅጣጫ በከፈቱት መብረቃዊ ጥቃት ጠላት ወዳሰበበት የጨሌ ገብርኤል ሳይደርስ አቡጫ አገር ላይ ገትረውት ውለዋል። በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ነበልባል ብርጌድ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ክፍል ለከሰም ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል በላከው መረጃ ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በተካሔደው እልህ አስጨራሽ ዉጊያ አንድ አይሱዙ ሙትና ሦስት አምቡላንስ ቁስለኛውን ተሸክሞ ፀሀይ ስትጠልቅ ወደ ጉድጓዱ የገባ ሲሆን ያሰበው ያልተሳካላት፣ሜዳው ሁሉ ገደል የሆነበት የብርሀኑ ጁላ ጦር ጄነራል መድፍን ጨምሮ ሌሎች ከበባድ መሳሪያዎችን ህዝባዊ ሀላፊነት በጎደለው መልኩ ሲተኩስ ውሎ ሁለት ንፁሀንን ገድሏል ብሏል። ድል ለሰፊው የአምሓራ ሕዝብ‼️ 🟢🟡🔴🟢🟡🔴 https://t.center/Negedeamharap https://t.center/Negedeamharap
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Бот для знакомств