Смотреть в Telegram
፩ አማራ ሚዲያ
ሰበር ዜና ከፍተኛ የጦር መሪዎች የአማራ ፋኖን መቀላቀላቸው ተበሰረ። ሻለቃ ሙላት ሲሳይና ሻምበል ጌትነት ንጉሴ የአማራ ፋኖ በጎጃምን ተቀላቅለዋል። በመከላከያ ተቋሙ ውስጥ በርካታ መኮንኖችን በማሰልጠን ስመጥር የሆነው ሻለቃ ሲሳይ በ1998 ዓ.ም ሰራዊቱን ከተቀላቀለ በኋላ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በተለያዩ የግልና የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመጀመሪያና የማስተርስ ዲግሪውን በማዕረግ በብር ሜዳልያ መመረቁ ተነግሯል። ሻለቃው በUN ከ12 በላይ የስልጠና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት በማግኘት በጦሩ ውስጥ ስመጥር ጀግና መሆኑ ሲነገር ተቋሙን እስከለቀቀበት ድረስ በርካቶችን ከማሰልጠንና ከማስተማር ባለፈ የስርዓተ ትምህርት ጥናትና ምርምር ቡድን መሪና የአካዳሚክ ዲፓርትመት ዲን እንደነበር ተነግሯል። በተመሳሳይ የአማራ ፋኖ በጎጃምን የተቀላቀለው ሻምበል ጌትነት ንጉሴ አልትሃድንና አልሸባብን ለ7 ዓመታ የተዋጋ ጀግና መሆኑ ሲነገር በኢትዮጵያ ወታደታዊ አካዳሚ በሚሊተሪ ሳይንስ እና አመራርነት በብር ሜዳልያ መመረቁ ተገልፃል። ሻምበል ጌትነት ንጉሴ በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር በመሄድ የ17ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ዘመቻ ኃላፊ በመሆን ማገልገሉም ተነግሯል። እኝህ እንቁ የአማራ ማህፀን ያፈራቸው ጀግኖች ትውልድና ዕደገታቸው፤ ሻለቃ ሙላት ሲሳይ ደቡብ ጎንደር ደብረታቦር እንዲሁም ሻምበል ጌትነት ንጉሴ ደግሞ ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ምድር ነው ተብሏል።
ድል ለሰፊው የአምሓራ ሕዝብ
‼️
🟢
🟡
🔴
⚔
⚔
⚔
🟢
🟡
🔴
https://t.center/Negedeamharap
https://t.center/Negedeamharap
Поделиться
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Бот для знакомств
Запустить