Смотреть в Telegram
፩ አማራ ሚዲያ
በራያ አላማጣ ወረዳ ከዋጃ ከተማ በቅርብ ርቀት በተካሄደ ውጊያ ሁለት ከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦችን ጨምሮ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ተሰማ! ታህሳስ 12/2017 ዓ/ም ምሽት ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት ገደማ ድረስ በራያ አላማጣ ወረዳ ከዋጃ ከተማ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ዋልካ መንደር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ በተደረገ ውጊያ ለጊዜው ማዕረጋቸው ያልታወቀ ሁለት በአራዊት ሰራዊቱና ሰራዊት አዛዦችን ጨምሮ ከ20 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸውን የአማራ ፋኖ በወሎ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል። በዚህ ጥቃት የተገደሉ የሁለቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች አስከሬን ከቆቦ ከተማ በቅርብ ርቀት ልዩ ስሙ ጮቢ በር ላይ የቀብር ስርዓቱ እንደተፈፀመ ማረጋገጡንም ነው የሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ለጣቢያችን የገለፀው። በአገዛዙ ወታደሮች ላይ እርምጃውን የወሰዱት አማራ ፋኖ በወሎ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የሀውጃኖ ክፍለጦር ቃኝ አባላት መሆናቸውንም ነው የሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ለጣቢያችን ጨምሮ የገለፀው።
Поделиться
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Бот для знакомств
Запустить