View in Telegram
Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
ተቀበል…7 • ማስታወቂያ… "…የፊታችን ማክሰኞ በእኔ በዘመዴ የቲክቶክ ቤት በወልቃይት ጉዳይ ነጭ ነጯን እናወራለን። የማይካድራን ጭፍጨፋም በሃላል እንወያይበታለን። ተከዜ ወንዝ ወስጥ ተገድለው የተጣሉት ትግሬዎች ናቸው ዐማሮች የሚለውንም እየጠየቅን በግልፅ እንወያያለን። ወልቃይት ለዐማራው እንደ ዐማራ፣ ለጎንደር ዐማራ በተለየ ሁኔታ አሁን ላይ ምን ዓይነት ጥቅም እየሰጠ ነው? እውን የጎንደር ዐማራ በወልቃይት ላይ የማዘዝ፣ የመኖር፣ የመጠቀም መብት አለውን? እንደ አያሌው መንበርና ምስጋናው አንዱአለም ቀይ መስመር ብሎ ነገር የለም። ቢያምህም፣ ቢጠዘጥዝህም። የግድ ጨከን ብለህ ትወያያለህ። የግድህን አልኩህ። የግድህን ትወያያለህ። "…ሌላው ትዊተር ስፔስ ነው። የስፔሱን ጥቅም ያየሁት በዚህ ባለፉት ሁለት ቀናት ነው። እናም እዚያ ሰፈር ቀደም ብዬ ቤት ቦታ ገዝቻለሁ። 10 ሺ ቤተሰብም አፍርቻለሁ። አሁን ምን አቀድኩ መሰላችሁ በትዊተር መንደር ብዙ የደርግ ርዝራዦች በዝተው አይቻለሁ። እናም እነዚህን የትውልድ ህልም ሾተላዮችን ቆንጆ፣ ቆንጆ ጠጡኝ፣ ጠጡኝ የሚል ነጭ ነጯን የሆነ የሚያሽር ፈዋሽ የሆነ የኮሶ መድኃኒት እየጋትኩ ብፈውሳቸው ብዬ አሰብኩ። እነ ሲሳይ ሙላውን፣ እነ ደርጉ አቶ ወዳጄን እና እስክንድራውያንና ስኳድን የማገኘው እዚያ መንደር ነውና ልክ እንደ ቲክቶካችን ስፔሱንም መስመር ባስይዘው ምን ትመክሩኛላችሁ? • እየኮመታችሁ…!
Share
Telegram Center
Channel
Join