View in Telegram
ወጋገን ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የአንድ አክሲዮን ትርፍ 36.89 በመቶ መድረሱን ገለጸ ባንኩ እ.ኢ.አ በ2023/24 በጀት ዓመት በታሪኩ ከፍተኛውን ብር 9.8 ቢሊዮን ገቢ ማስመዝገቡን አስታውቋል። ባንኩ ዛሬ በሒልተን ሆቴል 31ኛ መደበኛና 15ኛ አስቸኳይ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የጠራ ሲሆን፣ በዚህም ከታክስ በፊት 2.2 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን የባንኩ የዳይሬክቶሬት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዲሹ ሁሴን ተናግረዋል። በገለጻው መሠረት፦ - ባንኩ 9.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን፣ ተቀማጭ ገንዘቡ ደግሞ 22 በመቶ እድገት በማሳዬት 52.1 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ገልጿል። - እ.ኤ.አ ሰኔ 30/2024 የባንኩ ባለአክሲዮኖች ብዛት 12 ሺሕ፣ የተከፈለ ካፒታሉ 27 በመቶ እድገት በማሳዬት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 5.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል። - የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል 33 በመቶ እድገት በማሳዬት 9.2 ቢሊዮን ብር፣ የአንድ አክሲዮን ትርፍ 36.9 በመቶ ደርሷል። - ባንኩ የሰጠው ብድር በዓመቱ መጨረሻ ሲሰላ 45.1 ቢሊዮን ብር፣ የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 65.7 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል። #TikvahEthiopia @tikvahethmagazine
Telegram Center
Telegram Center
Channel