View in Telegram
🔈 #የወጣቶችድምጽ " በየት በኩል እንስራ ? " ከሰሞኑን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የኮንስትራክሽን እና ሌሎች ሾል ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ወጣቶች በምሬት አንድ ሃሳባቸውን አካልፈዋል። " እንናገረውና ሰው ሰምቶት ይወጣልን ብለን ነው "  ሲሉ ስለደረሰባቸው ነገር አጋርተዋል። እኚ ወጣቶች በክልል ከተሞች ተንቀሳቅሰው ለመስራት የሚታትሩ ናቸው። ግን በብሄር፣ በዝምድና በትውውቅ የሚሰሩ ስራዎች ፈተና ሆነውባቸዋል። ተስፋም እያስቆረጣቸው ነው። በቅርቡ ለአንድ ሾል ይወዳደራሉ ፤ ይህንን ሾል እንደሚያሸንፉ ባለሙሉ ተስፋ ሆነው ስራውን ለማሰራት ማስታወቂያ ወዳወጣው አካባቢና ቢሮ ያመራሉ። ከአንድ ኃላፊ ተሰጠን ያሉት መልስ ግን " አትልፉ ፤ ይሄንን ሾል ወስዳችሁ ልትሰሩ የምትችሉ አይመስለኝም " የሚል ነው። ይህ የሆነው ደግሞ " ከሌላ አካባቢ የመጡ ናቸው " በሚልና ከየት አካባቢ እንደመጡ በማጣራት እንደሆነ አስረድተዋል። በዚህም " ከሌላ አካባቢ " በሚል አደገኛ አመለካከት ብቻ ስራውን ሌላ ሰው እንዲወስደው ስለመደረጉ በምሬት ተናግረዋል። ድርጊቱ እጅግ እንዳሳዘናቸው ይሄ የብሄር፣ የዝምድና፣ የትውውቅ፣ የአካባቢ መርጦ ሾል ብዙ ወጣቶች አቅም እያላቸው እንዳይሰሩ እያደረገ ያለ እጅግ አደገኛ መርዝ መሆኑን ሳይናገሩ አላሉፍም። ሌላ ቃላቸውን የተቀበልናቸው ወጣቶች ለሾል ጉዳይ ካለው የተንዛዛ ሂደት ባለፈ የዝምድና የትውውቅ ሾል ተስፋ አስቆርጧቸው ምን እንደሚያደርጉ ግራ እንደገባቸው ተናግረዋል። በአንድ ሀገር በአንድ ባንዲራ ሾር ከአንዱ ክልል ወደ ሌላው ሄዶ ሾል መስራት ፈተና እንደሆነና ስራዎች በዝምድና፣ ለተወላጅ፣ ለአካባቢ ሰው በትውውቅ እንደሚሰጡ ጠቁመዋል። " ሚዲያውም ሆነ ሌላው አካል እነዚህን መሰል ጉዳዮች ሳይሆን ለልሹ የገቢ ትርፍ እና ተመልካች የሚያስገኝለትን ጉዳይ እየመዘዘ ነው የሚሰራው " በማለትም ወቀሳ አቅርበዋል። " ጨረታ፣ ውድድር በሚኖር ሰዓት እንኳን ዘመድ ያለው፣ ገንዘብ ያለው በእጅ አዙር ስራውን ያገኛል ይሄ ምንም የሚደበቅ አይደለም " ብለዋል። ወጣቶች በፈለጉት ቦታ ተንቀሳቅሰው መስራት ካልቻሉ ሀገር ውስጥ እንዴት ይቀመጣሉ ? ቆይ በገፍ ቢሰደዱስ ምን ይገርማል ? ሲሉም ጠይቀዋል። በዙሪያቸው ያለ እጅግ ብዙ ወጣት ባለው አሰራር ምክንያት ተማሮ ከሀገር ለመውጣት ብዙ እንደሚጥር ጠቁመዋል። " አሁን ላይ ያለው ነገር ሁሉ ብሶበት ቁጭ ብሏል። የወጣቱን፣ የህዝቡን ድምጽ ሰምቶ ችግር ከማስተካከል ይልቅ ህዝብን ዝቅ ብለው እንዲያገለግሉ የተቀመጡ አካላት ሌላ ስም መስጠት እና መፈረጅ ስራቸው ሆኗል " ሲሉ አክለዋል። ከአንድ ክልል፣  ዞን ፣ ወረዳ ሌላ ቦታ ሄዶ ለመስራት ችግር ከሆነና ስራው ሁሉ ብቃት ላለው ሳይሆን በብሄር፣ ትውውቅ፣ ዝምድና፣ በሙስና እየተመረጠ የሚሰጥ ከሆነ እንዴት ለውጥ ሊመጣ ይችላል ? ወደኃላ መጓዝ ማለትስ ይህ አይደለም ? ይህ የበርካታ ወጣቶች ጥያቄና ድምጽ ነው። #TikvahEthiopia #የወጣቶችድምጽ @tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram Center
Telegram Center
Channel