View in Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " ህዝብ በማደናገር ላይ ይገኛሉ " - በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የማዕከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ክፍፍል ተቀራርቦ ከመፈታት ይልቅ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ እየተካረረ መጥቷል። " ከህወሓት አባልነት የተባረሩ በማንኛውም ቦታና ጊዜ በህወሓት ስም ፓለቲካዊ ስራና እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም " ሲል በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት…
#TPLF ከዛሬ ጀምሮ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ጨምሮ ሁሉም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ በጉባኤ ያልተሳተፉ የስራ ሃላፊዎች በጉባኤ በተሳተፉ ሹማምንት መቀየሩን በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት " ወስኛለሁ " ብሏል። " ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ህወሓት ከሰጣቸው የስራ ሃላፊነት ተነስተዋል እንዴትና በማን እንደሚተኩ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገርኩ ነው " ብሏል በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት። ከየትኛው የፌዴራል መንግሥት አካል ጋር እየተወያየ እንደሆነ በግልጽ ያለው ነገር የለም። ስለ ጉዳዩ እስካሁን በምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ከሚመራው ህወሓት በኩል የተሰጠ መልስ የለም። በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራ ህወሓት ባወጣው የውሳኔ መግለጫ ፥ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔዎች ፣ ቢሮዎች ፣ ኤጀንሲዎች ፣ ኮሚሽኖች የዞን አስተዳደሮች የሚገኙ በጉባኤ ያልተሳተፉ የስራ ሃላፊዎች በማንሳት በጉባኤ በተሳተፉ አባላቱን ሙሉ በሙሉ መተካቱ አስታውቋል። በዚሁ መሰረት ፦ - አቶ በየነ መክሩ - ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት - ዶ/ር ሓጎስ ጎዲፋይ - ወ/ሮ አልማዝ ገ/ፃዲቕ ከጊዚያው አስተዳደሩ ካቢኔ በማንሳት በ - ዶ/ር አብራሃም ተኸስተ - አቶ አማኒኤል አሰፋ - ዶ/ር ፍስሃ ሃብተፅዮን - አቶ ተወልደ ገ/ፃድቃን - ወ/ሮ ብርኽቲ ገ/መድህን - አቶ ይትባረክ አምሃ - ዶ/ር ፀጋይ ብርሃነ መተካቱ ገልጿል። - አቶ ርስቁ አለማው - አቶ ሰለሙን መዓሾ - አቶ ሺሻይ መረሳ - አቶ ሃፍቱ ኪሮስ ከዞን ዋና አስተዳዳሪነት በማንሳት - በአቶ ተኽላይ ገ/መድህን - በአቶ ወልደኣብራሃ ገ/ፃዲቕ - በአቶ ሺሻይ ግርማይ - በአቶ ፍስሃ ሃይላይ - በአቶ ሃይላይ ኣረጋዊ - በዶ/ር አብራሃም ሓጎስ ተተክተዋል ብሏል። በተጨማሪ - አቶ ረዳኢ ሓለፎም - ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ - አቶ ነጋ አሰፋ - ዶ/ር ገ/ሂወት ገ/ሄር ከኤጀንሲ እና የኮሚሽን የስራ ሃላፊነት ወርደዋል ያለው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራ ህወሓት በእነ ማን እንደተተተኩ ያለው የለም። ይህ ዘገባ አስከተጠናቀረበት ቀንና ሰዓት ድረስ በምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ ከሚመራ ህወሓት በኩል የተሰጠ መልስ የለም። #TikvahEthiopiaMekelleFamily
@tikvahethiopia
Share
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Find friends or serious relationships easily
Start