" ... የቤተሰብ ዋነኛ ፍላጎት ፍትህን ማግኘትና እውነቱን ማወቅ ነው " - የአቶ በቴ ኡርጌሳ ቤተሰብ
የአቶ በቴ ኡርጌሳ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፅሟል።
ስርዓተ ቀብራቸው ቤተሰቦቻቸው ፣ ዘመዶቻቸው በርካታ ሰዎች ፣ ወዳጆቻቸው በተገኙበት ዛሬ በመቂ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው የተፈፀመው።
አንድ ቀላቸውን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ የሰጡ የቤተሰብ አባል ፤ " ያው እንደ በቴ ከዚህ በላይ ብጠበቅም ብዙ ሰው ከሩቅም ከቅርብም መጥተው ስርዓተ ቀብራቸው ላይ ተገኝተው ቤተሰብም ቀብሩን ፈጽመው በሰላም ወደ ቤት ተመልሰዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
በትውልድ ከተማቸው መቂ ስርዓተ ቀብራቸው የተፈጸመው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ማክሰኞ ሌሊት ተገድለው ትናንት ማለዳውን አስከሬናቸው ከመቂ ወደ ባቱ መውጫ መንገድ ላይ ተጥሎ መገኘቱ ይታወቃል።
የቤተሰቡ አባል ፤ " የበቴ አስክሬን ትናንት ጠዋት በአከባቢው ማህበረሰብ እና ቤተሰቦቻቸው ከመንገድ ተነስቶ ወደ ቤት ከተወሰደ በኋላ፤ ዛሬ ጠዋት ወደ አከባቢው ሆስፒታል በመውሰድ የአስከሬን ምርመራ ተደርጎለት ነበር፡፡ " ብለዋል።
" ቤተሰብ እንደ ትልቅ ነገር ያየው አንዴ የሞተውን ልጃቸውን ወስደው በስርዓቱ ቀብሩን መፈጸም ነው፡፡ ዛሬ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ አስከሬኑ እንዲመረመር የሆነው #በህግ_አዋቂዎች ምክር ነበር፡፡ ፖሊስ አስከሬኑን ወደ ምርመራ ባይወስድም ትናንት ጠዋት መረጃዎችን አሰባስቦ ሄዷል " ሲሉ ገልጸዋል።
እኚህ የቤተሰብ አባል በአቶ ቤተ አስከሬን የተለያዩ የሰውነት አካል ላይ በርካታ ያሉት ቦታ ላይ በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የሚያመላክት ብዙ ቁስሎች በአይናቸው መመልከታቸውን አስረድተዋል፡፡
" የቤተሰብ ዋነኛ ፍላጎት ፍትህን ማግኘት እና እውነቱን ማወቅ ነው " ብለዋል።
" ቤተሰብ የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ማወቅ ይፈልጋል፡፡ በፍርድ ሂደት ፍትህ ቢገኝ ቤተሰቡንም የአከባቢውንም ማህበረሰብ የሚያረካ ጉዳይ ነው " ሲሉ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።
በግፍ ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ተጥሎ የተገኘው የኦነግ ከፍተኛ አመራር አቶ በቴ ኡርጌሳ ባለትዳርና የ4 ልጆች አባት ነበሩ።
@tikvahethiopia