Смотреть в Telegram
በአደጋ ምክንያት ለእድሳት ተዘግቶ የነበረው ስመ ጥሩ የኖትር ዳም ካቴድራል በሮች በዛሬው እለት ድጋሚ ተከፍተዋል። በመክፈቻ ስነ ስርኣቱ ላይ ትራምፕን ጨምሮ በርካታ የሀገር መሪዎች ፈረንሳይ ከትመዋል። ቤተ ክርስቲያኑ ለአደጋ ያጋለጠው ጉዳይ በተመለከተ በውል ባይታወቅም ኤሌክትሪክ ወይንም ያልጠፋ ሲጋራ ሊሆን ይችላል የሚል በምርመራው ውጤት ላይ የተመሠረተ ጥርጣሬ አለ። ወጣም ወረደም አብዛኛው ታሪካዊ የሚባለውን ቸርች የሚያስመርቁ እንግዶች ሀይማኖት አልባ የሚባሉ ታዋቂ ስብእናዎች ናቸው። በሀይማኖታዊ ስርኣቱ ወቅትም መጠጥ እየተጎነጩ ሁኔታውን ሲከታተሉ ለተመለከተ አዝናኝ ትርኢት የሚያዩ እንጅ ሀይማኖታዊ ክስተት የሚታደሙ አይመስሉም። በምዕራቡ አለም ያለው ሀይማኖትን ባህል የማድረግና ከዚያ የዘለለ ሚና በህይወት ውስጥ እንደሌለው የማሰብ ተግባር በሒደት የመጣባቸው እጅግ አደገኛ በሽታ ነው። ሀይማኖታዊ ስርኣቱን ከትውስታ ማጫሪያነት የዘለለ ትርጉም ሳይሰጡ ለድግሶች መጠቀም ኖርማላይዝ የተደረገ ኹነት ሁኗል። ሀይማኖት የተሰመረለት ባውንደሪ ከሌለና የዘፈቀደ ከሆነ መሠል መደበላለቅ መኖሩ የሚጠበቅ ነው። ከአመታት በኃላ በሀገራችንም መሠል ፈተና በፕሮቴስታንቱ በኩል እንደሚመጣ ይገመታል። እንደ አማኝ ያሰመሩትና የከለሉት ይህ ነው የሚባል ጠንካራ መሠረት መፍጠር ላይ አልተሳካላቸውም። ለግብረ ሰዶማውያን ጥብቅና የሚቆሙ የአውሮፓ ሚሽነሪዎችን ተቀብሎ አብሮ የሚሰራ ቸርች ነገ ባውንደሪ ይፈጥራል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ለጸያፍ ተግባራቸው መጠቀሚያ ካላደረጓቸውም መልካም ነው። የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.center/Yahyanuhe
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Бот для знакомств