Смотреть в Telegram
"አውልቀው ይማሩ" እንደ ሙስሊም አንድ ሰው በአንድ አስተምህሮ ዙሪያ የተለያየ አቋም ሊኖረው ይችላል። ለአብነት ኒቃብን በተመለከተ "ኒቃብ ፈርድ ነው" ብሎ የሚያስብ ሊኖር ይችላል። አልያም "ሙስተሀብ ነው" ብሎ የሚያምንም ሊኖር ይችላል። ነጥቡ ግን እሱ አይደለም፤ ዋናው ነገር እንደ አንድ የሀገሪቱ ዜጋ "ፍላጎታችን ኒቃብ ለብሶ መማር ነው" ብለው የሚያምኑ ሰዎች መብታቸው እስከምን ድረስ ነው? የሚለው ይመስለኛል። "ኒቃብ እለብሳለሁ" የምትል እንስት ተማሪ ሀገሪቱ እሷን ያማከለ የመብት ማዕቀፍ የለውም?እንደ ዜጋ ለእሷ የሚሰጥ የመብት ከለላ የለም? ይህንን ጥያቄ የጠየቀ ሰው ሁሌም እንደ ባዕድ ዜጋ ምርጫ አልባ የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ "ኒቃብ አውልቃ ትማር" የሚለው መልስ እስከመቸ ነው ብቸኛ ምርጫዋ ሊደረግ የሚገባው? ኒቃቧን ለብሳ መማር የምትችልበትን የአሰራር ማዕቀፍ ማዘጋጀት ምን ያክል ከብዶ ነው ለዘመናት ሙስሊም ሴቶች በዚህ ጥያቄ መከራቸውን የሚያዩት?የቀናነት ችግር ከሌለ በስተቀር በጣም ኢምንት የሙስሊም ቁጥር ያለባቸው ሀገራት ሳይቀር አመቻምቸውና መብታቸውን ሳይጨፈልቁ የሚፈጽሙትን ቀላል ተግባር በዚህ ደረጃ የትውልድ መከራ አናደርገውም ነበር። በመጅሊሱም በኩል ይሁን በምሁራኑ በኩል ትኩረት መደረግ ያለበት ይህ ይመስለኛል። ዘላቂ የህግ ማዕቀፍና የአሰራር ሒደት እንዲዘጋጅለት ግፊት ማድረግ ያስፈልጋል። የዛሬ 30 አመት የነበረ ችግር ላይ ዘንድሮም መከራከር አድካሚና ጉልበት ጨራሽ ነው። https://t.center/Yahyanuhe
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Бот для знакомств