Смотреть в Telegram
የኦነግ ሸኔ መንግሥት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶችን በግዳጅ ለውትድርና እየመለመለ ይገኛል በማለት አዲስ ባወጣው መግለጫ ከሷል። 📌ክልሉ ሀሰት ነው ብሏል ቡድኑ፣ በርካታ ወጣቶች ከግዳጅ ውትድርና ለመቅረት ለመንግሥት ባለሥልጣናትና ለገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ከፍተኛ ገንዘብ እየከፈሉ ይገኛሉ ብሏል። ገዥው መንግሥት የክልሉን ሕዝብ የሰላም ጥያቄ በመጥለፍና የሰላም ጥሪ የሚደረግባቸውን ሕዝባዊ ሰልፍች በማዘጋጀት ለራሱ ፖለቲካዊ ዓላማ እየተጠቀመባቸው ይገኛል በማለት የወቀሰው ቡድኑ፣ ሕዝቡ መንግሥት ያልፈቀደውን ሰልፍ ሊያደርግ እንደማይችል ይታወቃል ብሏል። በተያያዘ፣ ዜና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ ትናንት በክልሉ በርካታ ዞኖች በተካሄዱት የሰላም ጥሪ የተንጸባረቀባቸው ሕዝባዊ ሰልፍች እጁ እንደሌለበት ዛሬ በኮምኒኬሽን ቢሮው በኩል አስታውቋል። ሰልፎቹ ሕዝቡ በራሱ ተነሳሽነት ያካሄዳቸውና በክልሉ ያለው አለመግባባት በሰላም እንዲፈታ የተጠየቀበት መድረክ መኾኑን የጠቀሰው የክልሉ መንግሥት፣ የክልሉ መንግሥት ለድጋፍ እንዳዘጋጀው ተደርጎ በተለያዩ አካላት የሚናፈሰው አሉባልታ ግን ከእውነት የራቀ ነው በማለት አስተባብሏል። አሉባልታው በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት የሕዝቡ የሰላም ጥሪ እንዳይደርሳቸው በሚፈልጉ አካላት ኾን ተብሎ የተደረገ መኾኑን እንደሚያውቅ የክልሉ መንግሥት ጨምሮ ገልጿል። ⬇️⬇️⬇️ ቤተሰብ ⬇️⬇️⬇️ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇 https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ https://t.center/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.center/+WNLm9dbzuIlp9DF4 ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ https://t.center/wasumohammed
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram Center
Telegram Center
Канал