ነባር የሙስሊም መካነ መቃብር በኮሪደር ልማት ይፈርሳል መባሉ ቅሬታ ገጠመው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ጌዲዮ ዞን፣ ይርጋጨፌ ከተማ ነባር የሆነ የሙስሊም መካነ መቃብር የተወሰነ ክፍሉ ለኮሪደር ልማት ይፈርሳል መባሉ ቅሬታ መፍጠሩን ነዋሪዎች እና የከተማው የእስልምና ጉዳዮች ሰብሳቢ ተናገሩ።
በከተማው የሚገኘው የቢላል መካነ መቃብር የመንገድ ማስፋፊያን ጨምሮ “ለሕዝብ መዝናኛ” ግንባታ 15 ሜትሩ እንደሚፈልግ የከተማው አስተዳደር ማሳወቁን ተናግረዋል።
መንገድ ዳር የሚገኘው እና ለ50 ዓመታት ዘላቂ ማረፊያ የሆነው መካነ መቃብሩ ለመንገድ ማስፋፊያ የተፈለገውን አምስት ሜትር ገደማ “አገራዊ ነው” በማለት ለኮሪደር ልማቱ እንዲውል ይሁንታ ቢያገኝም፤ ተጨማሪ የመካነ መቃብሩን 10 ሜትር መፈለጉ ግን ተቃውሞ ገጥሞታል።
የከተማው አስተዳደር በይርጋጨፊ ከሚገነቡ አራት ዘላቂ ማረፊያዎች ውስጥ አንዱ መሆኑን ጠቅሶ ‘ልማቱ አይቀሬ ነው’ ብሏል።
አንድ ለጉዳዩ ቀረብ ያሉ የአካባቢው ነዋሪ፣ ሕዝበ ሙስሊሙ “ከሚፈለገው በላይ” አንሰጥም እያለ ነው በማለት፤ ቅራኔው ለመዝናኛ ከተባለው ተጨማሪ ክፍል ጋር የተያያዘ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ከመካነ መቃብሩ የሚፈለገው ስፍራ “ፋውንቴን፣ ማረፊያዎች፣ መዝናኛ፣ በጎን ሱቆች” እንደሚሠሩበት መነገሩን ለጉዳዩ ቀረብ ያሉ ነዋሪ ገልጸዋል።/ቢቢሲ/
⬇️⬇️⬇️ ቤተሰብ❤ ⬇️⬇️⬇️
በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.center/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.center/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
https://t.center/wasumohammed