Смотреть в Telegram
#DireDawa በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ3 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በትራንስፖርት ዘርፍ ለማሰማራት የሚያስችል ስምምነት ከተማ አስተዳደሩ ከስዊፍት ቴክኖሎጂ እና ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር ተፈራርሟል። የስዊፍት ቴክኖሎጂ ተወካይ አቶ ብሩክ አሸብር  በሚቀጥሉት ሶስት አመታት የባጃጅ ተሽከርካሪዎችን በኤሌትሪክ መኪኖች ለመተካት  መታቀዱን ገልጸዋል። በዛሬው ዕለትም 21 የኤሌትሪክ መኪኖች መመረቃቸውን የገለጹት አቶ ብሩክ፥ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እነዚህን ዘመናዊ የኤሌትሪክ የትራንስፖርት መኪኖች በፍጥነት ስራ ለማስጀመር የብድር ምችችት እንደሚያደርግም አስታውቀዋል። ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖቹ ወደ ስራ በሚገቡበት ወቅት የሀይል አቅርቦት ችግር እንዳይከሰት በተለያዩ ቦታዎች ቻርች ማድረጊያ ጣቢያዎች እንደሚዘጋጁም ተገልጿል። @tikvahethmagazine
Telegram Center
Telegram Center
Канал