Смотреть в Telegram
አሐዱ ባንክ ከታክስ በፊት ብር 119.96 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ገለፀ አሐዱ ባንክ 3ተኛ መደበኛ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን ዛሬ አከናውኗል። የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ሰብስቤ የባንኩን የሥራ እንቅስቃሴና የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት ለባለአክስዮኖች አቅርበዋል፡፡ የባንኩ ሪፖርት ምን ይመስላል ? - ባንኩ ከታክስ በፊት ብር 119.96 ሚሊዮን ትርፍ ማስመዝገቡን ገልጿል። - ባንኩን የቅርንጫፍ ተደራሽነት ወደ 104 ከፍ ማድረግ ችያለው ያለ ሲሆን የደንበኞች ቁጥርን 704,000 በማድረስ የተቀማጭ ሃብት መጠኑ ብር 4.6 ቢሊዮን መድረሱን አሳውቋል። - በውጭ ምንዛሪ ረገድ 80.1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማሰባሰብ መቻሉን ሲጠቀስ በዚህ በጀት ዓመት በባንኩ የተሰጠ የብድር መጠን ብር 1.7 ቢሊዮን ደርሷል። - የባንኩ አጠቃላይ ሃብት ብር 6.26 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ የባንኩ የተፈረመ የካፒታል መጠን ብር 1.4 ቢሊዮን ነው። አጠቃላይ የተከፈለ ካፒታል መጠን ደግሞ ወደ ብር 1.03 ቢሊዮን ማድረስ መቻሉ ተነግሯል። አቶ አንተነህ እንደገለፁት የባንኩ ዘርፍ ተለዋዋጭና ጥብቅ በሆኑ መመሪያዎች ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፣ ለማሳያነት በነሐሴ 2016 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የናረውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር በማለም፣ የንግድ ባንኮች በሚያበድሩት ብድር ላይ ጣርያ ማስቀመጡን አስታውሰዋል፡፡ ይህ ፓሊሲ የንግድ ባንኮች በሚያበድሩት ብድር ላይ ጣርያ ማስቀመጡን እና ፓሊሲው አዳዲስ ባንኮችን በከፍተኛ ሁኔታ ገቢ ከሚያስገኝላቸው የብድር አገልግሎት ስለሚገድብ፣ በባንኮቹ አፈጻጸም እና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም በሀብት ማንቀሳቀስ አቅም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ እንደነበር ጠቅሰዋል። #TikvahEthiopia @tikvahethmagazine
Telegram Center
Telegram Center
Канал