የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በገበያ ሞሎች ላይ የቁጥጥር ሥራ በዘመቻ መልክ እየሰራው ነኝ ብሏል።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች በግብር ከፋይነት ተመዝግበው ደረሰኝ የማይሰጡ በመሆናቸው እና ችግሩም በጣም እየሰፋ በመሆኑ ወጥነት ባለው መንገድ ህጉን እንዲያከብሩ እና ወደስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።
ቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ የቁጥጥር ስራው ከዚህ ቀደምም የነበረ ቢሆንም በዘመቻ መልክ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ዘመቻ ሲባል ወደ ቫት ስርዓት ውስጥ ያልገቡትን ማስገባት ፣ፈቃድ የሌላቸው ፈቃድ እንዲያወጡ ማድርግ፣ ደረጃቸው ደረሰኝ መስጠት የሚገባቸው ሆኖ ሳለ የማይሰጡትን ደረሰኝ አስፈቅደው እና አሳትመው መጠቀም እንዲጀምሩ ለማስቻል ያለመ ነው።
ዘመቻው በልዩነት እየተሰራ ያለው የገበያ ሞሎች ላይ ነው ያሉት አቶ ተስፋዬ በዚህ ስፍራ የሚነግዱ ሰዎች የግብር ደረጃቸው ዝቅ ያለ በመሆኑ ወይም ደረጃቸው ትልቅ ሆኖ ሳለ እንደትልቅነታቸው ተመዝግበው ደረሰኝ መስጠት የሚገባቸው ሆኖ ሳለ ሳይሰጡ የሚነግዱ በመኖራቸው ትኩረት መደረጉን ጠቁመዋል።
በአሁኑ ሰዓት በከተማ አስተዳደሩ በግብር ከፋይነት የተመዘገቡ ነጋዴዎች ቁጥር ነጋዴ ያልሆኑ ግብር ከፋዮችን ጨምሮ 490 ሺ አካባቢ እንደሚሆኑ ተናግሯል።
ይህ ቁጥር አዲስ አበባ ላይ ያሉ ነጋዴዎችን በሙሉ አያካትትም።
በክልል ንግድ ፈቃድ ሳያስጠቅሱ ማለትም ክልል ላይ ፈቃድ ሲያወጡ ሌላ ክልል ላይ ቅርንጫፍ እንደሚኖረው ሳያስጠቅሱ የሚነግዱ በአንድ ክፍለ ከተማ ከ 100 በላይ ነጋዴዎች እየተገኙ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ጥያቄ :-መርካቶ አካባቢ በሞሎች ላይ ያለደረሰኝ እየሰራችሁ ነው በሚል ለሁሉም ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ እየተደረገ መሆኑን ሰምተናል መረጃው አላችሁ ወይ ስንል የጠየቅናቸው ዳይሬክተሩ በምላሻቸው :-
"መርካቶ በባህሪው ብዙ የክልል ግብር ከፋዮች የሚያለቅሱበት ቦታ ነው የሌሎች ክፍለ ከተሞች ግብር ከፋዮችም ቅሬታ ያቀርባሉ ደረሰኝ አይሰጡም በሚል ትልቅ ችግር ስላለበት ትኩረት ተደርጎበት ያለ ነው እንጂ አዲስ አይደለም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ቦታው በልዩ ሁኔታ (በግብር አሰባሰብ) በመንግስት ትኩረት ተደርጎበት ሊሰራበት የሚፈለግ አካባቢ ነው ነገር ግን ከአሰራር አንጻር በሚፈለገው ልክ ማሳካት አልተቻለም ነው ያሉት።
ማስጠንቀቂያው በሁሉም ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ገበያ ማዕከላት እና ሞሎች እንዲደርስ አድርገናል ያሉት አቶ ተስፋዬ ለእነዚህ እየተሰጠ ያለው ባደረግነው ክትትል በብዛት ያለደረሰኝ እንደሚሰሩ የተለዩ በመሆናችው ነው ብለዋል።
ማስጠንቀቂያውን በመቀበላቸው የሚደርስባቸው ነገር የለም ያሉ ሲሆን ነገር ግን " ያለ ደረሰኝ እየሰራችሁ መሆኑ ታውቋል አንታወቅም የሚል ድብብቆሽ አቁሙ እና በግልጽ በደረሰኝ ስሩ" ለማለት መሆኑን ተናግረዋል።
#በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ መሰረት ያለደረሰኝ ሲነግድ የተገኘ ነጋዴ እስከ 100 ሺ የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል።
@tikvahethmagazine