Смотреть в Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ፤ " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ " ሲል ውድቅ አድርጎታል። ህወሓት ባወጣው መግለጫ ፥ " የስራ ኃላፊዎቼ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማካሄድ ሕጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል። " በአፍሪካ ህብረት ፓናል ውይይትም ይህ ጉዳይ ተነስቶ ህጋዊ ሰውነቱ መመለስ እንዳለበት…
ትግራይን ዳግም ወደ ጦርነት የሚያስገባ ተጨባጭ ስጋት አለ ?
" ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው። ወደ ጦርነት የሚያስገባ ምንም ነገር የለም " - አቶ አማኑኤል አሰፋ
በሊቀ - መንበሩ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የ14ኛው የህወሓት ጉባኤ ቃል አቀባይ አማኑኤል አሰፋ ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ጦርነት የሚያስገባ ነገር የለም ብለዋል። አቶ አማኑኤል ፥ " በአንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ተሰብስቦ ስለ አንድ ድርጅት ውስጣዊ ጉዳዮች መወሰን ወደ ጦርነት የሚያስገባ አንድም ምክንያት የለም " ሲሉ ተናግረዋል። " ጦርነት በዚህን ያህል ኢትዮጵያ ውስጥ ርካሽ አይደለም " ብለዋል። " ጦርነት አስፈላጊ ሆኖ አማራጭ ቢሆን ኖሮ ትግራይ ውስጥ ያሉት ችግሮች ሌላ ጦርነት ይጋብዙ ነበር " ሲሉ ተደምጠዋል። እንዚህ ችግሮች ለተፈጸሙ ወንጀሎች የተጠያቂነት አለመረጋገጥ ፣ በህገመንግስት ላይ የተቀመጠው የክልሉ ግዛት አለመመለስ ፣ የተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው አለመመለስ ፣ የኢኮኖሚ ቀውስ ...ወዘተ እንደሆኑ ነው የጠቆሙት። " ዛሬም ትግራይ ውስጥ ብዙ ችግሮች አሉ። ህዝቡ መስእዋትነት እየከፈለባቸው ነው ግን የተጀመረውን የሰላም ተስፋ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲሸጋገር ህዝቡ መስእዋትነት እየከፈለ እየኖረ ነው " ብለዋል። " ያሉ ችግሮች ወደ ጦርነት ሳያስገቡ አንድ ህወሓት የሚባል ድርጅት በፕሪቶሪያ ስምምነት አካል የሆነ ባለቤት የሆነ ውስጣዊ ችግሮች አጋጥመውት ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ሰላሙን ዘላቂ ለማድረግ የሚያስችል ስራ በመስራቱ ወደ ጦርነት ሊገባ አይችልም " ሲሉ ተደምጠዋል። " ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደዚህ ብለዋል ... እንዲህ ብለዋል ተብሎ የተለያየ ትርጉም ከተሰጠው በኃላ ይሄን በሚመለከት ህወሓት ጠቅላይ ሚኒስትሩን engage አድርጓል። " ብለዋል። " በዚህ ደረጃ ጦርነት ውስጥ የሚያስገባን ነገር እንደሌለ ግልጽ ሆኗል " ሲሉ አክለዋል። " ህወሓት አንድ ድርጅት ነው " ያሉት አቶ አማኑኤል አሰፋ ፥ " የተለያዩ ስራዎች ሊሰራ ይችላል ፤ ያን ስራ በሚመለከት መወያየትና መነጋገር ይቻላል። ችግሮች ካሉ ለመወያየት እና አብሮ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የተጀመረ የሰላም ማዕቀፍ አለ ያን መሰረት አድርጎ መወያየት እና መፍታት ነው " ሲሉ ተናግረዋል። " ኢትዮጵያ ውስጥ በተከታታይ የተደረጉ ጦርነቶች ናቸው የዛሬውን ችግር ያመጡት " የሚሉት አቶ አማኑኤል " ብዙ ችግር ባለበት ሀገር ሆነን አሁንም ጦርነት ውስጥ ለመግባት የሚያስችል ምንም ምክንያት የለም " ብለዋል። " ስለተሰበሰብን ፣ አንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ህወሓት የሆነ ነገር ስላደረገ ጦርነት አይመጣም ፤ እንዴት ጦርነት በዚህ ልክ ርካሽ ይሆናል ? " ሲሉ ጠይቀዋል። " ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው ፤ ውስጣዊ ችግሩን ለመፍታት ነው ጉባኤ የሚደረገው " ሲሉ ለወይን በሰጡት ቃለ መጠየቅ ተናግረዋል። #TPLF #TIGRAY
@tikvahethiopia
Поделиться
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Бот для знакомств
Запустить