Смотреть в Telegram
FBC (Fana Broadcasting Corporate)
✔
ኢትዮጵያ ለጃፓን ኢንቨስተሮች የተመቸች በመሆኗ በርካታ ኩባንያዎች እየተሳተፉ ነው ተባለ አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለጃፓን ኢንቨስተሮች የተመቸች መዳረሻ በመሆኗ በርካታ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት እየተሳተፉ እንደሚገኙ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሽባታ ሂሮኖሪ ገለጹ። ከ50 በላይ ከጃፓን የመጡ የቢዝነስ ልዑካን የተሳተፉበት የኢትዮ-ጃፓን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ መካሄድ ተጀምሯል። የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፤ በኢትዮጵያ ያሉ የንግድ እና የህግ አሰራሮች የሚያበረታቱ በመሆኑ የጃፓን ኢንቨስተሮች ጋር የኢትዮጵያ መንግስት በትብብር እንደሚሰራ ገልፀዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በመክፈቻው፤ ኢትዮጵያ እና ጃፓን ጠንካራ እና ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል። የንግድ እና ኢንቨስትመንት ሲምፖዚየሙ...
https://www.fanabc.com/archives/279871
Поделиться
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Бот для знакомств
Запустить