Смотреть в Telegram
FBC (Fana Broadcasting Corporate)
✔
የአክሱም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል እየተከበረ ነው አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በየዓመቱ ሕዳር 21 በድምቀት የሚከበረው የአክሱም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ እየተከበረ ነው። ሐይማኖታዊ በዓሉን ለማክበር ወደ ከተማው ያቀኑ እንግዶች ከትናንት ጀምሮ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ በዛሬው እለት እየተከበረ ባለው በዓል ወደ ከተማው የገቡ እንግዶች በበዓሉ ላይ እየታደሙ ነው፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ የእምነቱ ተከታዮች፣ የሐይማኖት አባቶች እና የክልሉ ጊዜያዊ አሥተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። እንዲሁም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እና የውጭ ሀገራት የተገኙ እንግዶች በበዓሉ ላይ ታድመዋል።
Поделиться
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Бот для знакомств
Запустить