ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

Канал
Логотип телеграм канала ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
@esat_tv1Продвигать
238,47 тыс.
подписчиков
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot 🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
Photo
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች‼️

ለ24ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በርካታ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገራት ተሳታፊዎች ፣ አምባሳደሮች ፣ ተጋባዥ አትሌቶች የሚታደሙበት መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጀው የሩጫ ውድድር ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር የውድድሩ ተሳታፊዎች ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንዳለባቸው ፖሊስ ገልፆ  የወድድሩ ተሳታፊዎች  በሚያልፉት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አዲስ አበባ ፖሊስ  ጥሪውን እያስተላለፈ  ውድድሩ የከተማችንን ዋና ዋና መንገዶች የሚያካልል በመሆኑ ሩጫው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቆ ውድድሩ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት  አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው  ሾል መጀመራቸውን አዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ከውድድሩ ዓላማ ውጪ ህገ-ወጥ ተግባራትንና መልእክቶችን ማስተላለፍ የውድድሩን መንፈስ የሚረብሽ ስለሆነ አዘጋጅ ተቋሙ እና ተሳታፊዎች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደለባቸው እያሳሰበውድድሩ  ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፡-

-ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ )
-  ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ) ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ
-   ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ )
-ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት )
-  ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ )
  ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ )
  ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ )
-  ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ )
-  ከ22 አደባባይ ወይም ዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ )
-  ከፒኮክ አዲሱ መንገድ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)
-  ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ አደባባይ)
-  ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ነርክ ተራ )
-  ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት  (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ )
-  ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ )
-  ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ )
-   ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ (ፈረሰኛ መብራት )
-  ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር (ጌጃ ሰፈር መስቀለኛ )
-  ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት  አደባባይ)
-  ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ)
-  ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
-  ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትሮዎሎጂ መታጠፊያ )
-  ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን  (ጥቁር አንበሳ ሼል)
-  ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን (ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ)
-  ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አገር አስተዳደር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ)
ከንጋቱ 11:30 - ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ የተጠቀሱት መንገዶች የሚዘጉ ሲሆን በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ቅዳሜ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ መኪና ለአጭርም ይሁን ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ እያስታወቀ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት 011 1110111 ወይም ነጻ የስልክ መስመር 991 መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ አስታውቋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ታላቅ የምስራች ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ
👉 በካሬ  78,246 ብር ጀምሮ

👉 በ432,000 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ ከፍለው ይመዘገቡ

👉#እስከ 30% ቅናሽ ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚቆይ

👉#50% የባንክ ብድር የተመቻቸለት

  🏠ቢኖሩባቸው ምቹ ፣ ቢያከራዩዋቸው በዶላር ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙባቸው እንዲሁም መልሰው መሸጥ ቢፈልጉ በብዙ የሚያተርፉባቸው ውብና ማራኪ መንደር በለቡ መብራት ኃይል...

👉#እስቱዲዮ 56.6 ካሬ

👉#በለ 1 መኝታ
        ከ 69 ካሬ -85 ካሬ ድረስ

👉#ባለ 2 መኝታ
        ከ 99 ካሬ - እስከ 155 ካሬ

👉#ባለ 3 መኝታ
       ከ 139 ካሬ እና 181 ካሬ

ለበለጠ ☎️ +251940464607
                      0901022738
           
ቤተመንግስት ተገኘ የተባለው ወርቅ ከተሸጠ የመንግስት አካላት ተጠያቂነት እንደሚጠብቃቸው እናት ፓርቲ ገለፀ‼️

ፓርቲው ባወጣው መግለጫው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት “ባደረግነው የብሔራዊ ቤተ መንግሥት እድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪ.ግ. ወርቅ ኮሚቴ አቋቁመን ወደ ብሔራዊ ባንክ አስገብተናል” በሚል ያቀረቡት ገለፃ ላይ ለህዝብ ማብራርያ እንዲሰጡ ጠይቋል።

"የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ግልጽ አይደለም" ያለው ፓርቲው "ከእርሳቸው ወደ ሥልጣን መምጣት አስቀድሞ ለ44 ዓመታት ደርግ እና ኢህአዴግ ሲመሩ ይህ የተጠቀሰው ወርቅ ከእይታ ተሰውሮ ተደብቆ የተገኘ አዲስ ግኝት ወይንስ የአገር ቅርስ በመሆኑ ለጥፋት እንዳይጋለጥ ተጠብቆ የቆየ ነው?" የሚለው ምላሽ እንደሚፈልግ ገልጿል።

እናት ፓርቲ በመግለጫው በጠ/ሚኒስትሩ የተጠቀሰው ወርቅ በቤተ መንግሥት አገልግሎት ላይ ይውሉ የነበሩ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ወይንም ለነገሥታቱ ከውጭ አገራት መንግሥታት የተበረከቱ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ከሆኑ እነዚህ ወርቅ ተብለው በወርቅ ዋጋ የሚገመቱና ተመዝግበው በብሔራዊ ባንክ የሚቀመጡ ባንኩም አግባብነት አለው ባለው ጊዜ የሚሸጠው ንብረት ሊሆኑ ከቶውንም አይችሉም ብሏል።

ይህን መሰል የአገር ቅርስ ወደ ተራ ወርቅነት ተለውጦ መልኩን እንዲቀይርና በወርቅም ሆነ በሌላ መልኩ ተሸጦ ወደ ገንዘብ የሚለወጥ ከሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት በአጠቃላይና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን በተለይ የጋራ ተጠያቂነት እንደሚጠብቃቸው በመረዳት ከዚህ መሰል የጥፋት ሥራ እንዲታቀቡ እናት ፓርቲ በጽኑ ያሳስባል በማለት መግለጫውን አጠቃሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
በኦሮሚያ ክልል የተካሄዱት ሰላማዊ ሰልፎች 'በመንግስት የተመቻቹ ናቸው መባሉን' የክልሉ መንግስት አስተባበለ‼️

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች ትናንት ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ/ም የተካሄዱት የሰላም ጥሪ ሰልፎች “በመንግስት የተመቻቹ ናቸው” መባሉን የክልሉ መንግስት “ከእውነት የራቀ” ሲል አስተባበለ።የኦሮሚያ ክልል መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ “ህዝቡ ሰላምን ከመጠማቱ የተነሳ የወጣውን ሰላማዊ ሰልፍ በመንግስት አስተባባሪነት እንደተካሄደ ለማሳየት መሞከር ከእውነታ የራቀና የህዝቡን ቁስል በእንጨት መንካት እንደሆነ የሚታሰብ ነው” ብሏል።

መግለጫው የወጣው በክልሉ የተካሄደውን ሰልፍ አስመልክቶ ከመንግስት ጋር ለአመታት የትጥቅ ግጭት በማካሄድ ላይ ያለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና እንደ ጀዋር መሐመድ ያሉ ፖለቲከኞች በመንግስት ላይ ትችት መሰንዘራቸውን ነው።

ፖለቲከኛው ጀዋር መሐመድ በፌስቡት ትስስር ገጻቸው “መንግስት በአንድ በኩል ጉዳዩን የያዙ ሀገሮች ለሶስተኛ ዙር የሰላም ንግግር የሚያደርጉትን ውትወታ ባለመቀበል፤ በሌላ በኩል ምስኪኑን ህዝብ ወደ ፀኃይ በማውጣት ማስወትወት ትክክል አይደለም” ብለዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለሥራ ጉብኝት ባሕር ዳር ከተማ ገቡ‼️

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለሥራ ጉብኝት ባሕር ዳር ገብተዋል።

ፊልድ ማርሻሉ ባሕር ዳር ሲገቡ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ ሌሎችም የክልሉ እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ መሪዎች እና ነዋሪዎችም ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በባሕር ዳር ቆይታቸው በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በተለይም የክልሉን ሕዝብ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ውይይቶችን ያደርጋሉ።

ከዚህ በተጨማሪም በባሕር ዳር ከተማ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው እንደሚመለከቱ ይጠበቃል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሕዝባዊ ሰልፎች ተካሄዱ‼️

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሰላምን ለማፅናት ያለሙ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።

ሕዝባዊ ስልፉ በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ቄለም ወለጋ እና የአርሲ ዞኖች እየተደረገ ሲሆን፤ በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የሰልፉ ተሳታፊዎች 'ሰላምን ለማጽናት የበኩላችንን እንወጣለን'፣ 'በሰላም እጦት ምክንያት የህዝቡ ስቃይ ሊቆም ይገባል'፣ 'ወደ ሰላም መመለስ መሰልጠን ነው' የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን ማስተላለፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
አቶ ጃዋር መሀመድ ስለ አፈሳው የተናገሩት‼️

ካለፈው አመት ጀምሮ በኢትዮጵያ በታጣቂ ሃይሎች የሚፈጸመው የአፈናና የአፈና ቀውስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። እነዚህ ወንጀሎች ብዙውን ጊዜ መንግሥታዊ ባልሆኑ አካላት የሚፈጸሙ ቢሆንም፣ የመንግሥት ኃይሎች ከተለያዩ ታጣቂዎች ጋር በመሰባጠር ትርፉን በመካፈል ላይ መሆናቸውን ዘገባዎች ጠቁመዋል።

ይባስ ብሎ ደግሞ አሳሳቢ አዝማሚያ ታይቷል፡ የመንግስት አካላቶች አሁን ለብር ተብሎ የሚፈጸመውን አፈና በግልፅ እያረጋገጡ ነው። እየተካሄደ ባለው የእርስ በርስ ጦርነት፣ መንግሥት ወታደራዊ ግዳጁን ለመሙላት እየታመነ ነው። መጀመሪያ ላይ ቀዳሚ ኢላማው ያልደረሰው ወጣት፣ በተለይም ከቀያቸው ርቀው የሚሰሩ የቀን ሰራተኞች ነበሩ። ይሁን እንጂ ትኩረቱ በቅርቡ ከሀብታም ቤተሰቦች ወደ ወጣቶች ተዘዋውሯል.

የአካባቢው የጸጥታ ባለስልጣናት ወጣቶችን ከትምህርት ቤት ወይም ከማህበራዊ ስፍራዎች ሲመለሱ እያሰሩ ወደ ጊዜያዊ እስር ቤቶች በግዳጅ እያጓጉዟቸው መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የተያዙት ወጣቶች ወደ ማሰልጠኛ ካምፖች መጓጓዝን በመጠባበቅ ላይ እያሉ፣ ደላሎች ወደ ቤተሰቦቻቸው በመቅረብ ከፍተኛ ክፍያ እንዲከፍሉ ልጆቻቸውን ለማስፈታት ያቀርባሉ። እነዚህ ክፍያዎች እንደ ቤተሰቡ ሀብት ከ100,000 እስከ 500,000 ብር ይደርሳል። ባለሥልጣኖች እና ደላሎች የቤተሰብ ገቢ መረጃን ከባንክ እና ከግብር መዝገቦች በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ፣ ይህም የታለመውን የመክፈል አቅም ለመገምገም እና ምን ያህል እንደሚፈልጉ ለመወሰን ያስችላቸዋል። በእጃቸው ያሉት ገንዘብ የሌላቸው ከጓደኞቻቸው ለመበደር ተገድደዋል. ቀጣዩ ተጎጂ ከመሆን በመፍራት ብዙ ወጣቶች ትምህርታቸውን እና ስራቸውን ትተው ተደብቀዋል።

ይህ አፈሳ በሩቅ የገጠር መንደሮች ብቻ የተገደበ አይደለም። በዋና ዋና ከተሞች ያሉ ቤተሰቦች አሁን ዋና ኢላማዎች ሆነዋል። ይህ ከመላው ሀገሪቱ በወጡ ዘገባዎች ላይ የተመሰረተ ብቻ አይደለም - እኔ በግሌ የማውቀው ቤተሰብ ከጥቂት ቀናት በፊት ልጃቸውን ለማስፈታት 300,000 ብር መክፈል ነበረባቸው። የኑሮ ውድነቱ ሊቋቋመው በማይችልበት በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነቱ ምዝበራ ጨካኝነት ነው።

የግዳጅ ግዳጅ መግባቱ ራሱ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው። በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው ነገር አሳዛኝ ነው!

@Esat_tv1
@Esat_tv1
በአዲስ አበባ እና አዳማ የጀመረው አፈሳ እና የገንዘብ ድርድር ወደ ሻሸመኔ እና ሌሎች ከተሞች ተስፋፍቷል‼️

ሻሸመኔ 010 ቀበሌ ስታድየም ዋናው በር ፊት ለፊት ባለው መጋዘን ውስጥ እና 02 ቀበሌ ምክር ቤት ጀርባ (ብሔራዊ ትምህርት ቤት ጎን ባለው አዳራሽ) በርካታ ወጣቶች ታጭቀው እንደሚገኙ የሚደርሱኝ ጥቆማዎች ያሳያሉ።

"ዙሪያ ገባው በሚሊሻ ተከቧል፣ ቤተሰብ አይደለም መጠጋት ለራስም ያሰጋል። ግን ምን እየሆነ ነው ያለው?" ብለው የሚጠይቁት ነዋሪዎች ከመሸ መንቀሳቀስ ከባድ እንደሆነባቸው እና የሚሊሻው አፈሳ ተባብሶ እንደቀጠለ ተናግረዋል።

"ስልክህን ይፈተሻል ብለው መንገድ ላይ ይቀበሉህና ጠዋት ሚሊሻ ቢሮ ና ይላሉ። ስትሔድ ለማነው የሰጠኸው ተብለህ ወንጀለኛው አንተው። መሮናል። እኔም አንድ የኦሮሞ ወጣት ነኝ የታገልኩት ግን ለዚህ አልነበረም" በማለት መልዕክቱን ያደረሰኝ ደግሞ አንድ የከተማው ወጣት ነው።
ŠElias Meseret

@Esat_tv1
@Esat_tv1
Platinum Mass Gainer

ጤናማ የሆነ ክብደት መጨመር ይፈልጋሉ ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን እና የካርቦሃይድሬት ዉቅር ሲሆን  በአንድ  ማንኪያ:-

👉1,250 ካሎሪ
👉 60  ግራም ፕሮቲን
👉 6 G ግራም ግሉታሚን
👉 9 G ግራም ክሬቲን
👉 2 G ግራም ቢሲኤኤ
👉ቪታሚኖችን

👩🏽‍⚕️ የያዘው ይህ የከፍተኛ የፕሮቲን እና ካርቦሃይድሬት ድብልቅ የጡንቻን ብዛት በፍጥነት እና በብቃት ለማጎልበት የሚረዳዎትን በቂ የፕሮቲን ፍጆታ በማረጋገጥ የሰውነትዎን ጂኤች እና ቴስቶስትሮን ደረጃን ለማሳደግ የሚያስፈልግዎት ውህድ ነው።

አድራሻ📍 አዳማ - ፖስታ ቤት ሶሬቲ ህንፃ ፊትለፊት ጀርመን ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር 110

☎️ +251966113766 ☎️
በመርካቶ “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል ነው‼️

🗣አስተዳደሩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በመርካቶ አካባቢ አንዳንድ ነጋዴዎች “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” የሚል መሰረት የሌለው ውዥንብር ውስጥ መግባታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተመልክተናል ሲል አስታወቀ።ውዥንብሩ የመጣው “በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በዚህ ሂደት ውስጥ እንዲያልፉ በሚደረገው ሥራ” ነው ሲል የገለጸው አስተዳደሩ ይህ እንዲስተጓጎል ሆን ተብሎ የተነዛ አሉባልታ ነው ሲል ጠቁሟል።

“በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎችን በመለየት በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱን” ያወሳው አስተዳደሩ “ይሁን እንጂ ይህንን ጥሪ ወደ ጎን በመተው እና ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል የተሰራ ውዥንብር ነው” ብሏል።በውዥንብሮች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ንብረት የሚያሸሹና ሱቅ የሚዘጉ ነጋዴዎች ተገቢነት ከሌለው ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል ያሳሰበው አስተዳደሩ “እንዲሁም አምራች፣ አከፋፋይና ቸርቻሪ ነጋዴዎች ያለደረሰኝ መገበያየት ህገወጥ ተግባር መሆኑን በአግባቡ በመረዳት ወደ ህጋዊ መስመር ሊገቡ ይገባል” ብሏል።

በመርካቶ እየተከናወነ የሚገኘው ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል የንግዱ ማኅበረሰብ ተባባሪ እንዲሆንም አስተዳደሩ ጠይቋል።ከዚህ በፊት ያለደረሰኝ የተገዙ ዕቃዎች ካሉ ሕጉ በሚያዘው መሠረት የማስመዝገብ ሥራ ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው የአስተዳደሩ የከንቲባ ጽ/ቤት በፌስ ቡክ ገጹ ባጋራው መግለጫ አስታውቋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
በአዲስ አበባ ከተማ አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ስራ የሚያሰራ ምግብ ቤት እና ሆቴል የ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ የደንብ ረቂቅ ፀደቀ‼️

ከጉልበት በላይ የሆነ አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ስራ ያሰራ ሆቴል እና መሰል ተቋም እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የቱሪስት አገልግሎት ተቋማት ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ይመር ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ቢሮዉ በአዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀፅ 22 ቁጥር 6-13 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዙሪያ ኢትዮጵያዊ ባህልና እሴት እየተሸረሸረ በመሆኑ የወጣዉ የደንብ ረቂቅ ፀድቋል።በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የገፅታና የውበት አጠባበቅ እንዲሁም የጌጣጌጥ አጠቃቀም ስነ-ስርዓት ላይ ቢሮዉ ያወጣዉ የደንብ ረቂቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት እንዲፀድቅ ተደርጓል።

በረቂቅ ደንቡ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በሆቴሎችና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የሚለብሷቸው አልባሳት እና የሚያደርጓቸው ጌጣጌጦች የኢትዮጵያን ባህል እና እሴት የጠበቁ መሆን እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡እንደዚሁም ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ገንዘብ ቅጣትና ከባድ የሚባል እርምጃ ድረስ በረቂቅ ደንቡ ተጠቅሷል ሲሉ ዳይሬክተሯ ገልፀዉ  እንደ ጥፋት ደረጃዉ የገንዘብ መቀጮዉ ተወስኗል።

በተደነገገዉ ክልከላ መሰረት በደረጃ ሀ፣ አምሳ ሺህ ብር፣በደረጃ ለ ፣ 30 ሺህ ብር፣በደረጃ ሐ ደግሞ  5 ሺህ ብር  ያስቀጣል።በዚህም መሰረት አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ሾል ሲያሰራ የተገኘ የሆቴል ተቋም ሆነ መሰል አገልግሎት ሰጪ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያቀጣ ወ/ሎ ገነት ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴለተቪዥን ተናግረዋል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ ሆኖ ከአንድ በላይ ጥፋቶችን ያጠፋ ተቋም ለእያንዳንዱ ጥፋት አምሳ ሺህ ብር ተደምሮ ይቀጣል ሲሉ ዳይሬክተሯ  ጨምረዉ ተናግረዋል።

የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ እንደዚሁም ከጆሮ ጌጥ ዉጪ በሚታዮ የሰዉነት ክፍሎች ላይ ጌጣጌጦችን አድርጎ መገኘት  የፀደቀዉ ረቂቅ ደንብ ይከለክላል ሲሉ ወ/ሎ ገነት አስረድተዋል፡፡ይህ ደንብ በአዲስ አበባ ያሉ ሆቴልና መሰል ተቋማት ወጥ የሆነ ስርዓት እንዲሰፍን ከማገዙም በላይ ባህልና ወጉን ያልጠበቀ የአለባበስ ስነ-ስርዓትን በመቆጣጠር ኢትዮጵያዊ አለባበስና መስተንግዶ ስርዓትን ለማስከበር እና ባለሙያዎች ከሚደርስባቸዉ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጫናን ለማስቀረት አጋዥ ነዉ ተብሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ከሰሞኑ በስፋት ህዝብን እያስጨነቁ ያሉ፣ ብዙም ትኩረት ግን ያላገኘው የወጣቶች አፈሳ ነው። በአዲስ አበባ እና እንደ አዳማ ባሉ ከተሞች ድርጊቱ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ሚድያዎቻችን ሽፋን እንኳን እየሰጡት አይደለም‼️

የሚገርመው በአዳማ በፋብሪካዎች እና በአዋሳኝ ቦታዎች ባሉ ኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ጭምር ታፍሰው ተወስደው በገንዘብ እየተለቀቁ ነው። በግልፅ እገታ እንዲህ ተጀመረ ማለት ነው?

እስቲ ህዝብ የሚለውን ተመልከቱ:

- "ሰላም ኤሊያስ፣ በአዳማ ወጣቶች ከቤት መውጣት አልቻልንም፣ አፈሳ በሚል ምክንያት መታወቂያ ያለውም የሌለውም በሚሊሻ ይያዝና የቀበሌ አዳራሽ ውስጥ ይታጎራል፣ የኔ ሰፈር አዳማ ቦሌ የሚባለው ቦታ ነው፣ አንድ ጓደኞዬ የግል ዩኒቨርስቲ የሚማር በ 16/02/2017 ቀን 10:00 ሰአት የተያዘ ከተያዘ ዛሬ 14 ኛ ቀኑ ነው። ታፍሰው nafyad ት/ቤት ያለዉ ቀበሌ ገብተው ከቤተሰብ ጋር እንኳን መገናኘት አይቻል፣ ቤተሰብ በዱላ ነው ሚያባሩት ሊጠይቅ የሄደን ሰው ። ብር ያለው 50 ሺህ ብር ከፍሎ ይወጣል፣ እሱም የትኛው ቀበሌ እንደገባክ ከታወቀ ነው፣ ስልክ ይነጠቃል ዛሬም በጠራራ ፀሀይ በማፈስ ላይ ናቸው፣ ሁሉም ነገር በጣም ነው ሚያስጠላው።"

- "ሰላም፣ ባለፈው ወንድሜ በኦሮሚያ ፖሊስ ቡራዩ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አሸዋ መዳ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ገብርኤል ሰፈር ፖልስ ጣቢያ ነበር እዛው አከባቢ በነበረው ስውር ቤት እስከ 1,400 ልጆች ታፍነው ነው ያሉት እና እኔም እግዚአብሔር ረድቶኝ 15,000 ብር ከፍዬ ወንድሜን አስፈትቻለሁ። ካልሆነ ይዘውት እንደምሄዱ ስያስፈራሩኝ ነው ሄጄ ያስፈታሁት። ብዙ ታፍነው ነው ያሉት ቤተሰብ እንኳን የት እንዳሉ የማያውቃቸው እና በደላላ ጥበቃ ትሆናላችሁ ተብለው እና በ10 ቀን ውስጥ 7,000 ብር እንደሚከፈላቸው ተነግሮ ነው የሸወዷቸው እና ደላላው 5 ልጆች ካመጣላቸው 10,000 ብር ይከፍላል።"

- "አዳማ ከአዲስ አበባ በባሰ መታወቂያ ኖረህም አኖረህም በቃ እየታፈስክ ነው የምትወሰደው ። በአሁን ሰዓት ሰዎች ያውም ምንም የስራ እንቅስቃሴ በጠፋበት ጊዜና ኑሮ እንዲህ እንደ እብድ ለየብቻ ማስወራት በጀመረበት ጊዜ ተንቀሳቅሶ የተገኘውን ለቤተሰብ ይዞ ለመግባት የአፈሳው ነገር ከባድ በመሆነ ብዙ ሰው በፍራት ረሃቡን ተጋፍጦ ከቤት ከመውጣት እየታቀበ ነው።"

- "አዳማ ላይ እናቶች ምነው ወንድ ልጅ ባልኖረኝ የሚሉበት ዘመን መቷል መንገድ ላይ የተገኘ ሁሉ እየታፈሰ ነው"

- "እንዴት አደርክ? ጓደኛዬ ወደ ውጭ የሚልከው ምርት አምጥቶ አዳማ ማበጠሪያ እያስበጠረ 10 ሰራተኞችን እዛው ድርጅቱ ውስጥ ያሉትን በአፈሳ ወሰዷቸው ትናንት"

ይሄ ከብዙ በጥቂቱ ነው፣ ፈጣሪ ይሁነን።
ŠElias Meseret

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ኤፍቢአይ በመላው አሜሪካ ለጥቁሮች የተላኩ ዘረኛ የጽሑፍ መልዕክቶች ላይ ምርመራ ጀመረ‼️

በመላው አሜሪካ ለሚገኙ ጥቁሮች የተላኩ ዘረኛ የጽሑፍ መልዕክቶች ላይ ምርመራ መክፈቱን የአሜሪካው የፌደራል የምርመራ ቢሮ አስታወቀ።

የተላኩት የጽሑፍ መልዕክቶች በባርነት ዘመን እንደነበረው “ወደ ማሳ ሄደው ጥጥ ለቅመው ለጌቶቻቸው ሪፖርት” እንዲያደርጉ የሚጠቅስ ነው።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የዩኒቨርስቲ ጥቁር ተማሪዎችን ጨምሮ በአላባማ፣ ሰሜን ካሮላይና፣ ቨርጂኒያ፣ ኒውዮርክ እና ፔንስልቬንያ ግዛቶች ነዋሪ የሆኑ ጥቁሮች እነዚህ የጽሑፍ መልዕክቶች ደርሷቸዋል ተብሏል።

“ኤፍቢአይ ለነዋሪዎች የተላኩትን አጸያፊ እና ዘረኛ የጽሑፍ መልዕክቶችን ያውቃል እናም በጉዳዩ ላይ ከፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ከሌሎች የፌደራል ባለስልጣናት ጋር እየመከረ ነው” ብሏል የፌደራል ምርመራ ቢሮው
የጽሑፍ መልዕክቶቹ መላክ የጀመሩት አሜሪካ ካደረገችው ብሄራዊ ምርጫ ማግስት እንደሆነ ይታመናል።

አንዳንድ መልዕክቶች የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ቡድንን ቢጠቅስም ቡድኑ በበኩሉ ንክኪ የለኝም ሲል ውድቅ አድርጓል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
በሆላንድ እስራዔላውያንን ኢላማ ባደረገው ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ‼️

እንዲሁም በድርጊቱ የተጠረጠሩ 62 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአምስተርዳም ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የእስራዔሉ ማካቢ እግር ኳስ ቡድን ከሆላንዱ አያክስ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ለድጋፍ የሄዱ እስራዔላውያን በአምስተርዳም ከሚገኙ ፍልስጤማውያን ጋር ግጭት ውስጥ ገብተዋል።

የእስራዔል መንግስት ዜጎቹን ለማምጣት ሁለት የጭነት (cargo) አውሮፕላን ወደሆላንድ መላኩ ተዘግቧል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
Telegram Center
Telegram Center
Канал