Смотреть в Telegram
በኦሮሚያ ክልል የተካሄዱት ሰላማዊ ሰልፎች 'በመንግስት የተመቻቹ ናቸው መባሉን' የክልሉ መንግስት አስተባበለ‼️ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች ትናንት ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ/ም የተካሄዱት የሰላም ጥሪ ሰልፎች “በመንግስት የተመቻቹ ናቸው” መባሉን የክልሉ መንግስት “ከእውነት የራቀ” ሲል አስተባበለ።የኦሮሚያ ክልል መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ “ህዝቡ ሰላምን ከመጠማቱ የተነሳ የወጣውን ሰላማዊ ሰልፍ በመንግስት አስተባባሪነት እንደተካሄደ ለማሳየት መሞከር ከእውነታ የራቀና የህዝቡን ቁስል በእንጨት መንካት እንደሆነ የሚታሰብ ነው” ብሏል። መግለጫው የወጣው በክልሉ የተካሄደውን ሰልፍ አስመልክቶ ከመንግስት ጋር ለአመታት የትጥቅ ግጭት በማካሄድ ላይ ያለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና እንደ ጀዋር መሐመድ ያሉ ፖለቲከኞች በመንግስት ላይ ትችት መሰንዘራቸውን ነው። ፖለቲከኛው ጀዋር መሐመድ በፌስቡት ትስስር ገጻቸው “መንግስት በአንድ በኩል ጉዳዩን የያዙ ሀገሮች ለሶስተኛ ዙር የሰላም ንግግር የሚያደርጉትን ውትወታ ባለመቀበል፤ በሌላ በኩል ምስኪኑን ህዝብ ወደ ፀኃይ በማውጣት ማስወትወት ትክክል አይደለም” ብለዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Telegram Center
Telegram Center
Канал