Смотреть в Telegram
ጥቅም አልባ ነው። ለፍቅረኛ ወይም ለትዳር አጋር የሚኖር አክብሮት ጥልቅና ሩቅ መሆን አለበት። ከልብ የመነጨ ብቻ ሳይሆን ከነፍስም የተጨለፈ መሆን አለበት።ሚስት ለባሏ ሚስት ብቻ አይደለችም..የሴት ጓደኛ…የእናት ምትክ ዘመድ ጭምር መሆን አለባት..ባልም ለሚስቱ ወንድ ጓደኛ..ከዛም አልፎ የአባት ምትክ ዘመድ መሆን አለበት፡፡የማወራው ግልፅ ነው አይደል?›› ‹‹አዎ ..በጣም ግልፅ ነው..ቀጥል›› ትንፋሽ ወስዶ ከንፈሩን በምራቁ አረጠበና ንግግሩን ካቆመበት ቀጠለ‹‹…ከቤት ወጥታችሁ ስትለያዩ የሚኖር ሽኝት እና ከውጭ ውላችሁ ስትመለሱ እርስ በርስ የሚኖር የሞቀ አቀበል በጣም ወሳኝ ኩነት ነው።ተሳሳሞ ደህና ዋል..ደህና ዋይ ተባብሎ መለያየት እና ሲገናኙ እንዴት ዋልሽ…?እንዴት ዋልክ? ተባብሎ በናፍቆት መሳሳም በመሀከል ያለን ግንኙነት ያደረጃል ፍቅርም ግለቱን ጠብቆ እንዲጓዝ ያግዛል።በመጨረሻው ሚቻላችሁ ከሆነ እቤት ከገባችሁ  በኃላ  ለተወሰነ  ሰዓት  ስልክ  የሚጠፋበት  እና  ቲቨ  የሚዘጋበት  ልዩ የሆነ የቤተሠብ የጋራ የመጫወቻና የመወያያ ሰአት ቢኖር እንደቤተሠብ ለሚኖር መስተጋብር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል። ‹እና ሌላው ልጃችሁ ላይ ያላችሁ አቋም ትልቅ ማስተካከያ ሊደረግበት ይገባል፡፡›› ‹‹ማለት?›› ‹‹በፀሎት ነገሮች ተስተካክለው ወደቤት ስትመለስ..ለምሳሌ ስትወጣ ስትገባ በጋርድ እንድትጠበቅና እንድታጀብ ማድረግ አይገባችሁም..እንደማንኛውም ሰው በነፃነት ከፈለገችው ሰው ጋር ወጥታ ከፈለገችው ጋር የመመለስ መብት ሊኖራት ይገባል፡፡›› ‹‹ሰለሞን እዚህ ላይ አንድ ያልገባህ ነገር አለ…እኔ እኮ ልጄን በጋርድ ማስጠብቀው ወድጄ አይደለም…..ልጄ ልብ በሽተኛ ነኝ..የልብ ንቅለ ተከላ ተደርጎላታል …በጣም ጥንቃቄ የምትፈልግ ልጅ ነች..ድንገት መንገድ ላይ ወድቃ አጉል እንዳትሆንብኝ ስለምሰጋ ነው ዘወትር ሰዎች በዙሪያዋ እንዲሆኑ የማደርገው፡፡››ሲሉ ተቃውሞቸውን ያሰሙት አቶ ኃይለልኡል ናቸው ‹‹ቢሆንም ለዛ መፍትሄው ያ አይደለም….ይሄ የልጅቷን ነፃነት ከመንፈጉም በላይ በራስ የመተማመን ችሎታዋን በጣም ይጎዳዋል…በየሄደችበት በሰው መጠበቅ የመታፈን ስሜት እንዲሰማት ነው የሚያደርጋት፣እና የእዛ ውጤት ደግሞ እንዲህ አሁን እንዳደረገችው ራሷን ነፃ ለማውጣት አላስፈላጊ ጣጣ ውስጥ እንድትገባ ትገደዳለች›› ‹‹ትክክል ልትሆን ትችላለህ …ግን ያው ነፃ ትሁን… ብቻዋን ትንቀሳቀስ ብዬ ከፈቀድኩላት አንዳንድ አላስፈላጊ ቦታዎች ትሄድና የማይሆን ነገር ትሰራለች፡፡›› ‹‹ለምሳሌ የት?›› ‹‹ይሄውልህ የልብ ንቅለ ተከላ ሲደረግላት ልብ የሰጠቻት ልጅ ቤተሰቦች እዚሁ አዲስ አበባ አቃቂ አካባቢ ነው የሚኖሩት ..ልጄ አሁን አሁን ተወች እንጂ በፊት ሰሞን ቀንና ሌት እዛ ካልወሰድከኝ እያለች ታስቸግረኝ ነበር፣..እኛ ደግሞ ከልጅቷ አባት ጋር ስንስማማ በምንም አይነት ከእኛ በአካል መገናኘት እንደማይፈልጉ ነው ያነገሩን..እሷ ቤታቸው ሄዳ ቢያገኟት ልጃቸውን ስልምታስታውሳቸው ሀዘናቸውን ክፉኛ ትቀሰቅሳባቸዋለች.. እንደዛ አይነት ውለታ የዋሉልኝን ሰውዬ ደግሞ የማይፈልጉትን ነገር ማድረግ ላሳዝናቸው አልፈልግም..አንድ ለዛ ነው የማስጠብቃት››ንግግራቸውን እየተናገሩ ሳለ የሆነ እስከዛሬ ያላሰብት ገራሚ ሀሳብ በአእምሯቸው ብልጭ አለ….እንዴት እሰከዛሬ ትዝ ሊላቸው እንዳልቻለ ግራ ገባቸው‹‹ልጄ እነሱ ጋር ሄዳ ቢሆንስ?››ሀሳቡን በውስጣቸው አፍነው ያዙት፡፡ ‹‹የልጃችሁን ደስተኝነትና ሳቅ የምትፈልጉ ከሆነ ለችግሮች ሁሉ ሌላ መፍትሄ አበጁላቸው..ደግሞ ለበፀሎት በግልፅ ነገሮችን ቢያስረዶት ይገባታል…ብስልና አስተዋይ የ22 ዓመት ወጣት ነች….ይልቅ እናንተ  በመሀከላችሁ ያለውን ችግር ፈታችሁ ሰላም ከሆናችሁና ስትወጣ ስትገባ የሚከታተላት ሰው መመደብ ካቆማችሁ የልጃችሁን ደስታና ሳቅ መመለስ ብቻ ሳይሆን መቼም መልሳችሁ አታጦትም›› ወ.ሮ ስንዱ መለሱ ‹‹እሺ እንዳልክ እናደርጋለን….ኃይሌ እንዲህ ማድረግ ያቅተናል እንዴ?›› ‹‹አረ አያቅተንም..ችግር የለውም ሁሉን ነገር እኔ አስተካክለዋልው..አሁን ከፈቀድክልኝ ወደካማፓኒው አንድ አጭር ስልክ መደወል አለብኝ..ከባድ የስራ ጉዳይ ነበረ ..ምን እንዳደረሱት ልጠይቃቸው፡፡›› ‹‹ችግር  የለም..በቃ  ጨርሰናል..አሁን  ለጥዋት  ጉዙ  እቃችንን  መሸካከፍ  መጀመር እንችላለን፡፡›› ‹‹ጥሩ…››ብለው ቀድመው ከመቀመጫቸው ተነሱና  ወደክፍላቸው በመሄድ ስልካቸውን ካስቀመጡበት አንስትው በጀርባ በኩል ባለው በር ከቤት ወጡ….  ስልክ ደወሉ… ‹‹ስማ አቃቂ ለልጄ ልብ የሰጠቻት ልጅ ቤተሰቦችን ታውቃቸወላህ አይደል..?›› ‹‹አዎ አውቀዋለው›› ‹‹አሁኑኑ እዛ ሂድና ቀስ ብለህ ማንም ሳያይህ ወደቤታቸው የሚገባውንና የሚወጣውን ሰው ተከታተል…ከተቻለህ ሁሉንም ፎቶ አንሳ›› ‹‹እሺ….ግን በቀጥታ ምን ለማጣራት ነው የምንፈልገው…?ነገሩን ማወቄ ስራዬን ያቀልልኛል›› ‹‹አዎ….ምን መሰለህ..ለማንም እንዳትናገር..ልጄ ምን አልባት እዛ ቤት ተደብቃ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አድሮብኛል…እና ከአሁኑ ጀምረህ በቃ እስክልህ ደረስ እንዳልኩህ ተከታተለልኝ…እሷን በተመለከተ የሆነ ትንሽም ቢሆን ፍንጭ ካገኘህ ወዲያው አሳውቀኝ፡፡›› ‹‹ስልኩን ዘጉና ኪሳቸው ውስጥ ከተው ወደውስጥ ተመለሱ …ወ.ሮ ስንዱ አልጋቸው ላይ አረፍ ብለው አገኞቸው ፡፡በራፉን ዘጉን የራሳቸውን አልጋ ትተው ወደባለቤታቸው ሄዱና ከጎናቸው ተቀመጡ፡ ይቀጥላል #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ። 👇Sebscribe YouTube link👇 https://www.youtube.com/@atronose
Telegram Center
Telegram Center
Канал