Смотреть в Telegram
#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #አስራ_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ በፀሎት ግቢው ውስጥ ባለ የዛፍ ጥላ ስር ወንበር አውጥታ ቁጭ ብላለች…ፊራኦል ግንዱን ተደግፎ እሷን በትኩረት እያያት እያወሩ ነው፡፡ ወሬው ስለሟች እህቱ ስለበሬዱ ነው፡፡በእሷ ሞት ምክንያት ምን ያህል እንደተጎዳና የእሱ ብቻ ሳይሆን የቤተሱም ኑሮ እንደተመሰቃቀለ እየነገራት ነው፡፡ ‹‹ሀዘንንም ጨመሮ ሁሉም ነገር ጊዜያዊ መሆኑን አውቀህ ከክስተቶች ጋር እራስን አታጣብቅ…ከነገሮች ጋር እራስህን አስማምተህ ፍሰስ..እናም እራስህን ደስተኛ ለማድረግ ሞክር..ጊዜ የማይፈውሰው ህመም የለም››ብላ ልታፅናናው ሞከረች፡፡ ‹‹ጊዜ ሁሉንም ህመሞች እኩል አይፈውስም….አንዳንድ ህመሞች በዕድሜያችን ልክ ተሰፍረው የተሰጡን ናቸው..አንዳንድ ስብራቷች የዘላለም ናቸው፡፡እህቴ ከሞተች ሁለት አመቷ አልፎ ሶስተኛውን ልናገባድድ ነው…ግን አሁንም ድረስ አባዬ እህህ እንዳለ ነው….እማዬን እደምታያት አይኗን እንዲህ የደከመው ከእድሜ የመጣ ህመም ወይም ጭስ አይደለም…የዘወትር ለቅሶ ነው….አየሽ አንዳንድ ስንጥቆች እንዲህ በቀላሉ ጊዜ ስላለፈ ብቻ አይደፈኑም…›› ‹‹ትክክል ልትሆን ትችላለህ …ግን መሞከሩ አይከፋም…›› ‹‹.በይ አሁን ወጣ ብዬ ልምጣ፡፡›› ‹‹ሩቅ ካልሆነ ለምን እኔንም ይዘኸኝ አትወጣም?›› ‹‹አይ ይሄንን ሻርፕሽን ከላይሽ ላይ ካልጣልሽ ከእኔ ጋር ከእዚህ ጊቢ መውጣት አትችይም..ጓደኞቼ እኮ ያቺ ሊንጃ ዘመድህ እያሉ ፉገራቸውን አልቻልኩትም›› ‹‹እንዲሁ …ከአንቺ ጋር መታየቱ ይደብረኛል አትልም›› ‹‹አይ… ያ እውነት እንዳልሆነ አንቺም ታውቂያለሽ…ለማንኛውም ቀላል ነገር ነው የጠየቅኩሽ…ሻርፕሽን ከላይሽ ላይ አንሺና አብረን እንሂድ›› ‹‹አንተ ባለጣባሳዋ ዘመድህ ከሚሉህ ሊንጃዋ ቢሉህ አይሻልህም?፡፡›› ‹‹አይ ግድ የለም..ባለ ጠባሳዋ ቢሉኝ ይሸለኛል…›› ‹‹እንግዲያው ቀረብህ ሂድ በቃ›› ‹‹አንቺም ቀረብሽ…ቻው››ብሏት ወጣ……ፊራኦል ሆነ ብሎ በአላማ ነው እንደዚህ የሚያደርጋት፡፡በፀሎትን መጠራጠር ከጀመረ ቀናቶች አልፈዋል…የምትለውን አይነት ልጅ እንዳልሆነች ውስጡ እየነገረው ነው….ምን አልባት የተጠራጠረው እውነት ከሆነ ምን እንደሚያደረግ ግራ ገብቷታል….አጋልጦና አሳልፎ ይሰጣታል? ለአባቱ ይናገራል…?ለወላጆቾ አሳውቆ ለሽልማት ያቀረቡትን 5 ሚሊዬን ይቀበላል…?እንደዛ ካደረገ በእርግጠኝነት አባቱን ለዘላለም እንደሚያጣ እርግጠኛ ነው…ማጣት ምን እንደሆነ ደግሞ በእህቱ ሞት በደንብ ስለተማረ አባቱን ደግሞ ካጣ ከዛ በኃላ ሰው እንደማይሆን እርግጠኛ ነው…ብቻ የተወሳሰብ ነገር ውስጥ እንደገባ እርግጠኛ ነው….አንዳንዴ ነገሮችን በጥልቀት ከመቆፈር እራሱን ማገድ ቢችል ይመኛል…ምንም ትሁን ማንም ችላ ብሎ ሊተዋት ይወስንና ውሳኔውን ለረጅም ጊዜ አፅንቶ ማቆየት አይችልም…. ‹‹ውይ በፀሎት….ምን አይነት ልጅ ነሽ?››እንደጀማሪ እብድ ብቻውን መንገድ ላይ እየለፈለፈ እየሄደ ነው፡፡ ከሄደ በኋላ ግን እሷ ከፍተኛ ትካዜ ውስጥ ነው የገባችው፡፡ይሄ ልጅ ሙሉ ፊቷን እንድታሳየው ወጥሮ ይዞታል…አውጥተው አይናገሩ እንጂ የቤቱ ሰው ሁሉ ቀንና ለሊታ ፊቷን ጠቅላላ አልብሶ በአንገቷ ዙሪያ ተጠፍሮ ታስሮ የሚውለውን ሻርፖን ከዛሬ ነገ ለምን አይነሳም? የሚሉ ጥያቄ በውስጣቸው እየተጉላላ እንዳለ እርግጠኛ ነች….ይሄንን ማድረግ አትችልም…ቀኑ ከመድረሱ በፊት እራሷን ማጋለጥና ማንናቷን ማሳወቅ ሁሉን ነገር ነው ትርምስምስ የሚያደርግባት፡፡ከመቀመጫዋ ተነሳችና ከሻንጣዋ ውስጥ ስልኳን በማውጣት ወደጓሮ ሄደች …ወደእሷ ሰው ከመጣ በግልጽ ለማየት የሚቻላትን ቦታ መርጣ ተቀመጠችና የጠፋውን ስልክ አበራችው…..ሰሎሞን ጋር ደወለች፡፡ ‹‹እሺ እንዴት ነህ?›› ‹‹ሰላም ነኝ..አንቺ ደህና ነሽ….ከአሁን አሁን በደወለች እያልኩ በማስብበት ጊዜ ነው የደወለሽው›› ‹‹ምነው አዲስ ነገር አለ?›› ‹‹አዎ …ዛሬ አባትሽ ቤት አስጠርተውኝ ነበር›› ‹‹አትለኝም!! ታዲያ እንዴት ሆነልህ?›› ‹‹ሁሉ ነገር አንቺ እዳልሽው ነው የሆነው…ስለእኔ በድንብ ሲያጠኑ ነበር የከረሙት..የስልክ ልውውጣችንንም አግኝተው አዳምጠውታል…..በአጠቃላይ እውነቱን እንደተናገርኩ ተረድተዋል›› ‹‹እና መጨረሻው ምን ሆነ?››በጉጉት ጠየቀች ‹‹ምን ይሆናል..?ያው አሁን ቁጭ ብዬ ዝርዝር እቅድ እያወጣሁ ነው….ሁለቱም ነገሮችን መስመር ለማስዝ ያልኳቸውን እንደሚያደርጉ ውሳኔያቸውን አሳውቀውኛል፡፡›› ‹‹በጣም ደስ ይላል….በዚህ ፍጥነት ይስማማሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር›› ‹‹እኔም ከአንቺ በላይ ፈርቼ ነበር…ግን አንቺን በጣም ስለሚወዱሽ ምንም ምርጫ የላቸውም…እንደተረዳሁት ከሆነ ሁለቱም ጋብቻቸውን ስለማዳንና ፍቅራቸውን ስለማደስ ደንታም የላቸውም…ግን ደግሞ በምንም ብለው በምንም አንቺን መልሰው እጃቸው ለማሰገባት ከልብ ይፈልጋሉ..ለዛ ነው በፍጥነት የተስማሙት፡፡›› ‹‹አዎ ትክክል ነህ…እሷን ለማግኘት እርስ በርስ ተገዳደሉ ብተላቸው በተሻለ ቀሏቸው አሁን ከፈጠኑት በላይ ፈጥነው ያደርጉት ነበር፡፡›› ‹‹እንዴ ..አንቺ ደግሞ አጋነንሺው…እርስ በርስ ከተገዳደሉ እንዴት ብለው ነው አንቺን የሚያገኙሽ…ለማንኛውም ስራው ስለተጀመረ ስልክሽን ባትዘጊው ጥሩ ነው…ምክንያቱም ስለእነሱ አነሱን ጠይቄ ማወቅ የማልችለውን መረጃ አንቺ ነሽ ልትነግሪኝ የምትችይው…ለዛ ደግሞ የግድ በፈለኩሽ ግዜ ማግኘት አለብኝ፡፡›› ‹‹በስልኬ ተከታትለው ከደረሱብኝስ?›› ‹‹ስልኩን አዲስ ቁጥር ነው…ማንም አያውቀውም ያልሺኝ መስሎኝ?›› ‹‹አዎ ትክክል ነህ አዲስ ነው…አሁን ግን አንተ ታውቀዋለህ›› ‹‹እኔ ለእነሱም ሆነ ለሌላ ለማንም ሰው አልሰጥም…ለአንቺ ስል ሳይሆን ለራሴ ስል….ሁለተኛ አሁን አንቺን መፈለጉን እርግፍ አድርገው ትተው ጋብቻቸውን ላይ ሙሉ ትኩረት እንዲያደርጉ አጥብቄ ነግሬያቸዋለሁ እነሱም ሙሉ በሙሉ ተስማምተዋል›› ‹‹እና መቼ ልትጀምሩ ነው?፡፡›› ‹‹እንደነገርሺኝ በፍጥነት ወደቤትሽ መመለስ ትፈልጊያለሽ..ስለዚህ ምንም ጊዜ ማባከን አያስፈልግም…ነገ ስራ እንጀምራለን…ለሚቀጥሉት 15 ቀን ቢሾፍቱ ወዳለው ቤታችሁ እንሄዳለን ፡፡ከዛ በኋላ ደግሞ ውጤቱን እናይና ወደአንዱ ጋር እንሄዳለን፡፡;; ‹‹እንዴ ሁለቱም ለመሄድ ተስማሙ›› ‹‹አዎ…በደንብ ተስማምተዋል..ነገ ሶስት ሰዓት አዲስአበባን ለቀን እንወጣለን›› ‹‹ይገርማል….በዚህ ፍጥነት ከከተማው ይዘኸቸው ትወጣለህ ብዬ አላሰብኩም ነበር›› ‹‹አየሽ ነገሩ ለአመታት የተከማቸና ስር የሰደደ ስለሆነ …..ሙሉ ትኩረት ይፈልጋል….አዲስአባባ ተቀምጦ ደግሞ በሙሉ ትኩረት እንዲህ አይነት ነገር ለመከወን ምቹ አይደለም….ለዛ ነው ከከተማው ላርቃቸው የፈለኩት›› ‹‹በጣም እያስደስትከኝ ነው…›› ‹‹ተይ እንጂ….ገና ምኑም ሳይያዝ ምስጋና ከጀመርሽ በኋላ ጥሩ አይመጣም›› ‹‹አያያዝህን አየሁት …እንደምታሳከው በጣም ነው ምተማመንብህ›› ‹‹አመሰግናለሁ››› ‹‹እሺ.. በቃ ቻው›› ‹‹ቆይ…የስልኩን ነገር ምን አልሺኝ?›› ‹‹እሺ…አልዘጋውም…ግን ቀጥታ አትደውልልኝ….ለማውራት ስትፈልግ መልእክት ላክልኝ..ከዛ ሁኔታዎችን አመቻችቼ በተቻለኝ ፍጥነት ደውልልሀለው›› ‹‹ተስማምተናል..በይ ቻው›› ‹‹ስልኩ ተዘጋ….በጣም ደስ አላት…ነገሮች ሁሉ ባሰበቻው መንገድ እንዲህ መስመር ስለያዙላት ወደላይ አንጋጣ ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡
Telegram Center
Telegram Center
Канал