View in Telegram
ሕብረት ባንክ የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት የገበያ ቅስቀሳ መርኃ-ግብር አስጀመረ ሕብረት ባንክ ለክቡራን ደንበኞቹ «በሕብረት ወደ ከፍታ» ( “step it up together” ) በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 27 እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ የሚቆይ የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት የገበያ ቅስቀሳ መርኃ-ግብር አስጀምሯል ፡፡ የገበያ ቅስቀሳ መርኃ-ግብሩ ዋና አላማ ባንኩ የሚሰጣቸውን የተቀማጭ ሂሳብ አገልግሎቶች ለማስተዋወቅና የደንበኞችን ቁጥር የበለጠ ለማሳደግ ብሎም የባንኩን የተቀማጭ ሂሳብ ከፍ ማድረግ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ይህንኑ ለማሳካት ባንኩ ወለድ አልባ የባንክ አገልግሎቶችን ጨምሮ የተለያዩ ልዩ ወለድ እና ጥቅም የሚያስገኙ የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎቶችን አዘጋጅቶ ለደንበኞች አቅርቧል፡፡ የሕብረት ባንክ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ጽጌረዳ ተስፋዬ ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ/ም በሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ሕብር ታወር ቅርንጫፍ ተገኝተው የገበያ ቅስቀሳውን መጀመር በይፋ ያበሰሩ ሲሆን የባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራር አባላትም ተሳትፈውበታል፡፡ ሕብረት ባንክ በሕብረት እንደግ! 📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡ 🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ https://t.center/HibretBanket 🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡
Telegram Center
Telegram Center
Channel