View in Telegram
በመርካቶ “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል ነው‼️ 🗣አስተዳደሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በመርካቶ አካባቢ አንዳንድ ነጋዴዎች “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” የሚል መሰረት የሌለው ውዥንብር ውስጥ መግባታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተመልክተናል ሲል አስታወቀ።ውዥንብሩ የመጣው “በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በዚህ ሂደት ውስጥ እንዲያልፉ በሚደረገው ሥራ” ነው ሲል የገለጸው አስተዳደሩ ይህ እንዲስተጓጎል ሆን ተብሎ የተነዛ አሉባልታ ነው ሲል ጠቁሟል። “በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎችን በመለየት በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱን” ያወሳው አስተዳደሩ “ይሁን እንጂ ይህንን ጥሪ ወደ ጎን በመተው እና ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል የተሰራ ውዥንብር ነው” ብሏል።በውዥንብሮች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ንብረት የሚያሸሹና ሱቅ የሚዘጉ ነጋዴዎች ተገቢነት ከሌለው ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል ያሳሰበው አስተዳደሩ “እንዲሁም አምራች፣ አከፋፋይና ቸርቻሪ ነጋዴዎች ያለደረሰኝ መገበያየት ህገወጥ ተግባር መሆኑን በአግባቡ በመረዳት ወደ ህጋዊ መስመር ሊገቡ ይገባል” ብሏል። በመርካቶ እየተከናወነ የሚገኘው ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል የንግዱ ማኅበረሰብ ተባባሪ እንዲሆንም አስተዳደሩ ጠይቋል።ከዚህ በፊት ያለደረሰኝ የተገዙ ዕቃዎች ካሉ ሕጉ በሚያዘው መሠረት የማስመዝገብ ሥራ ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው የአስተዳደሩ የከንቲባ ጽ/ቤት በፌስ ቡክ ገጹ ባጋራው መግለጫ አስታውቋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Telegram Center
Telegram Center
Channel