View in Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ስራ የሚያሰራ ምግብ ቤት እና ሆቴል የ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ የደንብ ረቂቅ ፀደቀ‼️ ከጉልበት በላይ የሆነ አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ስራ ያሰራ ሆቴል እና መሰል ተቋም እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡ በቢሮው የቱሪስት አገልግሎት ተቋማት ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ይመር ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ቢሮዉ በአዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀፅ 22 ቁጥር 6-13 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዙሪያ ኢትዮጵያዊ ባህልና እሴት እየተሸረሸረ በመሆኑ የወጣዉ የደንብ ረቂቅ ፀድቋል።በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የገፅታና የውበት አጠባበቅ እንዲሁም የጌጣጌጥ አጠቃቀም ስነ-ስርዓት ላይ ቢሮዉ ያወጣዉ የደንብ ረቂቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት እንዲፀድቅ ተደርጓል። በረቂቅ ደንቡ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በሆቴሎችና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የሚለብሷቸው አልባሳት እና የሚያደርጓቸው ጌጣጌጦች የኢትዮጵያን ባህል እና እሴት የጠበቁ መሆን እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡እንደዚሁም ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ገንዘብ ቅጣትና ከባድ የሚባል እርምጃ ድረስ በረቂቅ ደንቡ ተጠቅሷል ሲሉ ዳይሬክተሯ ገልፀዉ  እንደ ጥፋት ደረጃዉ የገንዘብ መቀጮዉ ተወስኗል። በተደነገገዉ ክልከላ መሰረት በደረጃ ሀ፣ አምሳ ሺህ ብር፣በደረጃ ለ ፣ 30 ሺህ ብር፣በደረጃ ሐ ደግሞ  5 ሺህ ብር  ያስቀጣል።በዚህም መሰረት አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ስራ ሲያሰራ የተገኘ የሆቴል ተቋም ሆነ መሰል አገልግሎት ሰጪ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያቀጣ ወ/ሮ ገነት ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴለተቪዥን ተናግረዋል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ ሆኖ ከአንድ በላይ ጥፋቶችን ያጠፋ ተቋም ለእያንዳንዱ ጥፋት አምሳ ሺህ ብር ተደምሮ ይቀጣል ሲሉ ዳይሬክተሯ  ጨምረዉ ተናግረዋል። የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ እንደዚሁም ከጆሮ ጌጥ ዉጪ በሚታዮ የሰዉነት ክፍሎች ላይ ጌጣጌጦችን አድርጎ መገኘት  የፀደቀዉ ረቂቅ ደንብ ይከለክላል ሲሉ ወ/ሮ ገነት አስረድተዋል፡፡ይህ ደንብ በአዲስ አበባ ያሉ ሆቴልና መሰል ተቋማት ወጥ የሆነ ስርዓት እንዲሰፍን ከማገዙም በላይ ባህልና ወጉን ያልጠበቀ የአለባበስ ስነ-ስርዓትን በመቆጣጠር ኢትዮጵያዊ አለባበስና መስተንግዶ ስርዓትን ለማስከበር እና ባለሙያዎች ከሚደርስባቸዉ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጫናን ለማስቀረት አጋዥ ነዉ ተብሏል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Telegram Center
Telegram Center
Channel