View in Telegram
ከሰሞኑ በስፋት ህዝብን እያስጨነቁ ያሉ፣ ብዙም ትኩረት ግን ያላገኘው የወጣቶች አፈሳ ነው። በአዲስ አበባ እና እንደ አዳማ ባሉ ከተሞች ድርጊቱ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ሚድያዎቻችን ሽፋን እንኳን እየሰጡት አይደለም‼️ የሚገርመው በአዳማ በፋብሪካዎች እና በአዋሳኝ ቦታዎች ባሉ ኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ጭምር ታፍሰው ተወስደው በገንዘብ እየተለቀቁ ነው። በግልፅ እገታ እንዲህ ተጀመረ ማለት ነው? እስቲ ህዝብ የሚለውን ተመልከቱ: - "ሰላም ኤሊያስ፣ በአዳማ ወጣቶች ከቤት መውጣት አልቻልንም፣ አፈሳ በሚል ምክንያት መታወቂያ ያለውም የሌለውም በሚሊሻ ይያዝና የቀበሌ አዳራሽ ውስጥ ይታጎራል፣ የኔ ሰፈር አዳማ ቦሌ የሚባለው ቦታ ነው፣ አንድ ጓደኞዬ የግል ዩኒቨርስቲ የሚማር በ 16/02/2017 ቀን 10:00 ሰአት የተያዘ ከተያዘ ዛሬ 14 ኛ ቀኑ ነው። ታፍሰው nafyad ት/ቤት ያለዉ ቀበሌ ገብተው ከቤተሰብ ጋር እንኳን መገናኘት አይቻል፣ ቤተሰብ በዱላ ነው ሚያባሩት ሊጠይቅ የሄደን ሰው ። ብር ያለው 50 ሺህ ብር ከፍሎ ይወጣል፣ እሱም የትኛው ቀበሌ እንደገባክ ከታወቀ ነው፣ ስልክ ይነጠቃል ዛሬም በጠራራ ፀሀይ በማፈስ ላይ ናቸው፣ ሁሉም ነገር በጣም ነው ሚያስጠላው።" - "ሰላም፣ ባለፈው ወንድሜ በኦሮሚያ ፖሊስ ቡራዩ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አሸዋ መዳ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ገብርኤል ሰፈር ፖልስ ጣቢያ ነበር እዛው አከባቢ በነበረው ስውር ቤት እስከ 1,400 ልጆች ታፍነው ነው ያሉት እና እኔም እግዚአብሔር ረድቶኝ 15,000 ብር ከፍዬ ወንድሜን አስፈትቻለሁ። ካልሆነ ይዘውት እንደምሄዱ ስያስፈራሩኝ ነው ሄጄ ያስፈታሁት። ብዙ ታፍነው ነው ያሉት ቤተሰብ እንኳን የት እንዳሉ የማያውቃቸው እና በደላላ ጥበቃ ትሆናላችሁ ተብለው እና በ10 ቀን ውስጥ 7,000 ብር እንደሚከፈላቸው ተነግሮ ነው የሸወዷቸው እና ደላላው 5 ልጆች ካመጣላቸው 10,000 ብር ይከፍላል።" - "አዳማ ከአዲስ አበባ በባሰ መታወቂያ ኖረህም አኖረህም በቃ እየታፈስክ ነው የምትወሰደው ። በአሁን ሰዓት ሰዎች ያውም ምንም የስራ እንቅስቃሴ በጠፋበት ጊዜና ኑሮ እንዲህ እንደ እብድ ለየብቻ ማስወራት በጀመረበት ጊዜ ተንቀሳቅሶ የተገኘውን ለቤተሰብ ይዞ ለመግባት የአፈሳው ነገር ከባድ በመሆነ ብዙ ሰው በፍራት ረሃቡን ተጋፍጦ ከቤት ከመውጣት እየታቀበ ነው።" - "አዳማ ላይ እናቶች ምነው ወንድ ልጅ ባልኖረኝ የሚሉበት ዘመን መቷል መንገድ ላይ የተገኘ ሁሉ እየታፈሰ ነው" - "እንዴት አደርክ? ጓደኛዬ ወደ ውጭ የሚልከው ምርት አምጥቶ አዳማ ማበጠሪያ እያስበጠረ 10 ሰራተኞችን እዛው ድርጅቱ ውስጥ ያሉትን በአፈሳ ወሰዷቸው ትናንት" ይሄ ከብዙ በጥቂቱ ነው፣ ፈጣሪ ይሁነን። ©Elias Meseret @Esat_tv1 @Esat_tv1
Telegram Center
Telegram Center
Channel