View in Telegram
አትሮኖስ
#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ዘጠኝ : : #ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ሰሎሞን ሁለቱን ባለትዳሮች ፊት ለፊት አስቀምጦ እያወራ ነው፡፡‹‹የፈለገ ጥረት ብናደርግ ለእያንዳንዱ ብሎን የራሱን ትክክለኛ መፍቻ ካልተጠቀምን ልንፈታው አንችልም!! በህይወታችንም ውስጥ ችግሮች ሲያጋጥሙን ተረጋግተን ለችግሩ ትክክለኛ የመፍትሄ ሀሳብ ማስቀመጥና ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ካልቻልን እንዲሁ ስንባክን እና በችግሩ ውስጥ ስንዳክር ነው የምንኖረው፡፡ይሄንን በስራ አለም በትክክል እየተገበራችሁ ውጤታማ እንደሆናችሁ አውቃለው…በትዳር ህይወታችሁስ?ዋናው ጥያቄ እሱ ነው፡፡›› አቶ ኃይለልኡል ተቀበሉት‹‹ገብቶናል…እንደምንም ብለን በመሀከላችንን የተፈጠረውን ክፍተት በማስወገድ እና ፍቅራችንን መመለስ እንዳለብን በደንብ ተረድተናል…አዎ እንደምታየውም ጥሩ መሻሻል እያሳየን ይመስለኛል፡፡›› ሰለሞን ቀጠለ‹‹ጥሩ ግን ፍቅር ብቻውን በሰላም ለመኖር በቂ አይደለም፡፡በመሀከላችው ምንም አይነት ጥል የሌለ ጥንዶች በመሀከላቸው ፍቅር እንዳለ እርግጠኛ መሆን አይቻልም…እንደዛውም ዘወትር በነጋ በጣባ የሚጣሉና የሚጨቃጨቁ ጥንዶችም በመሀከላቸው ያለው ፍቅር አልቋል ወይም ቀዝቅዞል ማለት አይደለም….ከዛ ይልቅ እንዴት እርስ በርስ እንደሚግባቡ እና አንዱ የአንዱን ፍላጎት እንዴት እንደሚረዳ አልገባቸውም ማለት ነው፡፡ስለዚህ አሁን መልሳችሁ ማደስ የሚገባችሁ ፍቅራችሁን ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ የመግባባት ችሎታችሁንም ጭምር ነው፡፡አንዳችሁ ሌላችሁን በጥልቀት ለመረዳት እስከምን ድረስ ለመጓዝ ትፈቅዳላችሁ?ይሄ ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡›› ወ.ሮ ስንዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገሩ‹‹ትክክል ነህ ልጄ… ለፍቀራችን መበላሸት ዋናው ምክንያት እንደውም እርስ በርስ የመግባባት ችሎታችን ስለተበላሸ ነው….እሱም እኔን እኔም እሱን ለመረዳት ምንም የምናደርገው ጥረት አልነበረም…ሁለታችንም እርስ በርስ እንከን ነበር የምፈላለገው….ያንን በደንብ ተረድቼለው፡፡›› ‹‹አዎ ይሄ ችግር የእናንተ ብቻ ሳይሆን የአብዛኛው ባለትዳር ችግር ነው…አንድ ሰው በፍቅር ሲወድቅ በመጀመሪያ ስለራሱ ምቾና ደስታ እንጂ ስላፈቀረው ሰው ደህንነት አይደለም የሚጨነቀው…ሁለቱም ተጣማሪዎች በጋብቻ ጥምረት ውስጥ ለእነሱ የሚመች ሰፋ ያለ ግዛት ቶሎ ብሎ ለመያዝ ይጣጣራሉ…ሁለቱም ተመሳሳይ ፍላጎት ስላላቸው ፍትጊያ ይፈጠራል…አንዱ የሌለኛውን ድምበር ማለፍ…ይሄኛው የዛኛውን ቀይ መስመር መደፍጠጥ ይጀምራል……ከሁለት አንዱ በፍጥነት ነቅቶ ወደኃላ በመመለስ መረጋጋት ውስጥ ካልገባ ችግሩ መስመር ይስታል፡፡ እኔ 25፡50፡25 የሚል ፕሪንስፕል አለኝ፡፡በትዳር ውስጥ እሷ(ሚስትዬው) እሱ(ባልዬው) እና እነሱ (ባልና ሚስቶቹ)አሉ፡፡እና ስሜታቸው፤ፍላጎታቸው፤የህይወት አላማቸው ወ.ዘ.ተ ተጠቅልሎ መቶ ፐርሰን ቢሰጠው፡፡እሷ የግሏ ፍላጎት በግሏ የሚያስደስታት ነገር፤ መዝናኛ ቦታ፤ጓደኞች፤ 25 ፐርሰንት ትይዛለች….እሱም ለብቻው 25 ፐርሰንት ይይዛል፡፡50 ፐርሰንቱ ግን የጋራቸው ነው፡፡በጋራ የሚያቅዱበት፤በጋራ የሚሰሩበትና የሚለፉበት ቤት መስራት፤ልጆች መውለድና ማሳደግ…ወዘተ፡፡ሁል ግዜ ተሰፍሮ 25፤50፤25 ላይሆን ይችላል፡፡በተለይ ሴቶች ከእነሱ 25ፐርሰንት 10ሩን ወይም 15 ቱን ቆርሰው ለጋራቸው ያውሉታል…ወንዶች ደግሞ ከሞላ ጎደል አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከጋራቸው ላይ ቆረስ አደርገው የእነሱን 25 ፐርሰንት 30 እና 40 አንዳንዴም ከ50 በላይ ያደርሱታል..የዛን ጊዜ የጋብቻው ባላንስ ይናጋል፡፡ምሰሶው መነቃነቅ ይጀምራል..እርማት ካልተደረገለት ጋብቸውን እያከሳ ይሄድና መጨረሻ ያከትምለታል፡፡…የምናገረው ግልፅ ነው አይደል›› ‹‹አዎ..በጣም ግልፅ ነው፡፡›› ‹‹በምሳሌ ይበልጥ ለማስረዳት አንድ ገጠር የምትኖር አክስቴ ከአስር በላይ ባሎች አግብታለች፡፡ግማሹን እነሱ ናቸው የፈቷት ግማሾቹን እራሷ ነች ያደረገችው፡፡ከሁሉም ግን የሳበኝን አንደኛውን ልንገራችሁ፡፡አገባሁት አለች..በጣም ሰላማዊ ..ምንም አይነት ክፉ ነገር ማይናገር…የጠየቅኩትን ሁሉ የሚያሞላልኝ ሰላማዊ ሰው ነበር አለች፡፡በፊት ከለመደቻቸው ተደባባዳቢ እና ተጨቃጫቂ ባሎች ጋር የትኛውም ፀባዩ የሚገጥም አልነበረም፡፡ግን ብዙም ሳይቆይ ሰለቻት….ሁሉ ነገር ዝም እና ጭጭ ያለ ሆነባት…በቃ ግንኙነታቸው ውስጥ ነፍስ አጣችበት ፡፡አንድ ቀን በለሊት ተነሳና በሬዎቹንና ሞፈር ቀንበሩን ይዞ ወደማሳ ወጣ …ሲሄድ ቁርስም አልሰጠችውም..ምሳም ይዛ መሄድ ቢገባትም አልወሰደችለትም..ጭራሽም አልሰራችም…በጣም የባሰው ነገር ደግሞ የቤቱን እቃ ብረትድስት ፤ሰሀን ፤ብርጭቆ አንድም ሳታስቀር ከቤት ጀምራ የቤቱን መግቢያ ደጃፍ…ወለሉን ጠቅላላ አዝረክርካ እና ሞልታ ኩርሲ ላይ ቀጭ ብላ ትጠብቀው ጀመር ፡፡. ከዛ መጣ…ከውጭ ጀምሮ ያዝረከረከችውን እቃ አንድ በአንድ ጎንበስ ብሎ እየለቀመ…‹‹እታዋቡ …ሰላም ነሽ….?ምንም አልሆንሺብኝም አይደል….?››እያለ ሁሉንም እቃ ወደመደርደሪያ መልሶ ስሯ ቁጭ ብሎ በልምምጥ ጭንቅላቷን መዳበስ ጀመረ.. ከዛ ይህቺ አክስቴ ምን ብታደርግ ጥሩ ነው‹‹ ብድግ አለችና ሻንጣዋን ይዛ‹‹እንዴት ቁርስ አላበላሁህ ..ምሳ አለመጣሁልህ….ቤቱን እዲህ አዝረክርኬ ነው የጠበቅኩህ..ምን እስካደርግህ ነው የምትጠብቀው…?ምንም አይነት የወንድነት ወኔ የለህም እንዴ…?ሁለት ሴት አንድ ቤት አይኖርም… ነውር ነው››ብላ ጥላው ወጣች..በዛው ፈታችው ፡፡አያችሁ ትዳር በጣም ውስብስብ ግንኙነት ነው፡፡የበዛ ጭቅጭና ጥል ብቻ ሳይሆን የበዛ ሰላምና ፀጥታም ሊያፈርሰው ይችላል፡፡፡ዋናው በሁሉም ነገር ሚዛን ጠብቆ መጓዝን መልመድ ነው፡፡›› የተወሰነ ትንፋሽ ወሰደና ፊትለፊቱ ካለ የታሸገ ውሀ በማንሳት አንዴ ተጎንጭቶለት ከንፈሩን አረጣጠበና ንግግሩን ቀጠለ፣እነሱም ልክ በቅርብ ፈተና እንደደረሰበት ቸካይ ታማሪ በጥሞናና በትኩረት እየተከታተሉት ነው‹‹አሁን ልብ በሉ፣ ጥረታችን በመካለላችሁ ያላውን ግጭትና ጭቅጭቅ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይደለም..አይ እንደዛማ አይሆንም እናንተ ሰው ናቸው፣ሁለት ሰዎች ደግሞ በአንድ ጣሪያ ስር አብረው እስከኖሩ ድረስ በሆነ ነገር መነጋገራቸውና በነገሩ ላይ የተለያየ ተቃራኒ ሃሳብ ማንፀባረቃቸው አይቀርም…ስለዚህ መነጋገርና መጨቃጨቅ ኖርማል ነው…አሁን ምንድነው ምናደርገው.. በማንኛውም ጉዳይ ላይ አለመግባባት ተከስቶ ስትነጋገሩ በምን መልኩ ነው ኮምንኬት የምታደርጉት..?ነገሩን ማስረዳትና ማሳመን ላይ ነው ትኩረታችሁ ወይስ ያንን ምክንያት አድርጎ በስድብና በዘለፋ ማጥቃትና ልብ መስበር…አያችሁ ትልቁ ችግር መጋጨታችን ሳይሆን በያንዳንዱ ግጭታችን አንዳችን ለሌላቸውን የልብ ቁስለትና የነፍስ ህመም መስጠታችን ነው፡፡ማጥፋት ያለብን እርስ በርስ መወጋጋቱን ነው…አንዳችን ሌላችን ላይ በምንም አይነት ሰበብ የሚያቆስል ነገር ጦር አስበን አይደለም አምልጦን እንኳን መወርወር ለብንም፡፡እርስ በርስ ከፍ ባለ ቃላት በተነጋገራችሁ ቁጥር ደግሞ እየተጣላችሁ መሆኑን አታስቡት..መጣላት ቃሉ እራሱ አሉታዊ ነው፡፡እየተጣላችሁ ሳይሆን በጋለ ስሜት እየተነጋገራችሁ ነው፡፡በቃ እንዲህ ነው ማሰብ ያለባችሁ፡፡እንደዛ ካሰባችሁ ቀጥታ ችግሩ በጋለ ስሜት መነጋገራችን ብቻ ስለሆነ ስሜታችሁን በማረጋጋት ነገሩን ትፈታላችሁ፡፡እየተጣላን ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ግን ጋና ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው ወይም ሽማግሌ ልትፈልጉ ነው፡፡ልብ በሉ ጮክ ብሎ መናጋገር ሁል ጊዜ መጣላት አይደለም አብዛኛውን ጊዜ በጋለ ስሜት
Share
Telegram Center
Channel
Join