View in Telegram
‹‹እስከአሁን ወደእኔ መጥተው የሚያናግሩኝ ከሁለት አንዱ ማለቴ ባልዬው ወይም ሚስትዬው ናቸው….የእናንተ ግን ልጃችሁ ነች ያናገረችኝም የቀጠረችኝም፡፡›› ‹‹አዎ እሱስ ትክክል ነህ›› ‹‹ስለዚህ አሁን ስራችንን ስንጀምር እሷን እያሰብን መሆን አለበት ፡፡በፍቅር የታነፀ ትዳር ውስጥ ያላደጉ ልጆች በመጨረሻ በስነ-ልቦናም ሆነ አካላዊ በሽታ እንደማያጣቸው የተረጋገጠ ነው። ልጅ ስናሳድግ ጥሩ ልብስ ፣ጥሩምግብና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት እንዲያገኙ መጣር ብቻ ሳይሆን የተሞላ ፍቅርም እየመገብን ማሳደግ እንዳለበት እንደወላጅ ግንዛቤው ሊኖረን ይገባል።የመፈቀር እና የመፈለግ ስሜት ማጣት በከፍተኛ ሁኔታ የልጆችን በራስ የመተማመን ችሎታን ከመሸርሸሩም በላይ ለአእምሮ ውጥረትና ድብርትም እንዲዳረጉ ያደርጋቸዋል።ለልጆች በፍቅርና በእንክብካቤ ማደረግ ደስተኛ ሆኖ ለመኖር ብቻ ሳይሆን ጤነኛም ሆኖ ለመኖር በጣም አስፈላጊ ነገር ነው።በወላጆቹ የሚወደድ እና ወላጆቹም የሚወድት ልጆች በጣም ደስተኛ ናቸው።በፍቅር ውስጥ መኖር ጤነኛ ሆኖ ለመኖር እና የበሽታ የመከላከል አቅማችንን ለመጨመር እንደሚያግዝ በሳይንስ የተረጋገጠ ነው።ስለዚህ ልጆቻችን በፍቅር ታንፀው የመፈለግና የመወደድ ስነልቦና ኖሮቸው ማደግ አለባቸው፡፡ለዚህም ወላጆች ሁሉ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው፡፡፡ እንደውም እናንተ እድለኛ ናችሁ፡ ‹‹እድለኛ ናችሁ ስትል?›› ‹‹እንዴ በፀሎት እኮ በጣም የምትገርም ብስልና በቀላሉ የማትሰበር ልጅ ነች፣አብዛኞቹ በእሷ እድሜ ያሉ ልጆች በእንደዚህ አይነት ችግሮች ውስጥ ሲያልፉ ከፍተኛ ድብርት ውስጥ ይገቡና ለተለያዩ ሱሶች ይጋለጣሉ ..ከዛም አልፈው በህይወት ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ይገቡና እራሳቸውን ወደማጥፋት ይሄዳሉ….በፀሎት ግን ያደረገችው ከውጥረቱ ራሷን ዞር አድርጋ እናንተን ለመርዳትና ወደመስመር ለመመለስ መጣር ላይ ነው ያተኮረችው›› ‹‹አዎ እውነትህን ነው …በልጄ ታላቅ ኩራት ተሰምቶኛል….ምንም ጭረት ሳይነካት ወደቤቷ እንድትመለስ ማድረግ ያለብኝን አደርጋለሁ..ማለት ሁለታችንም ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን አይደል ስንዱ?›› ‹‹አዎ ትክክል ነህ…ለዛም አይደል እዚህ የተገኘነው›› ‹‹እንግዲያው ጀመርን …ከአሁን በኃላ የምናወራውና የምንናገረው ሁሉ እየተቀዳ ነው.››.ብሎ አይፓዱን አስተካክሎ ተጫነውና ቦታውን ይዞ ተቀመጠ…›› ለሶስት ሰዓት ቀጠለ…..በመጀመሪያ ወ.ሮ ስንዱ አቶ ኃይለመለኮት ላይ ያላቸውን ቅሬታ እስከአሁን በደሉኝ የሚሉትን ነገር እንዲያወሩና አቶ ኃይለመለኮት ደግሞ ለደቂቃ እንኳን ሳያቆርጡ እንዲሰሙ አደረገ…በቀጣዩ ሰዓት ደግሞ አቶ ኃይለልኡል በተራቸው ሚስታቸው ላይ ያላቸውን ቅሬታ በዝርዝር እንዲናገሩ አደረገ……..ቀጣዩን አንድ ሰዓት ደግሞ እራሱ ሰሎሞን ጥያቄ እየጠየቃቸው ሁለቱም ተራ በተራ እዲመልሱ ተደረገና የጥዋቱ ክፍለጊዜ አለቀና ሶስቱም ተያይዘው ወደሳሎን ሄዱ ..ምሳው በስርአት ተዘጋጅቶ ስለጠበቃችው ሶስቱንም ጠረጴዛውን ከበው ፀጥታ በተጫነው ና እርስ በርስ በተፈራራ በሚመስል ሁኔታ ምሳቸው ተበልጦቶ አለቀ..ብና ተፈልቶ ስለነበረ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ንፋስ እየተቀበሉ ጠጡ ‹‹አሁን ለአንድ ሰዓት ያህል መኝታ ክፍላችሁ ገብታችሁ አረፍ በሉ….ሰዓት ሲደርስ እኔ መጥቼ ቀሰቅሳችኃላው›› እሺ ብለው ሁለቱም ከመቀመጫቸው ተነሱ..ሰለሞን ከኃላ ተከተላቸው….››መኝታ ቤታቸው እንደደረሱ ሊከፍቱ ሲታገሉ‹‹ይቅርታ ሳልነግራችሁ መኝታ ቤታችሁ ተቀይሮል..ተከተሉኝ››ብሎ ቀደማቸው፡፡ ‹‹የማ…? የእኔም ነው የተቀየረው?›› ‹‹አዎ ወ.ሮ ስንዱ….ሁለታችሁም ተከተሉኝ..›› ግራ በማገባት ሁለቱም በዝምታ ከኃላው ተከተሉት …የኮሪደሩ መጨረሻ ላይ ካለው በራፍ ሲደርስ ቆመና ከፈተው….‹‹ግቡ ›› ‹‹ማ እኔ ነኝ እሷ?›› ‹‹ሁለታችሁም›› እርስ በርስ ተያዩ…ቀጥሎ በጋራ እሱ ላይ አፈጠጡበት…አንድ ክፍል ውስጥ አብረው ከተኙ አስር አመት አልፏቸዋል..አሁን በአንዴ እንዴት….?ጉዳዩ ሁለቱንም እኩል ነው ያስበረጋጋቸው፡፡ ጫን ባለ የአዛዥነት ቃና‹‹እባካችሁ ግቡ››አላቸው ምርጫ ስላልነበራቸው አቶ ኃይለልኡል ቀድመው ገቡ…ወ.ሮ ስንዱ ተከተሏቸው….ሁለቱም ጎን ለጎን ቆመው ክፍሉን ዙሪያ ጋባ ቃኙት …ሻንጣቸው ሆነ ጠቅላላ እቃቸው በየቦታው ተቀምጦል…ሁለት አልጋ ማዶ ለማዶ ግድግዳ ተጠግቶ ይታያል…፡፡ ያው ..ሁለት አልጋ አለ …ተነጋገሩና አንዳንደ አንድ ተካፈሉ …በቃ መልካም እረፍት..ሰዓቱ ሲደርስ መጥቼ ቀሰቅሳችኃላው››አለና ከክፍሉ ወጥቶ በራፉን መልሶ ዘግቶላቸው ወደገዛ ክፍሉ ሄደ፡፡ /// የሁለት ሰዓት የረፍት ጊዜ ከሰጣቸው በኃላ በጥዋቱ ጊዜ ባለው ፕሮግራም የቀረጸውን ወደኮምፒተሩ ገለበጠና ይዞ ወደእነሱ ክፍል አመራ…በስሱ ቆረቆረ…ወዲያውን ነበር የተከፈተለት፡፡ ‹‹መጣህ ..?እየጠበቅንህ ነበር›› ‹‹አዎ መጥቻለው›› ‹‹ስንዱ ተነሽ..እንሂድ››አቶ ኃይለልኡል ተናገሩ፡፡ ‹‹አይ ቆይ መሄድ አያስፈልግም ….እዚሁ እናድረግው›› ‹‹ይሻላል ..እሺ ግባ..››ብለው በራፉን ለቀቁለትና ወደውስጥ በመመለስ አልጋቸው ጠርዝ ላይ ተቀመጡ ፡፡ወ.ሮ ስንዱም የራሳቸው አልጋ ላይ እንደተቀመጡ ነው፡፡ ወንበር ሳባና ከሁለቱ መካከል ተቀመጠና ኮምፒተሩን ጠረጳዛ ላይ አስቀመጠው፡፡ ‹‹ይሄውላችሁ በትዳር ውስጥ ችግር መፈጠርና አለመስማማት የእናንተ ብቻ ሳይሆን የሚሊዬን ጥንዶች ችግር ነው..እመኑኝ ያልተስማማንበት ነገር ይህ ነው ያ ነው ብላችሁ ቀኑን ሙሉ ስትዘረዘሩ ብትውሉ የእናንተ ከሌላው ትዳር ውስጥ ከተፈጠረው ችግር የተለየ ሊሆን ይችላል እንጂ የባሰ ግን አይደለም፡፡ስሙኝ አብዛኛውን ጊዜ በትዳር ውስጥ ችግር ሲከሰት በትዳር ውስጥ ችግር የፈጠረውን ነገር ከማየት ይልቅ እራሱ ትዳርን እንደችግር የመውሰድ  አዝማሚያ  ይታያል።ያ  ደግሞ  ከትዳራቸው  ውስጥ  ሾልኮ  ስለመውጣት ስለመፋታት እንዲያስብ ያደርጋቸዋል።እንደሀሳባቸው ትዳራቸውን ፈተው የተሻለ ወዳሉት ወደሌላ ትዳር መሸጋገር ቢችሉም ችግሩም አብሯቸው ነው ወደአዲሱ ትዳራቸው የሚሸጋገረው። መፍትሄው ትዳሩን እንደችግር ወስዶ ያልሆነ ድምዳሜ ላይ ከመድረስ ይልቅ ትዳሩ ውስጥ የተከሰቱ ችግሮች ምን ምን ናቸው ብለው በመለየት እነሱን ለማስወገድ መጣር እና በዛ ሂደት የጋብቻውን ህልውና ማስቀጠል ይበጃል።ምክንያቱም የመኪናህ ጓማ ቢያልቅ ጎማውን ትቀይራለህ እንጂ መኪናዋን ሙሉ በሙሉ አታስወግድም።አይደለም ጎማ ሞተሩ ቢነክስ እንኳን ሞተር አስወርደህ ከእንደገና ተፈቶና ተበታትኖ ችግሩ ተለይቶ ከተወገደ በኃላ መልሶ ይገጣጠምና መኪናው እንደነበረ ይቀጥላል... ጋብቻም እንደዛ ነው የሚደረገው።እና አሁን እያደረግን ያለነው በመሀከላችሁ ያለውን ችግር የመቃቃራችሁን መንሴ መለየት ነው፡፡አሁን በጥዋቱ ክፍለ ጊዜ ሁለታችሁም የተናገራችሁትን እዚህ ኮምፒተር ላይ ከፍትላችኃላው በጋራ አብራችሁ ታዩታላችሁ…ይሄ መልሳችሁ የተናገራችሁትን እንድታዳምጡና የትኛው ትክክል ነው..የትኛው ንግግራችሁ ተጋኗል የሚለውን መልሳችሁ እንድታስበቡበት ይረዳችኃላ…በቃ አሁን ቀጥታ ወደማዳመጡ እንግባ ››አለና ኮምፒተሩን ከፈተና ለ.ወሮ ስንዱ አቀበላት…አቶ ኃይለልኡል ያለምንም ንግግር ከተቀመጠበት የራሱ አልጋ ተነሳና ሄዶ ወ.ሮ ስንዱ አልጋ ላይ ከጎኗቸው ተቀመጠና በኮምፒተር የሚታየውን የራሳቸውን ንግግር ለማደመጥ ዝግጁ ሆነ…ሰለሞን በፀጥታ ከተቀመጠበት ተነሳና ክፍልን ለቆ በራፍን ዘጋላቸውና ወጥቶ ሄደ… ይቀጥላል #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ። 👇Sebscribe
Telegram Center
Telegram Center
Channel