View in Telegram
#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሰባት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ይዘውት የሄዱት ቦታ ከቢሾፍቱ ከተማ በባቦጋያ ሀይቅ አካባቢ ከከተማው ወጣ ብሎ የሚገኝ ቪላ ነው፡፡ይህ ቪላ ቤተሰቡ ከውጥረት ረገብ ለማለት ሲፈልግ የሚገለገልበት ስፋራ ነው፡፡ለአለፉት አንድ አመት ከግማሽ ማንም ዝር ብሎበት አያውቅም ነበር፡፡ሰለሞን ስፍራውን ሲያይ ከውበትም ሆነ ከፀጥታ አንፃር ሲታይ ሙሉ በሙሉ እሱ እንደሚፈልገው አይነት ሆኖ ነው ያገኘው፡፡አንድ ሺ ካሬ ሜትር በላይ የሚሆን ቅፅር ግቢ ነው፡፡መሀከል ላይ ግዙፍና ባለግርማ ሞገስ ጥንታዊ ግን ደግሞ ጥሩ ይዞታ ላይ ያለ ግዙፍ ቪላ ቤት አለበት…ግቢው ውስጥ እድሜ ጠገብ ግዙፍ ባለግርማ ሞገስ የባህር ዛፍና የጥድ ዛፎች ስብስባ ላይ እንደተቀመጠ ታዳሚ እዚህም አዛም ዙሪያውን ተሰራጭተው ይታያሉ…ገና ግቢውስጥ ገብተው እንዳቆሙ የቤት ጠባቂዎች በልና ሚስቶች በፍጥነት መጥታው መኪናዋ አጠገቡ ቆሙ፡፡መኪናዋን ሲነዳ የነበረው እራሱ ሰሎሞን ስለነበረ….ሞተሩን አጠፋና ቀድሞ ወረደ…አቶ ኃይለመለኮትን ወ.ሮ ስንዱም ወረዱና ከጠባቂዎቹ ጋር ሰላምታ መለዋወጥ ጀመሩ…ከዛ ቀጥታ ወደ ቤት ነው የገቡት….ቀድመው ደውለው ስለነበር..እቤቱ ምሉ በሙሉ ፀድቶና የእነሱም መኝታ ክፍል ተዘጋጅቶ ነበር የጠበቃቸው…. ታፈሰ ‹‹ጋሼ ባዘዙኝ መሰረት ሶስት ክፍል ለመኝታ አዘጋጅቼያለው…ይሄው እርሶ እዚህ ግቡ….እትዬ ደግሞ ቀጥሎ ያለው …ወንድም አንተ ደግሞ የፊት ለፊተኛው ክፍል…..ድንገት ስለሆነብን ሁሉንም ነገር ማዘጋጀት አልቻልንም….የጎደለውን ንገሩኝና ከተማ ወጣ ብዬ ገዝቼ አሟላላሁ›› አቶ ሃይለመለኮት ወደሰለሞን እያመለከቱ‹‹ተፈሰ…ይሄውልህ እዚህ 15 ቀን ነው የምንቆየው….በዚህ 15 ቀናት ውስጥ የእኛም ሆነ የአንተ ሀለቃ እሱ ነው….ምንም ነገር ቢያዝህ እሱ ያለውን ነው የምታደርገው…እኛም እንደዛው››ሲሉ መመሪያ አስተላለፉ፡፡ ታፈሰ…የአቶ ኃይለልዕልን ንግግር ከበፊት ቆፍጣና ባህሪያቸው ጋር አልሄድ ስላለው ..ግራ በመጋባት አፍጥጦ ያያቸው ጀመር…እሱ እንደሚየውቀው እኚ ግዙፍ አዛውንት ለሰው ምንም ሊሰጡ ይችላሉ የአዛዥነት ቦታቸውን ግን ፈፅሞ ሸርፈው እንኳን ለሌላ ሰው ይሰጣሉ ብሎ ማመን ይከብደዋል፡፡ ‹‹ታፈሰ ..ሰምተኸኛል…የሁሉ ነገር አዛዣችን እሱ ነው››ደገሙለት፡፡ ‹‹አዎ ..ገባኝ ጌታዬ…እንዳሉት ይደረጋል›› ‹‹አሁን ሁላችንም ወደክፍላችን እንግባና ትንሽ አረፍ እንበል ..አይደል?››ወ.ሮ ስንዱ የሰለሞንን አይኖች በልምምጥ እያዩ ጠየቁ፡፡ ቆይ አንዴ ክፍላችሁን ልይ ብሎ..ለአቶ ኃይለልኡል የተመደበውን ከፍቶ አየው፡፡ቀጥሎ የወ.ሮ ስዱን ከፈተና አየው፡፡‹‹ጥሩ በቃ ግቡና እረፉ›› ሁለቱም ገቡና የየራሳቸውን ክፍል ዘጉ ‹‹አንተም ወደክፍልህ ግባ ጌታዬ..እኔ ደግሞ እቃችሁን ከመኪና ላውርድ›› ‹‹ቆይ አብሬህ ልምጣ››ብሎ ተከተለው፡፡የታፈሰ ባለቤት ለእንግዶቹ ምግብ እያበሰለች ስለነበር ታፈሰ እቃዎቹን ማለት ይዘው የመጡትን አስቤዛ እና ሻንጣዎች ሲያወርድና ወደቤት ሲያስገባ ሰሎሞን አገዘው፡፡እንደጨረሱ፡፡‹‹ተለቅ ያለ ክፍል የለም?››ሲል ጠየቀው፡፡ ‹‹ምን አይነት ክፍል…ማለቴ ለምን የሚሆን?›› ‹‹ለመኝታ ቤት የሚሆን ..ሁለት አልጋ የሚያዘረጋ›› ‹‹ቆይ ..ኮሪደሩ መጨረሻ ላይ ያለው ክፍል ሰፋ ይላል›› ‹‹ማየት እችላለሁ?›› ‹‹አዎ ይቻላል….››ብሎ ይዞት ሄደና ከፈተለት…ሰለሞን ወደውስጥ ዘልቆ ሳይገባ በራፉ ላይ በመቆም አንገቱን ወደውስጥ አስግጎ ተመለከተው….አቦራ የጠጣና ለብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ያልዋለ ቢሆንም የሚፈልገው አይነት ክፍል ነው፡፡›› ‹‹ታፈሰ ይሄንን ክፍል በአስቸኳይ ልታስፀዳልኝ ትችላለህ….?›› ‹‹እችላለሁ..አፀዳዋለው›› ‹‹አይ ብቻህን ይከብድሀል..ሰው ቅጠርና በፍጥነት ወለሉም ግድግዳውም ይፅዳ….ውስጥ ያሉት እቃዎችም ወደሌላ ክፍል ይዘዋወሩ›› ‹‹እሺ›› ተሰናብቶት ንፁህ አየር ሊቀበልና እግረመመንገዱን አካባቢውን ለመቃኘት ወጥቶ ሄደ፡፡ /// በማግስቱ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ ሁለቱንም የማይጣጣሙ ባለትዳሮችን አንድ ክፍል ጎን ለጎን እንዲቀመጡ አደረገና እሱ ከፊት ለፊታቸው ተቀመጠ..ጉሮሮውን አፀዳዳና የመግቢያ ንግግሩን ጀመረ ‹‹በሰዎች መካከል ለተለያየ አለማ ተብለው የሚደረጉ የእርስ በርስ ጉድኝቶችና ቁርኝቶች አሉ፡፡ከነዛ መካከል ግን በጣም ውስብስቡ የጠበቀውና የጠለቀው ግንኙነት በአንድ ወንድ እና ሴት መካከል የሚፈጠር የጋብቻ ጉድኝት ነው፡፡በጋብቻ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ሁሉ ጊዜ ቀላል የተባለ መንገድ አይገኝም….አንዱ ጋብቻ ውስጥ የሚፈጠረው ችግር ከሌላው ጋብቻ ችግር በአይነትም በይዘትም ፍፁም የተለየ በመሆን ችግሩን ለማስተካከል የሚወሰደውም እርምጃ የዛኑ ያህል የተለያ ነው፡፡በዛ ላይ ሁሉም ችግሮች እዲፈቱ  በጥንዶቹ  መካከል  ስክነት፣  ትዕግስትን፣ጥረትን  እና   እራስ  መግዛትን ይጠይቃል፡፡አሁን ልብ በሉ ፣ጥረታችን በመካለላችሁ ያላውን ግጭትና ጭቅጭቅ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይደልም..አይ እንደዛማ አይሆንም እናንተ ሰው ናቸው፣ሁለት ሰዎች ደግሞ በአንድ ጣሪያ ስር አብረው እስከኖሩ ድረስ በሆነ ነገር መነጋገራቸውና በነገሩ ላይ የተለያየ ተቃራኒ ሃሳብ ማንፀባረቃቸው አይቀርም…ስለዚህ መነጋገርና መጨቃጨቃችሁ ኖርማል ነው…አሁን ምንድነው ምናደርገው በማንኛውም ጉዳይ ላይ አለመግባባት ተከስቶ ስትነጋገሩ በምን መልኩ ነው ኮምንኬት የምታደርጉት..?ነገሩን ማስረዳትና ማሳመን ላይ ነው ትኩረታችሁ ወይስ ያንን ምክንያት አድርጎ በስድብና በዘለፋ ማጥቃትና ልብ መስበር…አያችሁ ትልቁ ችግር መጋጨታችን ሳይሆን በያንዳንዱ ግጭታችን አንዳችን ለሌላቸውን የልብ ቁስለትና የነፍስ ህመም መስጠታችን ነው፡፡ማጥፋት ያለብን እርስ በርስ መወጋጋቱን ነው…አንዳችን ሌላችን ላይ በምንም አይነት ሰበብ የሚያቆስል ጦር አስበን አይደለም አምልጦን እንኳን መወርወር የለብንም፡፡ እርስ በርስ ከፍ ባለ ቃላት በተነጋገራችሁ ቁጥር ደግሞ እየተጣላችሁ መሆኑን አታስቡት..መጣላት ቃሉ እራሱ አሉታዊ ነው፡፡እየተጣላችሁ ሳይሆን በጋለ ስሜት እየተነጋገራችሁ ነው፡፡በቃ እንዲህ ነው ማሰብ ያለባችሁ፡፡እንደዛ ካሰባችሁ ቀጥታ ችግሩ በጋለ ስሜት መነጋገራች ብቻ ስለሆነ ስሜታችሁን በማረጋጋት ነገሩን ትፈታላችሁ፡፡እየተጣላን ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ግን ገና ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው ወይም ሽማግሌ ልትፈልጉ ነው፡፡ልብ በሉ ጮክ ብሎ መናጋገር ሁል ጊዜ መጣላት አይደለም ..አዎ አብዛኛውን ጊዜ በጋለ ስሜት መነጋገር ነው፡፡ሌላው በምንም አይነት ሁኔታ ንግግራችሁ ሰው ፊት አይሁን፡፡የምንወደው ሰው ላይ ያለንን ቅሬታ ብቻውን በሆነበት ጊዜ ነው መናገር ያለብን…እንደዛ ሲሆን ነው ውጤታማና ጥፈቱን ለማረም ፍቃደኛ የሚሆነው…ወቀሳው..ሰው ፊት ሲሆን ግን ሰውዬው የበለጠ በእኛ ቅሬታ እንዲያድርበት መንገድ ያመቻቻል፡፡ ‹‹እንግዲ ሁላተችሁም እንደምታውቁት አሁን ለእኛ እዚህ መገኘት ዋናዋ ምክንያት በፀሎት ነች፡፡እኔ በስራ በተለይ ከሀገር ውጭ በነበርኩበት ጊዜ በጣም ብዙ ባለትዳሮችን አማክሬያለሁ ትዳራችውም መካከል ያለውን ችግር በመተጋገዝ ለመፍታት ችያለሁ....በብዙዎችም ረክቼለው..ከብዙ ቤተሰቦች ጋርም እቤተሰብ ለመሆን ችያለው….ግን እመኑኝ እንዲህ እንደእናነተ የተለየ ጉዳይ ገጥሞኝ አያውቅም›› ‹‹የተለየ ስትል?››
Telegram Center
Telegram Center
Channel