….ከሶስት ቀን በኃላ
አቶ ለሜቻ ነገሮችን ተቀብለው….ቱታቸውን ለብሰውና ሌሎች ሁለት ሰዎችን ቀጥረው ቀጥታ ቤቱን ወደመገንባት ስራ ገቡ..ይሔ ሁኔታ የቤቱን ሰው ሁሉ በጣም ሲያስደስት በፀሎትን ደግሞ በይበልጥ አስፈነጠዛት፡፡ቢያንስ አንድ ነገር ልታደርግላቸው በመቻሏ የውስጥ እርካታ ተሰማት….ማንነቷን በሚያቁበት ቀን መልሰው ብስጭት እና ቁጭት ውስጥ እንደሚገቡ እርግጠኛ ነች..ቢሆንም ግን ምርጫ ያላትም…በዚህ ጉዳይ ላይ እሷቸው ትክክል ናቸው ብላ አታስብም…ሰው እርስ በርሱ መረዳዳትና አንዱ የሌላውን ኑሮ ማቃናት ያለና የነበረ ተግባር ነው….እሷቸው ይሄንን ጉዳይ ከክብር አንፃር ማየታቸው የእሷቸውን ኑሮ ብቻ ሳይሆን የጠቅላላ የቤተሰቡ ኑሮ እየጎዳ ያለው፡፡
ስራውን ከጀመሩት በኋላ እንደፊቱ አልከበዳቸውም..እንደውም ይበልጥ ጉጉት አሳደረባቸውና ከወር በኃላ ለሚከበረው ከልጃቸው የ3ተኛ አመት የሙት አመት መታሰቢያ ቀን በፊት ጥንቅቅ አድርገው መጨረስ አቅደው ቀን ከሌት መስራት ጀምረዋል፡፡አዎ ልጃቸው በህይወት ብትኖር ኖሮ እሰከዛሬ ይሄንን ቤት ሰርታ እንደምትጨርስ ያምኑ ነበር…አሁንም የሙት አመት መታሰቢያዋን ሲደግሱ የሙት መንፈሷ ሊያያቸው እንደሚመጣ እርግጠኛ ናቸው… ታዲያ ያንን ጊዜ ለእነሱ ቤት መስራት ህልሞ ስለነበረ ተሰርቶ ስታየው በጣም ደስ ብሏት እንደምትመለስ እርግጠኛ ናቸው…፡፡
እንደ ወትሮ መሽቶ ቤተሰቡ ሁሉ ተሰብስበው በሳቅና በጫወታ እራታቸውን በልተው ቡና ተፈልቶ ተጠጥቶ ከተጠናቀቀ በኃላ አምስት ሰዓት አካባቢ ሁሉም ሰው ወደመኝታው ሄደ…ፊራኦልም የውስጡን በውስጡ ይዞ ልክ እንደወትሮ እንደተኛ ሰው ሆኖ አደፈጠ…..በጨለማ ውስጥ አፍጥጦ እስከሰባት ሰዓት ድረስ በሀሳብ ሲባትት ነበር…ልክ ሰባት ሰዓት ሲሆን ቀስ ብሎ ከተኛበት ሶፋ ላይ ተነሳና መብራቱን አበራ ..የቤቱን ዙሪያ ገባ ቃኘ….በፀሎትና ለሊሴ ተዘረጋግተው እንደተኙ ነው፡፡ከወላጆቹ ክፍልም ምንም የሚሰማ እንቅስቃሴ የለም…..ቀስ ብሎ ወደሴቶቹ መኝታ ተጠጋ… ሁለቱም አይናቸውን ጨፍነው ጥልቅ የሚባል እንቅልፍ ውስጥ ናቸው፡፡ይሄኔ ህልም እያለሙ እንደሚሆን ገመተ…ቀስ አለና በፀሎት በተኛችበት በኩል ዞሮ ከራስጌዋ ጎን ካለ መቀመጫ ላይ ተቀመጠ…ቁልቁል አዘቅቆ አያት…ቀስ ብሎ እጁን ዘረጋና ፊቷ ላይ የተጠቀለለውን ሻርፕ ጫፍ ይዞ ጎተተው…ቀስ በቀስ ከፊል ፊቷ እየታየው መጣ …ሻርፑን ሙሉ በሙሉ ከፊቷ አስወገደእና በትኩረት ይመለከታት ጀመር…..ድንገት ተገላበጠችን በጀርባዋ ተንጋለለች ..በዛን ጊዜ ሙሉ በሙሉ ለእይታው ተጋለጠች….አሁን እርግጠኛ ሆነ…ምንም እንኳን የተወሰነ መጓሳቆል ቢታይባትም …ምንም እንኳን ቀኝ የፊቷ ክፈል ላይ ብዛት ያላቸው ጭረቶችና ጠባሳዎች ቢኖሩም እራሷ ነች…ለአመታት በድብቅ ከሩቅ ሲያያት የነበረችው..የእህቱን ውድ ልብ በውስጧ የተሸከመችው ልጅ….
‹‹እሺ አሁን ምንድነው የማደርው?››እራሱን ጠየቀ…ቀስ ብሎ ሻርፑን መልሶ ፊቷን ሸፈነና ከተቀመጠበት ተነስቶ መብራቱን አጠፋና ወደ መኝታው ተመለሰ….ሙሉ ለሊቱን እንቅልፍ ሊወስደው አልቻለም…..
አሁን ያወቀውን ነገር ባያውቅ ምኞቱ ነበር….አንዳንድ ማወቆች ሸክማቸው ያጎብጣል..አውቆ የሆነ ነገር ማድረግም አለማድረግም እዲህ አስቸጋሪ ሲሆን ምነው ምንም ነገር ባላወቅኩ ኖሮ ያስብላል፡፡ይህቺን ልጅ አፍቅሯት ነበር…የሞች እህቱን ልብ የተሸከመችው ልጅ መሆኗን ሳያውቅ በፊት ከእሷ ፍቅር ይዞት ነበር..ለእሷም ሆነ ለማንም ይሄንን ስሜቱን ተናግሮ አያውቅም….ግን እሱ በፍቅር እንደተነደፈ እርግጠኛ ነበር‹‹እሺ አሁን ምንድነው የማደርገው….?››እራሱን ጠየቀ…ብዙ ጊዜ ስለፍቅር ና ውበት ሲያወራ እርዕስ የምትቀይረውና ወሬውን የምትገፋው ለምን እንደሆነ አሁን ገባው…‹‹ይህቺ ልጅ ተአምረኛ ነች››ሲል አሰበ‹‹እራሷን በበሬዱ ቦታ ለመተካት እየጣረች ነው…አዎ ወደቤታችን የመጣችው ድንገት በአጋጣሚ ሳይሆን ሆነ ብላ አስባና አቅዳበት ነው… አንተ ወንድሜ ነህ ስትለኝ እንዲሁ ለአባባል ብቻ የምትጠቀምበት ይመስለኝ ነበር..ለካ እሷ ከአንጀቷ ነው፡፡››ሲል አሰበና በድቅድቅ ጨለማው ፈገግ አለ….‹‹ይሄን ጉድ ወላጆቹ ሲሰሙ ምን አይነት ምላሽ እንደሚሰጡ አሰበ…..ለመገመት አንኳን አልቻለም፡፡በተለይ አባቱ በበሬድ ጉዳይ ስሜተ ስስ እንደሆነ ያውቃል….ፈራ …በጣም ፈራ…. ‹‹ግን እሷስ እስአመቼ እንዲህ ከወላጆቾም ተሰውራ እውነቱን ከእኛም ደብቃ ትዘልቃዋለች..?እቅዷ ምንድነው?››ሊገባው አልቻለም፡፡
✨ይቀጥላል
✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link
👇
https://www.youtube.com/@atronose