View in Telegram
አስገራሚ እውነታዎች
ዛንዛኒንን ነው የምጠራልህ ፡ ሲባል የማይፈራ ህጻን የለም ። ...... የዚህ ልጅ እናት ፡ ይህንን ህጻን የገኘችው ፡ ከአመታት የልጅ ናፍቆት በኋላ ነው ። ከሱ በፊት አምስት ልጅ ወልዳ በሞት አጥታቸዋለች ። እና በመጨረሻ ግን አንድ ልጅ ወለደች ። ዛንዛኒ ስልት ስም አወጣችለት ። ሆኖም የወለደችው ልጅ ፡ ከሌላው ሰውነቱ አንጻር ሲታይ የጭንቅላቱ መጠን አነስተኛ ነበር ። ይህም ገፅታው የተለየ አይነት መልክ ይሰጠው ጀመር ። ...... ይህም ገፅታው በመንደሩ ሰወች እንዲያገሉት ምክንያት ሆነበት ። በመንደሩ ውስጥ ህጻናት ሲጫወቱ አይቶ አብሮ ለመጫወት ሲጠጋ ፡ የያዙትን መጫወቻ ጥለው ይሮጣሉ ። ወላጆች ልጆቻቸው ሲያጠፉ ፡ ዛንዛኒን ነው የምጠራልህ በማለት ልጆቻቸውን ያስፈራሩበት ጀመር ። ይህ የማግለል ነገር በዚህ አላበቃም ። የመንደሩ ሰወች ሲያዩት ጦጣው እያሉ ይሰድቡት ፡ ጀመር ። ብቸኛ ፍቅር የምትሰጠው ፡ እናቱ ነበረች ። ዛንዛሚ ኤሊ ፡ በእድሜ እያደገ መጥቶ ፡ ትምህርት ቤት የሚገባበት ጊዜ ደረሰ ። እናቱ ይዛው በአካባቢው ወደሚገኘው ት/ቤት ይዛው ሄደች ። ሆኖም የመገለሉ ደረጃ ከፍተኛ ሆኖ ነበርና ፡ ወደትምህርት ቤት ለመሄድ ሲሞክር ፡ ተማሪዎች ከጦጣ ጋርማ አንማርም እያሉ ሰላም ነሱት ። .... ይህ የማግለልና የጥላቻ ሁኔታ ፡ እየባሰ ሲነጣም ፡ ሁሉን ነገር ተወላቸውና ፡ ጫካ ገባና ፡ ውሎው እዛ ሆነ ። ዛፍ ለዛፍ እየተንጠላጠለ ዱር ውሎ ይገባል ። ....... እናትና ልጅ ፡ በዚህ ሁኔታ ፡ የመንደሩ ሰው አግልሏቸው ፡ ለአመታት ኖሩ ። ሆኖም ግን ታሪክ ሊለወጥ ግድ ሆነና ፡ ይህንን የዛንዛኒን ሁኔታ የሰማ አንድ የአፍሪማክስ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ወደ መንደራቸው መጥቶ ፡ የደረሰባቸውን መገለልና ፡ የድህነት ህይወታቸውን በተመለከተ ፡ አንድ ሰፊ ዶክመንተሪ ተሰርቶ በቴሌቪዥን ተላለፈ ። ይህ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሚሊዮኖች ተመለከቱት ። ከቀናት በኋላም ዛንዛኒ ኤሊንና እናቱን ለመርዳት የጎ ፈንድ ሚ አካውንት ተከፈተ ። ....... በአውሮፓ አሜሪካና አፍሪካ የሚገኙ ፡ ፕሮግራሙን የተከታተሉ ሁሉ ፡ ለዚህ ቤተሰብ ደግነታቸውን አሳይተው ብዙ ገንዘብ ተሰበሰበ ። ........ ህይወታቸው ተቀየረ ። ዘመናዊ ቤት ተገነባላቸው ። ለእናትየው የስራ እድል ተከፈተላት ። ያ ፡ ጦጣው እየተባለ ጫካ የሚውለው ዛንዛኒ ኤሊ ፡ ለአመታት አብራው ያረጀችውን አሮጌ ልብስ ጣለ ። በደርዘን የሚቆጠሩ ዘመናዊ ልብሶችና ጫማዎች እየቀያየረ የሚለብስ ፡ ዘናጭ ሰው ሆነ ። ትምህርት ቤት ገባ ። አስጠኚ ተቀጠረለት ። ትምህርት ቤት የሚሄደው በሹፌር ነው ። አሁን ያ የድሮው ማግለል የለም ። የመንደሩ ልጆች ፡ ብስክሌት እንዲያስነዳቸው የሚከቡት ። ከሱ ጋር ለመጫወት በልጆች የሚከበብ ሰው ሆኗል . ይህን በተመለከተ እናትየው ስትናገር ፡ ፈጣሪ አንድ ቀን ታሪካችንን እንደሚለውጠው አምን ነበር ብላለች ። ....... ደጋግና ፡ መልካም አሳቢ ሰወች እስካሉ ድረስ ተባብረው የማይቀይሩት ነገር የለም
።
Share
Telegram Center
Channel
Join