View in Telegram
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
የእንግሊዝኛው የዘረኝነት ቃል የሆነው N* word (Nig**) መሠረቱ የት እንደሆነ ያውቃሉ? እንዳለመታደል ሁኖ የቃሉ መሠረት መጽሀፍ ቅዱስ ሲሆን ቃሉም የሚገኘው በሐዋርያት ስራ 13:1 ላይ ነው። እንደሚከተለው ይነበባል፦ “በአንጾኪያ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም፦ በርናባስ፣ #ኔጌር የተባለው ስምዖን፣ የቀሬናው ሉክዮስ፣ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስ አብሮ አደግ የነበረው ምናሔና ሳውል ነበሩ።” — ሐዋርያት 13፥1 (አዲሱ መ.ት) በዚህ አንቀጽ ውስጥ ኔጌር የሚለው ቃል በእንግሊዝኛው Nig*er ተብሎ የተቀመጠ ሲሆን የዚህ ትርጉም መሠረት የሆነው የግሪኩ ቃል Νίγερ ነው። ይህም ማለት ትርጉሙ "ጥቁር" ማለት ነው። ግሪኩ ሲነበብም ቀጥታ ለዘረኝነት በሚውለው ቃል መሠረት neeg'-er ተብሎ ነው። እንደ ሜሪያም ዌብስተር መዝገበ ቃላት መሠረት ቃሉ የቆዳ ቀለምን ለመግለጽ ሳይሆን የለየለት ዘረኝነትንና ጥላቻን ለመግለጽ አገልግሎት ላይ የሚውል ቃል መሆኑን ይጠቅሳል። "..the word ranks as almost certainly the most offensive and inflammatory racial slur in English, a term expressive of hatred and bigotry..." ባህላቸው Judeo-Christian ነው የተባሉት የክርስቲያን ሀገራት፣ የጥላቻ ቃላቸው መሠረቱ መጽሀፍ ቅዱስ መሆኑ ያሳዝናል። ⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻ የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.center/Yahyanuhe
Share
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Find friends or serious relationships easily
Start