View in Telegram
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
Photo
በቅርቡ አንድ "እፎይ" ለሚባል ሰው መልስ መስጠት ጀምሬያለሁ። ግለሰቡን የእውነትም ተከታትየው ካለማወቄ አንጻር ሰዎች መልስ እንዲሰጠው አብዝተው ቪዲዮ ሲልኩልኝ ነው በደንብ ማየት የጀመርኩት። መጀመሪያ ሳየው ጤነኛ/Stable/ አልመሰለኝም ነበር። እንደመጣለት የሚሰነዝራቸው ጸያፍ ቃላት፣ የጤነኛ የማይመስሉ አካላዊ ተግባራቱ አንድ ላይ ተደማምረው ይህ ሰው በምን ተአምር በብዙ ኦርቶዶክስ ምዕመን ዘንድ እንደ "ብጹእ" እንደታየ ደንቆኝ ነበር። "የሊቃውንት አድባር ነኝ" የምትለዋ ቤተ ክርስቲያን አቃቤዎቿ ተንጠባጥበው አልቀው የቀሩት እነዚህ ከሆኑ በእርግጥም ስለቤተ ክርስቲያኗ አሁናዊ ሁኔታ የሚጠቁመን ብዙ ነገር አለ ማለት ነው። ወደ ዋናው አጀንዳየ ስመለስ እነዚህን ምላሽ መስጠት የጀመርኩባቸውን ቪዲዮዎች አስመልክቶ አንድ ወንድም ጋር ሀሳብ እየለተዋወጥን ነበር። በወሬያችን መሀል ተመልካች አለመኖሩ እንዳሳዘነው ነገረኝ። ግራ ተጋብቸ ቪዲዮዎቹን ገብቸ አየኃቸው፣ እይታቸውን ትቸ ቪዲዮው አስፈላጊ ነው ብለው ሼር ያደረጉ ሰዎችን ብዛት ተመለከትኩት። የአንደኛው ከ1ሺ የሚበልጥ ሲሆን የሌላኛው ደግሞ ከ2 ሺ ይበልጣል። ትምህርቱን ሼር ያደረገው ሰው ብቻ በሺ የሚቆጠር ነው። የወንድሜ የተከታታይ ማነስ ያሳዘነው ለምን እንደሆነ ገብቶኛል። ምላሽ የምንሰጣቸው ሰዎች ያላቸውን የተከታታይ መጠን በማየት ነው። ግን መርሳት የሌለብን ተለፍቶ የተሰራን ቪዲዮ በጥንቃቄ የተመለከተ 1 ሺህ ሰው ካለ ትልቅ ነገር ነው። በየቦታው 50 የማይሞላ ሰው በአንድ ክፍል ውስጥ ለማስተማር ብዙ ኡስታዝ ተዘጋጅቶና ለፍቶ ይሔዳል። በዚህ ቴክኖሎጂ ሳቢያ 1ሺ ሰው ካየ ደግሞ ትልቅ ነገር ነው። ዋናው ጉዳይ ኢኽላሱ እንደመሆኑ መጠን እሱ ሳይሸራረፍ ካለ ስራዎች ዘመን ይሻገራሉ። እንደ አንድ ወቅት የዘመድኩን ተመልካቾች የሙቀት ሰው ሁነው በሺህ ቢከቧቸው የሆነ ቀን ሌላ የተሻለ የሙቀት አጀንዳ ሲመጣ ደግሞ ጥለዋቸው ይሄዳሉ። ከዚያ የሙቀት ተመልካች የቁምነገር ተከታታይ 100 ካሉ አጀንዳ መሆን ያለባቸው እነሱ ብቻ ናቸው። ሰለፎች በኻለቃቸው ብዙዎቹ የሚያስተምሩት ከ10 የማይበልጥ ተማሪ ነበር። ስራቸው ግን ዘመን ተሻጋሪ ሁኖ ከምዕተ አመታት በኃላም አሁን ድረስ ተሻግሮ የማይቋረጥ ሰደቃ ሁኖላቸዋል። እኛ ከነሱ ጋር ለውድድርም የማንቀርበው ደግሞ በሚገርም ሁኔታ ከነሱ ዘመን የተሻለ ተከታታይ አለን። ህዝባችንን ወደ ሚጠቅመው ነገር ለማምጣት ከሆነም አላማችን ከወቀሳ ይልቅ ሌላ በርካታ መንገዶችን በመጠቀም መሳብ የተሻለው መንገድ ነው። የሰው ልጅ አምቢሺየስ ቢሆንም በንጽጽር ወንድሞች በኩል በተለይም በቲክቶክ እየተሰራ ያለውም ስራ መልካም የሚባል ነው፣ ነገ ደግሞ በአላህ ፍቃድ የተሻለ ይሆናል። ⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻ የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.center/Yahyanuhe
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Find friends or serious relationships easily