View in Telegram
በኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ውስጥ ከመነሻው ጀምሮ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን የተተቸ፣ የተወገዘ ከዚያም አልፎ በጠቅላይ ሚንስትር ደረጃ ሳይቀር ስሙ በክፉ ተነስቶ "የተወነጀለ" ተቋም ኦርቶዶክስ ውስጥ አላውቅም። ድኅረ ደርግ ድርጀቱ ከተመሰረተ ጀምሮ ያሳለፋቸውን ሒደቶች ማጥናት ለሚፈልግ ብዙው መረጃ ለማግኘት ምቹ ነበርና ከጓደኞቼ ጋር በቅርበት ለማየት ችለናል። ከድርጅቱ ቀደምት መስራቾች ጀምሮ አሁን እስካሉት ድረስ ለእስልምና ያላቸው አሉታዊ አመለካከት የሚታወቅ ቢሆንም ድርጅቱን ለማቆም የከፈሉት መስዋዕትነት ግን የሚካድ አይደለም። ተቋሙ እንዲበረታ የግል ኢጓቸውን ከማፈን ጀምሮ ግለሰቦች ያልገነኑበት ተቋም እንዲሆን በሲኖዶሱ አጋዥነት (ኃላ ተቃርኖ ውስጥ ቢገቡም) ሰፊ ስራ ለመስራት ሞክረዋል። ሰንበት ት/ቤቶችን ማደራጀት፣ የግቢ ጉባኤዎችን መምራትና ማገዝ፣ ኦርቶዶክስ ገጥሟት የነበረውን የተሀድሶ ፈተና በመታገል ረገድ የሰሩት ስራ ቀላል አልነበረም። አሁን ላይ በተለያዩ የፖለቲካ አመለካከት የምታዮቸው ታዋቂ ግለሰቦች ሁሉ በአንድ ወቅት በአንድ ላይ የተሰባሰቡበትና በሙያቸው ድርጅቱን ያገዙበት ነበር። በመዋቅር ደረጃ እንደ ኢትዮጵያ ሰፊ ቅርንጫፍ በመክፈት፣ ከፍተኛ ፋይናንስ በማንቀሳቀስ፣ ሰፊ የሰው ኃይል በመምራትና የተደራጀ የሚዲያና ኮሚንኬሽን በማዋቀር ከሲኖዶሱ ያልተናነሰ ኔትዎርክ በመላ ሀገሪቱ መፍጠር ችለዋል። እንደ አንድ ተቋም በተለይም ለእምነቱ ሰዎች ሞዴል መሆን የሚችል የተቋም ግንባታን ሰርተው አሳይተዋል። የዛሬ 10 አመት ገደማ የሙስሊሙ የዳዕዋ እንቅስቃሴ ከወትሮው ከፍ ያለበት ጊዜ ነበር። በመሀል የመጡት የመንግስት ጭቆናዎች መነቃቃቱ ላይ ውሀ ቢቸልሱበትም ባልታሰበ መልኩ ደግሞ ለጭቆናው የተሰጠው ግብረ መልስም ሌላ የመነቃቃት ምዕራፍን የፈጠረ ነበር። ያንን ጥንካሬና አንድነት እንዲሁም መስዋዕትነት ለተመለከተ ሰው ከጥያቄው መልስ በኃላ ሁሉም ነገር ይቀዛቀዛል ብሎ የጠበቀ ያለ አይመስለኝም። መሪዎቹም ሆኑ ከጀርባ የነበሩ አስተባባሪዎች ያንን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ወደ ተቋም ለማምጣት የተሻለ እድሉም አቅሙም ነበራቸው። ተቋም መገንባቱን መጅሊሱ ላይ ብቻ ተውነውና አጋዥ ተቋማትን የመፍጠሩ ሒደት ላይ ተዘናጋን። ለዚህ በርካታ የግል ምክንያቶች/ኡዝሮች ሊነሱ ይችላሉ፣ እድሉን በማባከን በኩል ግን የሚለውጡት ነገር የለም። በተበታተነ መልኩ ከሚደረጉ ያልጠረቁ ስራዎች በተሻለ ግለሰብ ያልገነነባቸው አሰባሳቢ ድርጅቶች እውን ቢሆኑ መልካም ነበር። ዘመንም ትውልድም መሻገር የሚችሉት "ተቋም" ሲሆኑ ነው። መጭው ጊዜም አንዳለፉት አመታት እንዳይባክን ዱዓ እናድርግ.! አንዳንድ የሚባክኑ እድሎች ድጋሚ በቀላሉ አይገኙም።
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Find friends or serious relationships easily