View in Telegram
ጣልያናዊው ጓድ ፍራንኮ ፎንታና የፍልስጤማውያን ሰቆቃ ሲያንገሸግሸው ለነጻነታቸው ሊታገል በ1970ዎቹ ፍልስጤም ምድር የከተመ ሰው ነበር። በወቅቱ የነበሩ ሙጃሒዶችን በተለይም በሮኬት ተኩስ ካገዙ ወታደራዊ ጠበብቶች መካከል ነበር። በመጨረሻም በጣልያን ያፈራውን ንብረት ሁሉ በመሸጥ ለትግሉ አበረከተ። ይህ ቀና ሰው በስተመጨረሻም አላህም ﷻ ሒዳያውን ወፍቆታል። በ2005 እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ ለፍልስጤማውያን ህዝቦች ነጻነት ሲታገል እድሜውንም፣ ህይወቱንም፣ ንብረቱንም ሰውቷል። በመጨረሻ ጊዜዎቹ ከተናገረው ውስጥ፦ "ምናልባት እኔ የፍልስጤማውያንን ነጻነት ለመመልከት አልታደልኩ ይሆናል፣ ግን ያለምንም ጥርጥር ልጆቼና የልጅ ልጆቼ የፍልስጤማውያንን ነጻነት ያያሉ። ያኔም ለዚህች የተባረከች ምድር የከፈልኩትን መስዋዕትነት ይረዳሉ" አላህ ﷻ ይዘንለት፣ ያለምንም ጥርጥር ቁድስ ከወራ*ሪዎቿ ነጻ ትሆናለች - ኢንሻአላህ..! https://t.center/Yahyanuhe
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Love Center - Dating, Friends & Matches, NY, LA, Dubai, Global
Find friends or serious relationships easily